2015-01-12 15:31:39

የአንቀጸ እምነት የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበርና የኤውሮጳ የአንቀጸ እምነት ድርገት ግኑኝነት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከጥር 13 ቀን እስነ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በአንቀጸ እምነት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅይነተ ብፁዕ ካርዲናል ሚዩለር የሚሸኝ የዚሁ ቅዱስ ማኅበር የበላይ አካላት ከኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የአንቀጸ እምነት ጉዳይ የሚከታተሉት ድርገት ሊቀ መናብርት በሃንጋሪ ኤስተርጎም ከተማ እንደሚገናኙ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የአንቀጸ እምነት የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር እ.ኤ.አ. የካቲት 23 ቀን 1967 ዓ.ም. ያቆሙት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ በኤውሮጳ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጭምር የአንቀጸ እምነት የሚከታተሉ ድርገቶች እንዲቋቋሙ ማድረጋቸውም ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ይኽ ድርገት ለብፁዓን ጳጳሳት ምክር በቤቶችና ለብፁዓን ጳጳሳት በአንቀጸ እምነት ጉዳይ የሚደገፍና ብሎም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት እቃቤ የሚያንጽ መሆኑ ገልጦ፣ ከዚህ ባሻገርም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ኵላዊነት ገጽታውን የሚከታተል ብሎም ኵላዊነቱን የሚያረጋግጥ መሆኑ ያመለክታል።
የቅድስት መንበር የአንቀጸ እምነት ተከታትይ ቅዱስ ማኅበርና የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት የአቀንጸ እምነት ተከታታይ ድርገቶች እ.ኤ.አ. ከ 1982 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃም ጭምር ተከታታይ ይፋዊ ዓውደ ጉባኤ ማካሄድ ጀምረው፣ እ.ኢ.አ. በ 1984 በላቲን አመሪካ በቦጎታ፣ ቀጥሎም በ1987 ዓ.ም. በአፍሪቃ በኪንሻሳ፣ እ.ኤ.አ. በ 1989 ዓ.ም.በኤውሮጳ ቪየና ከተማ፣ እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. በእስያ በሆንግ ኮንግ ከተማ፣ በ 1997 ዓ.ም. ዳግም በላቲን አመሪካ በጉዋዳላኻራ ከተማ፣ በ 1999 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በሳን ፍራንቸሲስኮ በ 2009 ዓ.ም. በአፍሪካ ዳር ኤስ ሳላም ከተማ መካሄዱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውሶ፣ የወቅቱ የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበር የሃንጋሪ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ የአንቀጸ እምነት ተከታታይ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሚዩለር የ2015 ዓ.ም. ዓውደ ጉባኤው በአገረ ሃንጋሪ እንዲካሄድ ያቀረቡት ጥሪ ተቀብለው ሃንጋሪ የጉባኤው አስተናጋጅ አገር እንድትሆን ማረጋቸው በሃንጋሪ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ጸጋ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ መግለጣቸው ያመለክታል።
ይኽ የሚካሄደው ጉባኤ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ እምነት ትምህርት እቃቤና የሚያካሂዳቸው ጉባኤዎችም በኤውሮጳና በተለያየ ክፍለ ዓለም የሚታየው ወቅታዊ ተጋርጦ ግምት የሚሰጥ መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.