2015-01-14 15:32:55

የቅዱስ አባታችን የስሪ ላንካ ሐዋራያዊ ጉብኝት የሰላምና የእርቅ ምልክት ነው


RealAudioMP3 በስሪ ላንካ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ፒየር ንጉየን ቫን ቶት ከቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሲልቮነይ ፕሮትዝ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት በስሪ ላንካ የተስፋ ምልክት ነው። በማለት ገልጠው፣ የአገሪቱ ሕዝብ ለቅዱስነታቸው ያለው ፍቅር አቢይና ጥልቅ መሆኑ መስክረዋል፣ ምክንያቱ ሰላምና እርቅ ይቅር መባባልና ምኅረት የሚያነቃቁ ብቻ ሳይሆን የዚህ አቢይ ክብር አብነት ናቸው ብለው ስለ ሚያምን ነው። ስለዚህ ለሰላሳ ዓመት የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የደማው ሕዝብ የሰላምና የእርቅ ጥማቱ ለይተው ለማርካት የሚያግዘው መንገድ የሚያመልክቱ መሆናቸው ሕዝቡ እምነቱ እንዳለውም በቃልና በተግባር በተደረገላቸው አቀባበል ተመስክረዋል።
ቅዱስ አባታችን ከአገሪቱ ከተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ከቡድሃ ከሂንዱ ከምስልምናና ከአቢያተ ክርስቲያን መንፈሳዊ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ያስደመጡት ንግግር በሁሉም ልብ ታትሞ የሚቀር መሆኑ አያጠራጥርም ብለው፣ ቅዱስ አባታችን የቡድሃ ገዳም እንዲጎበኙ የቡድሃ ሃይማኖት መሪ አንዳደሙዋቸውና፣ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች ተመሳሳይ ጥሪ እያቀረቡላቸውም ነው። ይኽ ደግሞ በእውነቱ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ለቅዱስነታቸው የሚሰጡት ክብር ምንኛ የላቀ መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.