2015-01-14 17:49:15

ሐዋርያዊ ዑደት ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በስሪላንካና ፍሊፒን ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በኤስያ ክፍለ ዓለም በየቀድሞ ሳይሎን የአሁንዋ ሲሪላንካ
ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ ። ቅድስነታቸው በስሪላንካ እያካሄዱት ያሉት እና ቀጥሎም በፊሊፒን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሰባተኛ ሀገራት ሐቆፍ ጉብኝት መሆኑ ነው ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሁለቱ የኤስያ ክፍለ ዓለም ሀገራት የሚያካሄዱት ዑደት ሐዋርያዊ ጉብኝት የሰላም እና የውይይት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አጽንኦት ሰጥቶ አስገንዝበዋል። ቅድስነታቸው ስሪላንካ እንደገቡ የርእሰ ከተማ ኮሎምቦ እና የአካባቢው ህዝብ ላደረገላው እጂግ ደማቅ አቀባበል ከልብ ማመስገናቸውከቦታው የደረሱን ዜና ያመለክታሉቅድስነታቸው የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ዋንኛ ዓላማ ሀገሪቱ ውስጥ በአጠቃላይ ክርስትያን በተለይ ካቶሊካውያን ለማበረታታት እና ከነሱ ጋር በጋራ ስለ ሰላም ለመጸለይ እና ከሀያ ዓመታት በፊት አክሊለ ለብፅዕና የበቃ ለብጹዕ ጁሰፐ ቫዝ ሥርዓተ ቅድስና ለመፈጸም እንደሆነ አስታውቀዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ርእሰ ከተማ እንደገቡ በሶውስት መቶ ሺ የሚገመት ህዝብ በመንገድ ዳር በመገኘት የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ መግለጡ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገልጠዋል። ስሪላንካ ላይ ካቶሊካዊ እምነት የሚከተል ማሕበረ ሰብ ውሁድ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እና ትናትና ወደ የስሪላንካ ቤተ መንግስት በመጓዝ ለሀገሪቱ መሪ የክብር ጉብኝት አድረገው ከፕረሲዳንቱ ጋር በግል መወያየታቸው ተዘግበዋል ።
በርእሰ ከተማ ኮሎምቦ በሚገኘው ቤተ ሊቀ ጳጳሳት አጭር ዕረፍት ካደረጉ በኃላ ወደ ሃገራት አቀፍ ማእከል አዳራሽ ተጉዘው ከሀገሪቱ የተለያዩ የሃይምኖት አባቶች ጋር የተገናኙ ሲሆን
ሃይማኖት የሰላም የመቀራረብ እና የመወያየት መሳርያ እንጂ ሃይምኖትን አስታኮ የሚደረገው ህውከት እና ግጭት እንዲወገዝ ለሃይማኖቶች አባቶች አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል። ይህ አጠር ባለ መልኩ የትናትና ውሎዋቸው ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ኮሎምቦ ላይ ከሚገኘው ካረፉበት ቤተ ሊቀ ጳጳሳት Galle face Green ተብሎ ወደ ሚጠራው ትልቅ የህዝብ መናፈሻ መጓዛቸው እና የኮሎምቦ ከተማ ከንቲባ እና በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገላቸውም ተገልጸዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ 500 ሺ ህዝብ በተገኘበት የተለያዩ የኤስያ ሀገራት ብፁዓን ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ታጀበው ለቡዕ ጁሰፐ ቫዝ ሥርዓተ ቅድስና ፈጽመውለታል። ከሃያ ዓመታ በፊት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዚሁ የህዝብ መናፈሻ ዛሬ ቅዱስ ለተሰየመው ሥርዓተ ብጽዕና ፈጽመውለት ነበር ።ዛሬ አክሊለ ቅድስና የተቀበለ ቅዱስ ማን ነው ! ቅዱስ ጁሰፐ ቫዝ በጎርጎርዮስ የቀን መቁጠርያ በ1651 እና 1711 መካከል ይኖር የነበረ በጎአ ህንድ የተወለደ የፖርቱጋል ዜጋ ነበር ። ቅዱስ ጁሰፐ ቫዝ የስሪላንካ የመጀመርያ ቅዱስ ነው ።
በዚያን ወቅት ሳይሎን የዛሬ ሲሪላንካ የሆላንድ ቅኝ ግዛት መኖርዋ እና ቅዱሱ በ1686 በጎርጎርዮስ ዘመን አቁጣጠር ካህን የቅዱስ ፍሊፖ ኔሪ ማህበር አባል በድብቅ ሳይሎን ገብቶ በድብቅ ካቶሊካዊ እምነት የሚከተሉ ሰዎች አፈላልጎ እና አደራጅቶ እምነቱ ስር እንዲሰድ ያደረገ ለዶች ያደረገ ትሁት እና ታታሪ ካህን መኖሩ የሕይወቱ ታሪክ ይመሰክረለታል። ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፋራንሲስ በዚሁ የህዝብ መናፈሻ ሥርዓተ ቅድሴ አሳርገዋል። ከፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ ቅድስና በኃላ ቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተመልሰዋል ። ከምሳ እና አጭር ዕረፍት በኃላ ከርእሰ ከተማ ኮሎምቦ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክልል 250 ኪሎሜትር ርቃ ወደምትገኘው ከተማ madhu ተጉዘዋል። በዚች ማዱ በተባለች ከተማ ጥንታዊ የማዱ ገዳመ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሚገኝ ይታወቃል ።
የማዱ ቅድስነታቸው ገዳመ ቅድስት ድንግልማርያም ማዱ እንደደረሱ የማናር ሀገር ሰብከት ውሉደ ክህነት እና በብዙ ሺ የሚገመት ህዝብ ሺ የሚገመት ህዝብ ደማቅ አቀባበል እድርጎውላቸዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በየማዱ ገዳመ ቅድስት ድንግልማርያም ለተገኘ በመቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ንግግር አድርገዋል። የተወዳችሁ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ እነሆ በእናታችን ቤት እንገኛለን እሷ እንኳን ወደ ቤተ ደሃና ም አጣችሁ ተለናለች በዚህ የማዱ ገዳም ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ተሳላሚ ሁሉ እንደ ቤቱ ይሰማዋል ብለው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ፍራንሲስ ምክንያቱም እዚህ የልጅዋ የጌታችን መድኀኒታችን ህልውና ትነግረናለች ከሱ ጋርም ዳግም እንድናውቀው ታደረገናልች ብለዋል።
እዚህ ገዳም ውስጥ የስሪላንካ ማህበረ ሰቦች እንደ አንድ ቤተ ሰብ የሚቀርቡብበት ቅዱስ መካን ሆኖ ደስታቸው እና ሐዘናቸው የሚገልጡበት መካን መሆኑም አስገንዝበዋል። ስሪላንካ ውስጥ በሰሜናዊ እና ደቡባዊ የሀገሪቱ ክልሎች አስከፊ የርስ በርስ ጦርነት በተካሄደበት ግዜ ከባድ ስቃይ ያሳለፉ ቤተ ሰቦች እዚህ ከኛ ጋ ይገኛሉ ቅድስት ድንግል ማርያም ስቃያቸው ትቀበልላቸዋለች ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳቱ ።የተወደዳችሁ ውንድሞቼ እና እኅቶቼ እዚህ በመካነ ማዱ ገዳመ ቅድስት ድንግል ማርያም ከናንተ ጋር መገኘቶቴ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል በማከል። እሷ ማለት ቅድስት ድንግል ማርያም ሰላም ትስጠን ሰላምዋ ታውርድልን ዘንድ እንለምናት ካሉ በኃላ በገዳሙ ከተገኘ ህዝብ ጋ አብረው ማርያማዊ ጸሎት ደግመው እና ተሰናብተዋል። ከየማዱ ገዳመ ማርያም ወደ ርእሰ ከተማ ኮሎምቦ ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተመልሰው ከሸኝዋቸው ብጹዓን ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት እንዲሁም ከየከተማይቱ ሊቀ ጳጳሳት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ውሉደ ክህነት ጋር ለእራተ ስርዓት ቀርበው በዚህም የዛሬ ውሎአቸው ፍጻሜ ሁነዋል። ነገ በፍሊፒን ተመሳሳይ ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ወደ ዋና ከተማ ማኒላ ይበራሉ ።









All the contents on this site are copyrighted ©.