2015-01-12 15:28:44

ኾርገ ሚሊያ፦ እስያ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልብ ነች


RealAudioMP3 የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅርብ ጓደኛ አርጀንቲናዊ ጋዜጠኛና ደራሲ ኾርገ ሚሊያ ቅዱስ አባታችን የዛሬ ስድስት ወር በፊት በደቡብ ኮርያ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ይኸው እ.ኤ.አ. ከጥር 12 እስከ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በስሪ ላንካና ፊሊፒንስ በሚያካሂዱት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት አማካኝነት ለሁልተኛ ጊዜ ወደ እስያ ክልል ማቅናታቸው እስያ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልብ መሆንዋ የሚመሰክር ነው። ቅዱስ አባታችን ገና ካህን እያሉ በማኅበራቸው ወደ እስያ ወንጌላዊ ልኡክ ሆነው እንዲላኵ ያቀርቡት የነበረ ጥያቄ የሚያረጋግጠው እውነት መሆኑ ገልጠው፣ ባለፈው ዓመት በእስያ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉት ቁጥር ብዛት በኤውሮጳ ከተቀበሉት እጅግ ከፍ ያለ ነው፣ በእስያ የካቶሊክ ምእመን ብዛት በቁጥር እድገት እያሳየም ነው። በዚያ ክልል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ሰብአዊ መንፍሳዊ ሕንጸት በግብረ ሠናይና በሕንጸት ዘርፍ አመርቂና በክልሉ ሕዝብና መንግሥታት እጅግ የሚመሰገንም ነው። የዓለማውያን ምእመናን ሱታፌ በዚህ በሕንጸት ዘርፍ ብሎም በአስፍሆተ ወንጌል የሚሰጠው አስተዋጽዖ የተዋጣለት ነው ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ወደ እስያ ያቀናው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ቻይናን የሚያስብ ነው። ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. የተገባው 2015 ዓ.ም. እጅግ እንዲህ ባለ በከፍተኛና አድካሚ በሆነው ሐዋርያዊ መርሃ ግብር አማካኝነት ጀምረዉታል፣ እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በእስያ በሚያካሂዱት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸ ከ 180 በእስያ ከሚገኙት የተለያዩ መንግሥታት ልኡካን ጋር ይገናኛሉ፣ ለልኡካኑ ንግግር ያስደምጣሉ ብለው፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ በቻይና መንግሥት ውሳኔ መሠረት ጳጳስ እንዲሆኑ የተሸሙትን በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ ነው በማለት ሲያወግዙ ቻይና በበኵልዋም በአገሪቱ የነበረው ቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በማባረርዋና ይኸውም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በቅዱስ ጴጥሮስ ውሳኔ የሚመረጥና የሚሾም በመሆኑም ይኽ ጉዳይ በቻይና በመንግሥት ሥር የምትተዳደር ብሔራዊ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በመቋቋሟ ምክንያት ከ1951 ዓ.ም. ወዲህ የተቋረጠው የቻይናና የቅድስት መንበር ግኑኝነት መሆኑም ገልጠው፣ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ መቀመጫም ወደ ታይዋን መዛወሩንም አስታውሰው፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በእስያ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደት የቻይናና በቅድስት መንበር መካከል የተቋረጠው ግኑኝነት ቀስ በቀስ ዳግም እንዲጀመር የሚያነቃቃ እንደሚሆን ተስፈኛ ነኝ ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በደቡብ ኮሪያ ሐዋርያዊ ዑደት ለማካሄድ የሚጓዙባት አየር በቻይና የበረራ ድንበር ታልፍ ዘንድ ቅድስት መንበር ጥያቄ አቅርባ እንደነበርና ጥያቄውም በቻይና መንግሥት አወንታዊ ምላሽ እንደተሰጠው አስታውሰው፣ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1989 ዓ.ም. ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው አሉታዊ ምላሽ እንደተሰጣቸው የሚታወስ ነው። ስለዚህ ይኸንን ሁኔታ ሁሉ በማጤንም በቅድስት መንበርና በቻይና መካከል ሙሉ በሙሉ ሳይሆን የተቋረጠው ግኑኝነት ለማስጀመር የሚያግዝ አወንታዊ ምልክት በአሁኑ ወቅት አየታየ ነው ብለው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሰላም በዓለም እንዲረጋገጥ ለዚህ ዓላማ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸው በማኖር ስለ እኔ ጸልዩ አደራ የሚሉ ሕዝቦችን ለማቀራረብ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ናቸው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.