2015-01-14 15:26:53

“የምድር ዳርጃ ሁሉ የአምላካችን መዳን ያያሉ” (ኢሳ. 52.10)



RealAudioMP3 ከዕለቱ አንደኛው ምንባብ የሚያስደንቅ ትንቢት አዳምጠናል፣ ኢሳያስ ነቢይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ወደ ምርድ ዳርጃ ሁሉ እንደሚበሠር ነበየ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያረጋጋጠው ሁሉ ከሞት የተነሣው ጌታችን ሁሉንም አሕዛብ ተከታዮቹ ለማድረግ ለወንጌላዊ ተልእኮ እሺ ብለው የታዘዙት ብዙ ልከዋል (ማቴ. 28.12) ይኽው እኛም የታላቂ ወንጌላዊ ልኡክ ዮሴፍ ቫዝ የቅድስና አዋጅ ለማክበር ለተሰበሰብን ልዩና አቢይ ትርጉም ያለው ጥሪ ነው፣ ተልእኮው በቃል ብቻ ሳይሆን አብነት በካተተ ሕይወት ጭምር የዚህች አገር ሕዝብ ወደ እምነት በመምራት “አሁንም ለእግዚአብሔር ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳኑም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ” (ግብ.ሓ. 20.32) ሰጥተዋል።
ቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ እግዚአብሔር ለስሪ ላንካ ሕዝብ ላለው መልካምነትና ፍቅር ምልከት ነው፣ በወንጌላዊ ሕይወት ለመኖር በእኛ ውስጥ የቅድስናው ጥሪ ያብብ ዘንድ መላ ሕይወቱን መስዋዕት ላደረገበት እርቅ ለተሰየመው ወንጌላዊ መልእክት ለወቅታዊው ሁነት ለመመስከር የሚያነሳሳ አወንታዊ ግፊትም ነው።
በጎአ የተወለደው ቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ በወንጌላዊ ልኡክነት ቅናት ተነሳስቶ ወደ ስሪ ላንካ በመምጣት ፍቅር በመመስከር በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረው ስደትና መከራ ምክንያትም የእኛ ቢጤ ተመስሎ በስውር አማኞች ጋር በተለይ ደግሞ ጸሓይ መጥልቀ በኋላ በመገናኘት ክህነታዊ አገልግሎቱ በመኖር ለተከበቡት በስቃይ ለሚገኙት ካቶሊካውያን ምእመናን መንፍሳዊና ግብረ ገባዊ ጽናት ምክንያት ሆነዋል። በክልሉ የወረርሽኝ በሽታ በታየበት ወቅትም ህሙማንን በማገልገል በሰጠው አብነት በአገሪቱ ንጉሥ እንዲደነቅ አደረገው፣ የሚፈጽመው አገልግሎት በሙሉ ነጻነት ያካሂድም ዘንድ አበቃው፣ በአገሪቱ በተለያየ ክልል በማገልገልም በ 59 ዓመተ እድሜው በሰማያዊ ቤት ተወለደ። የተቀደሰው ሕይወቱም በሁሉም ዘንድ ተከባሪ ሆነ።
እግዚአብሔርንና ባለ እንጀራን በቃልና በሕይወት በተካነ አገልግሎት የመሰከረው አብነታዊ ክህነት፣ ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ክልል በመወጣት ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉም ሊታወቅና ሊፈቀር ለማድረግ ያነቃቃናል፣ ስለ ወንጌል መሰቃየትና መሰደድ ቢኖርም ታጋሽነትን ያስተምረናል፣ ለእግዚአብሔርና ለቤተ ክርስቲያኑ ካለው ፍቅር ታዛዥነትን መረጠ፣ የተአዝዞ አብነት ሆኖም በዚህ ክልል ካቶሊክ ምእመናን ውሁዳን ብቻ ሳይሆኑ በውስጣቸውም መከፋፈል የነበራቸው መቃቃርና መለያየት፣ በክልሉ ለስደት የተጋለጡትን ለመምራት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ በጥልቅ ጸሎት ተካፋይ በመሆን ለሕዝቡ ተጨባጭ የፍቅር የምኅረት በጌታ ለመታረቅ ሕያው ምስል ሆነ።
ለሰላም አገልግሎት ዓላማ የሚታየው የሃይማኖት ልዩነት ሁሉ መቅረፍ ያለው አስፈላጊነት መሰከረ፣ ያ ለሌሎች ክፍት እንዲሆን ያደረገው ለእግዚአብሔርና ለባለ እንጀራ የነበረው ያልተፈራረቀ ምሉእ ፍቅር ምክንያትም ለተናቁት ለሚሰቃዩት መላ ሕይወቱን ሰዋ። አብነቱም በዛሬይቱ ስሪ ላንካና በዚህች አገር በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ኅብረተሰብ ዘንድም ሕያው ነው።
የሃይማኖት ነጻነት የመላ ሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት ነው። በቃልና በሕይወት ክርስቶስን በሙላት መኖር ውስጣዊ ነጻነት እንደሚያጎናጽፍና ይኽ ደግሞ ለውጫዊ ነጻነት መሠረት መሆኑ ያንን ወደ መነጣጠልና መለያየት የማይመራው እውነተኛው ስግደትና አምልኮ ለእግዚአብሔር በመኖር ቂም በቀል የጥላቻ መንፈስ ሁሉ እንዲወገድ የሌላው ክብርና መብት በማክበር መሠረት መሆኑ መሰከረ።
ቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ ለወንጌላዊ ልኡክነት ቀናተኛነቱ ለወንጌላዊ ልኡክነት አብነት ነው። ቤቱንና አገሩን በአገሩ የነበረው የተመቻቸው ሕይወትን ትቶ በወንጌላዊ ፍቅር ተነቃቅቶ ስለ ክርስቶስ ለመናገር እሺ በማለት ስሪ ላንካ በመግባት በዚህች ኅብረ ባህል ኅብረ ሃይማኖት በተካነቸው አገር የወንጌል እውነትና ውበት መሰከረ፣ ይኽ ደግሞ እያንዳንዱ ወንጌላዊ ልኡክ ሊከተለው የሚገባው መንገድ ነው። ወደ ጥጋ ጥግ የዓለማችንና የአገሮቻችን የህልውና ክፍል እንድንል ያነቃቃናል።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፦ የቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ አብነት እንከተል ዘንድ እማጠናለሁ፣ የዚህች አገር ማኅበረ ክርስቲያን እንደ ቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ በእምነት ጸንቶ ለሰላም ለፍትህ ለእርቅ ያገልግል። ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ ይኸንን ነው የምትጠይቃችሁ፣ ከዚያች በሁሉም ዓለም ከምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ጋር በውኅደት የጌታችን አዲስ ዜማ እንድናዜምና ክብሩን እስከ ዓለም ዳርጃ እናበስሥር ዘንድ ለቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ ጸሎት አወክፋችዋለሁ፣ ጌታ አቢይና የሁሉም ምስጋናና ክብር የተገባው ነው አሜን።








All the contents on this site are copyrighted ©.