2015-01-16 17:12:30

የር.ሊቃ.ጳጳሳት ሐዋርያዊ ዑደት በፍሊፒን ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በስሪላንካ ያካሄዱት የነበረውን ሐዋርያዊ ዑደት አጠቃልለው ፍሊፒንን በተመሳሳይ ለመጐብኘት ርእሰ ከተማ ማኒላ ገብተዋል።
ቅድስነታቸው ከማኒላ ርእሰ ከተማ ኮሎምቦ ወደ ማኒላ ፍሊፒን በበረሩበት ግዜ አውሮፕላን ውስጥ ከጋዜጠኞች ጋር ቆያታ ያደረጉ ሲሆን የፍሊፒን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ድሆች ማእከል ያደረገ መሆኑ አስታውቀዋል። በፍረንሳይ ፓሪስ ላይ በአሸባሪዎች የተፈጸመው ጥቃት በተመለከተ ተጠይቀው ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መሰረታዊ መብት መሆኑ ጠቁመው ሃይምኖት የማላገጥ ሰለባ መሆን አይገባም ብለዋል። ቅድስነታቸው በፍሊፒን ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ማኒላ ቪላ ሞር ኤይር በይዝ አውሮፕላን ማረፍያ እንደ ደረሱ የሀገሪቱ ቤተ ክርስትያን እና የመንግሰት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ቅድስነታቸው ከየማኒላ ቪላ ሞር ኤር በያዝ አውሮፕላን ማረፊያ ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተጉዘዋል። ከአጭር ቆይታ በኃላ ለሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የክብር ጉብኝት ለማድረስ በመኪና ወደ ማላካኛን ቤተ መንግስት ተጉዘዋል ርእሰ ብሔር በኒኞ አኲኖ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለቅድስነታቸው በደስታ የሟላ ሙቅ አቀባበል አድረገውላቸዋል።የእንኳን ደህና መጡ 21 ግዜ መድፍ ተሰምቶ የቅድስት መንበር እና የፍሊፒን ብሔራዊ መዝሙሮች ተደምጠዋል።ድስነታቸው እና ርእሰ ብሔሩ ሙዚክ ሩም በተባለ ቤተ መንግስታዊ አዳራሽ በግል ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው እንዲሁም ርእሰ ብሔሩ ቤተ ሰቦቻቸውን ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳስተዋወቅዋችው ተመልክተዋል። ጳጳሳት ፍራንሲስ እና የፍሊፒን ርእሰ ብሔር ስጣታ ተለዋውጠው በጋራ የማስታወሻ ፎቶግራፍ ተነስተዋል። በሐዋርያዊ መርሀ ግብር መሰረትም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቤተ መንግስት አዳራሽ ከጠበቅዋቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት እና በሀገሪቱ የተመደቡ ዲፕሎማቶች ጋር የገናኙ ሲሆን ፡ የፍሊፒን ፕረሲዳንት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ከባለስልጣናቱ እና ዲፕሎማቶች ጋር አስተዋውቀው በስማቸው እና በየፍሊፒን ህዝብ ስም የእንኳን ደህና መጡ አጭር ንግግር ያደረጉ ሲሆን የፍሊፒን ቆይታቸው መልካም እና ስኬታማ እንዲሆን ተመኝትውላቸዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለየመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጥናት እና ለዲፕሎማቶቹ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፕረሲዳንቱ ላደረጉላቸው መልካም አቀባበል ላሰሙት ንግግር እና በፍሊፒን ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ለተሰጣቸው ዕድል አመስገነው ሐዋርያዊ ዑደታቸው ሐዋርያዊ ባሕርይ ያለው መሆኑ በመጥቀስ የፍሊፒን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሀገሪቱ ውስጥ ቅዱስ ወንጌል የተበሰረበት አምስተኛ ሚእተ ዓመት ለማክበር በምትዘጋጅበት ግዜ መሆኑ ጥልቅ ደስታ እንደ ሚሰማቸው አስገንዝበዋል ።ክርስትያናዊ መልዕክቱ በሀገሪቱ ባህል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ አመልክተው ሐዋርያዊ ጉብኝቴ ከአንድ ዓመት ሁለት ወር ገደማ ያላንዳ በተባለ ተፈጥሮአዊ ኃይለኛ ማዕበል ሕይወታቸው ላጡ ከፍሊፒን ህዝብ ጋር ለመጸለይ ለተረፉ እና ከባድ ጉዳት ለደረሳቸው ለማጥናናት የስቃያቸው ተሳታፊ መሆኔ ለመንገር ከሃገሪቱ ድሃ ማህበረ ሰቦች ጋር ለመገናኘት ማእከል ያደረገ መሆኑ ለመግለጥ እወዳለሁኝ ብለው ያሉ ቅድስነታቸው መቅሰፍቱ እንደተከሰተ ለዚሁ አደጋ ሰለባ ከሆኑ ለተባበሩ የቤተ ክርስትያን ተቋማት አባላትም ሆነ የሲቪል ድርጅቶች ላመስገናቸው እወዳለሁ ብለዋል። በበርካታ ተጓራባች ደሴቶች የቆመችው ፍሊፒን ከሌሎች የኤስያ ሀገራት ጋር በመሆን ዘመናዊ እና ቀዋሚ ሕብረተ ሰብ ለማነጽ በሂደት ላይ እንደሆነች ጠቁመው ሰብአዊ መብት አክባሪ ፈሪሀ እግዚአብሔር የተላበሰ ድሆችን የማያገል ሕብረተ ሰብ ቢገነባ ሐለፌታ ነው ብለዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለየመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረው ይሰናበቱ እና ከዛ አምስት ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው የማኒላ ጽንሰተ ቅድስት ድንግል ማርያም ካተድረል በመኪና ተጉዘዋል። ካተድራሉ ጠቅላላ የሀገሪቱ አብያተ ክርስትያናት እናት ተብሎ የሚጠራ በ1581 እንደ ኤውሮጳውያን አቆጠጠር የተቆረቆረ ካተድራል ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ካተደራሉ ትንሽ ባሲሊክ ተብሎ እንዲሰየም መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን ለእድሳት ከ2012 እስከ ላፈው ወርሀ ሚያዝያ እኤአ ዝግ መኖሩ እና በየማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ሉዊስ አንቶንዮ ታግለ በመሩት ሥርዓተ ቅዳሴ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሁለት ሺ ምእመናን የማያዝ ዓቅም ያለው ነው ።ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ካተድራሉ እንደ ደረሱ ቅጥር ግቢ እና አከባቢ የተገኙ በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናን በደስታ እና በጭብጨባ ተቀብሎዋቸዋል ።
ሁለት ሺ ምእመናን ጳጳሳት ካህናት መነኲስያት እና መነኮሳን ካተድራሉ ውስጥ ተገኝተው ነበር ቅድስነታቸው በካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ተሸኝተው ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል፡በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ፡ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የላኩት ዘገባ እንደሚያመለክተው ፡ከሥርዓተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኃላ ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ከመመለሳቸው ማኒላ በአንድ ፈርንሳዊ ካህን አባ ማትዩ እንክብካቤ የመንገድ ተዳዳሪ ሕጻናት ወደ ሚገኙበት ቦታ ተጉዘው ከሕጻናቱ ጋር ተገናኝተዋል ለሕጻናቱም ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል። ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተመልሰው የሀገሪቱ ውሉደ ክህነት ያካተተ እና ከሸኙዋቸው ብጹዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ለምሳ ተቀምጠዋል። የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የፍሊፒን ሐዋርያዊ ዑደት መርሀ ግብሩ ፋታ የማይሰጥ በተቀራረበ ድርጊት የተዋቀረ እንደሆነ የተመልከተ ሲሆን ከትንሽ ዕረፍት በኃላ ከሀግሪቱ ቤተ ሰቦች ጋ ለመገናኝት Mall of Asia Arena ወደ ተባለ ትልቅ አዳራሽ ተጉዘዘዋል ።
በዚሁ አዳራሽ ሲጠባበቅዋቸው የቆዩ ቤተ ሰቦች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በየማኒላ ረኪበ ጳጳሳት የቤተ ሰብ ኮሚስዮን ሊቀ መንበር የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል ለተደረገላቸው አቀባበል በማመስገን ባሰሙት ንግግር ቅድስነታቸው ከየቤተሰቦች አባላት ጋር በጋራ ሥርዓተ ጸሎት ካደረጉ በኃላ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል ፡ ወደ የሚያርፉበት ቤተ ሊቀ ጵጵስና ተመልሰዋል በዚህ የዕለቱ ሐዋርያዊ መርሀ ግብሩ ተጠናቅቀዋል። ነገም ቀጥሎ ይውላል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.