2015-01-16 15:54:11

በጌታ መኖር


RealAudioMP3 የተወደዳችሁ ቤተሰቦች በክርስቶስ የተወደዳችሁ ሁሉ
በዚህ ምሽት እዚህ ተገኝታችሁ የመሰከራችሁት ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያኑ ያላችሁ ፍቅር ለማዳመጥ በመቻሌ እድለኛ ነኝ፣ የእንኳን ደህና መጡት ንግግር ላስደመጡት ለፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቤተሰብና የሕይወት ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ረየስ አመሰግናለሁ። በተለይ ደግሞ በዚህ ግኑኝነት ህያው የምስክርነት ቃል ላስደመጡት አመሰግናለሁ።
ቀድሞ በተነበበው ወንጌል ቅዱስ ዮሴፍ በእንቅልፍ ላይ እያለ በመልአኩ አማካኝነት የእግዚአብሔር ፈቃድ ተገለጠለት፣ በተነበበው ቃለ ወንጌል ተኝቶ የሚለው ቃል ሁለት ጊዜ ተደግሟል፣ በዚህች ሰዓት ከሁላችሁ ጋር ሆኜ በጌታ ለማረፍና ስለ ሰጠው የቤተሰብ ጸጋ ለማስተንተን እወዳለሁኝ።
ዮሴፍ በእንቅልፍ ላይ እያለ የጌታ ፈቃድ ተገለጠለት፣ ማንቀላፋቱ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጥ ምክንያት ሆነው፣ ይኽም በጌታ በማረፉ ነው። በዕለታዊ ሕይወታችንና በውጣ ውረድ ደክሞን ገዛ እራሳችን ለማደስ ትንሽ ጋደም ስንል ጋደም ማለታችን ከጌታ ጋር ካደረግን ለእርሱ ፈቃድ መገለጥ ምክንያት ይሆናል በዚህ በተነበበው ቃለ ወንጌል፣ በአንደኛው ደረጃ በጌታ ማንቀላፋት፣ ከኢየሱስ ከማርያም ጋር መነሳት፣ እንደ እነርሱ ነቢያዊ ድምጽ መሆን በተሰኙት ነጥቦች ላይ ታተኩሩ ዘንድ አደራ።
በጌታ ማረፍ፦ ከድካም በኋላ አረፍ ማለት መተኛት ለጤናማ ሕይወት አሰፈላጊ ነው፣ እንደ ዮሴፍ በጌታ ማረፍ፣ እንዲህ በማድርጉም የኢየሱስ ጠባቂ አባት የማርያም እጮኛ ለመሆን በቃ፣ እናንተም እንደ ክርስቲያኖች መጠን በቤታችሁ በቤተሰባችሁ በማኅበረሰባችሁ በቁምስናዎቻችሁ እንደ ዮሴፍ ለኢየሱስ ቤት ታዘጋጁ ዘንድ ተጠርታችኋል።
የእግዚአብሔር ጥሪ ለማዳመጥና ለማስተናገድ ለኢየሱስ ቤት ለማዘጋጀት የበቃችሁ ትሆኑ ዘንድ በጌታ ማረፍ ይገባችኋል፣ ለጸሎት ጊዜ ማግኘት ይገባችኋል፣ በሥራ በቤተሰብ ጉዳይ የተጠመድኵኝ ነኝ ይቅር ለመጸለይ በሰላም ትንሽ ጋደም ለማለትም ጊዜ የለኝት ትሉኝ ይሆናል፣ እውነት ነው። ነገር ግን ካልጸለይን የማንጸልይ ከሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? አለ ጸሎት ጥድፊያችን ሁሉ አነስተኛ ውጤት ነው የሚኖረው። ስለዚህ በጸሎት ማረፍ። ይኽ ደግሞ ለአንዲት ቤተስብ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።
ከኢየሱስና ከማርያም ጋር መቆም። “ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ…” (ሮሜ. 13.11) እምነት ከዓለም አያገለንም፣ የዓለም ሳንሆን በጥልቀት ወደ ዓለም እንገባ ዘንድ ነው የሚያበቃን። እግዚአብሔር በዕለታዊ ሕይወታችን ህልው ይሆናል ማለት ነው። እንዲህ ባለ ሁነትም ጌታ ማርያምንና ዮሴፍን ከክፋት መንፈስ እንደከለላቸው ሁሉ እኛንም ይከላከልልናል።
ለዓለምና ዓለም የተደቀነበት ተጋርጦ ሁሉ ለማሸነፍ ቤተሰብ ያስፈልገዋል። ቅዱስ ፍቅር የተሞላው የቤተሰብ ውበትና ውህበት መስካሪ ቤተሰብ ያስፈልገዋል።
ነቢያዊ ድምጽ፦ ዮሴፍ በጌታ በማረፍ ኢየሱስንና ማርያምን ተንከባከብ ለሚል የእግዚአብሔር ጥሪ ለማዳመጥ በቃ። ይኸንን ጥሪ አዳምጦ በመታዘዝ በማዳን እቅድ ሱታፌ አደረገ። ከማርያም ጋር በመሆን ኢየሱስ በጥበብ በእድሜና በጸጋ ያድግም ዘንድ አብነት ሆነ። ስለዚህ ነቢያዊ ድምጽ መሆን ማለት በምንቀበለው ምስጢረ ጥምቀት አማካኝነት የእግዚአብሔር ፍቅር በቃልና በሕይወት መስካሪ አብነት መኖር ማለት ነው።
ይኽ የ 2015 ዓ.ም. የድኾች ዓመት ተብሎ መሰየሙ ብፁዓን አቡኖቻችሁ ነግረውኛል። በገዛ እራስ ከመዘጋት ተላቀን ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ክፍል እንል ዘንድ አደራ። ለድኾች ለተናቁት ማሰብ እነርሱን ማገልገል።
ውዶቼ ጌታ እናንተ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር በውስጣችሁ በጥልቀት ያኖረውም ዘንድ ዘወትር ስለ እናንተ እጸልያለሁ፣ ይኽ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር በመካከላችሁና በቤተ ክርስትያናችሁ ይገለጥ፣ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና ምህረት ያውቅ ዘንድ ጸልዩ የጸሎታችሁ ጸጋ ወደ ዓለም አድርሱ፣ የእናንተ ጸሎት ያስፈልገኛልና አደራ ስለ እኔ ጸልዩ።








All the contents on this site are copyrighted ©.