2015-01-14 15:30:06

የስሪ ላንካ ሕዝብ ለቅዱስ አባታችን ያሳየው የሞቀ አቀባበል


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ስሪ ላንካ እንገቡ ለእንኳን ደህና መጡ የአገሪቱ ሕዝብና መንግሥት ያሳየው ባህላዊ የአቀባበል ያቀረበው ትርኢት የሚያስደንቅ የአገሪቱ ባህል ያለው ውበት በጥልቀት የሚያጎላ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን የሰላም ቅብአ ለመሆን በአገሪቱ እንደሚገኙ አገሪቱን ለረዥም 30 ዓመታት ያደማው የእርስ በእርስ ግጭት በእርቅ ይገሰጽም ዘንድ ለማነቃቃት በአገሪቱ እንደሚገኙ ሲነገር፣ ይኽ ግጭትና ጦርነት ጥሎት ያለፈው ጠባሳ እርሱም በታሚልና ቺንጋለዚ እንዲሁ በአገሪቱ በሚገኙት በጠቅላላ ጎሳዎች መካከል አለ መተማመን በአይነ ቁራኛ ለመተያየት አደጋ ያጋለጠው መጠራጠር ያኖረ ቢሆንም ቅዱስ አባታችን ክፋት በመልካምነት ብቻ በሙላት ሊሸነፍ የሚቻል መሆኑና ይኽ ደግሞ ለፍትህ ለውህደትና ለእርቅ ማእከላዊ ቦታ መስጠት በሚያውቅ ሠናይ ተግባር አማካኝነት ለመቅረፍ ታቻይ መሆኑ ባካሄዱትና እያካሄዱት ባለው ግኑኝንት እያሰመሩበት ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችንን ለመቀበል የተፈጸመው የእንኳን ደኃና መጡ አቀባበል ሥነ ሥርዓት የሚያስደንቅ ስሪ ላንካ ያላት የባህል ውበት የሚመስከር ነው። ጉንጉን አበባ በአንገታቸው ባንጠለጠሉ በተለያዩ በሚያሸበርቁ ቀለማት በተነቀውሱ ከአርባ በላይ በሚገመቱት ዝሆኖች የተሸኘ ሥነ ሥርዓት እንደነበር የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፣ ቅዱስ አባታችን ስሪ ላንካ ርእሰ ከተማ ኮሎምቦ ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ እንደደረሱ የተሳፈሩበት አይሮ ፕላን በመዘግየቱ ምክንያት እንደ ደረሱ ከተደረገላቸው የሞቀ ያቀባበል ሥነ ሥርዓት በኋላ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ከተገናኙዋቸው ከአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ጋር ለመግናኘት የነበራቸው መርሃ ግብር መዛወሩና በአገሪቱ ከሚገኙት ከቡድሃ ከሂንዱ ከምስልምናና ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በመገናኘት የአንደኛው ቀን የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው መርሃ ግብር እንዳጠናቀቁ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.