2015-01-14 15:38:38

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉብኝት የተስፋ ምልክት ነው


RealAudioMP3 በስሪ ላንካ ወንጌላዊ ልኡክ የጸላይቱ ንጽህት ድንግል ማርያም ወንጌላዊ ልኡካን ማኅበር አባል የአገሪቱ ተወላጅ አባ ሻኒል በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በስሪ ላንካ የቡድሃ ሃይማኖት የአብላጫው ሕዝብ ሃይማኖት ነው። የሂንዱ የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና እንዲሁ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ተከታዮችና የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚኖርባት አገር ነች፣ ከሁሉም ጋር አለ ምንም ችግር በጋራ የሚኖሩና ከሁሉም ሃይማኖቶች ጋር መልካም ግኑኝነት እንዳለም ገልጠዋል።
በአገሪቱ የጎሳም ሆነ የሃይማኖት ችግር የለብንም አገሪቱን ለረዥም ዓመታት ያደማው ውጥረትና የእርስ በእርሱ ጦርነት በመንግሥትና ገዛ እራሱን ታይገር በማለት በሚጠራው ተቃዋሚ ታጣቂ ኃይል መካከል ነው። የጦርነቱ መንስኤ በታሚል ይፈጸም የነበረው ኢፍትሃዊነት እንዲገታ የታሚል ሕዝብ አመጽ ያነሳሳበት ሁነት የሚገልጥ ጦርነት እንጂ በታሚልና በቺንጋለዚ ጎሳ መካከል ያለ ውጥረት አይደለም። በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ምንም ዓይነት ውጥረት የለም፣ ጉዳዩ እንዲህ ሆኖ እያለ የዓለም አቀፍ ማኅበረብ ይኸንን የተረዳው አይመስልም፣ በታሚልና በቺንጋለዚ መካከል የተቀሰቀው የእርስ በእርስ አለ መተማመንና የጠላትነት መንፈስ የወለደው በመንግሥትና በታይገር ተዋጊ ሃይሎች መካከል የተቀጣጠለው ጦርነት ነው። በአሁኑ ወቅት መረጋጋት እየታየ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሰሜናዊው የስሪ ላንካ ክልል የሚገኘውን ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ይጎበኛሉ፣ ይኽ ቅዱስ ሥፍራ የሚገኝበት የማድሁ ክልል በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት እጅግ የተነካው ክልል የሚገን ነው፣ በዚያ ቅዱስ ሥፍራ ታሚሎችም ሆነ ቺንጋለዞች ጭምር አለ ምንም ልዩነት መንፈሳዊ ንግደት የሚፈጽሙበት ቅዱስ ሥፍራ በመሆኑ ቅዱስነታቸው ከመላ የስሪ ላንካ ሕዝብ ጋር በመሆን በዚያ ለመጸለይ ያላቸው መርሃ ግብር እርቅና ሰላም የሚያነቃቃ ተስፋ የሚመስከር ንግደት ነው። ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት እርቅና ሰላም የሚዘራ እንደሚሆን ያላቸው እምነት ገልጠዋልው በታሚልና በቺንጋለዚ ካቶሊካውያን መካከል የነበረው ልዩነት እንዲቀረፍና ፈጽሞ እንዳይኖር የቅዱስ ዮሴፍ ቫዝ ሕይወት አብነት ነው። ቅዱስ ዮሴፍ በሁለቱ ጎሳዎች ክፍል የሆኑት ካቶሊካውያን ማኅበረሰብ መካከል የሚከበር ነው፣ ታሚሎችም ሆኑ ቺንጋለዞች ማኅበረ ክርስቲያን የስሪ ላንካ ሐዋርያ በሚል መጠሪያም ነው የሚገልጡት፣ የሴፍ ቫዝ ቅዱስ ብላ ቤተ ክርስቲያን ታውጅለትም ዘንድ የክልሉ ሕዝብ ለ 300 ዓመታት በጉጉት ይጠባበቀው የነበረ ተስፋ ነው። ስለዚህ ለመላ ስሪ ላንካ ዓቢይ ወቅት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.