2015-01-12 15:23:25

ቫቲካን፦ ሃይቲ ድኅረ አምስተኛው ዓመት ክስተት ርእደ መሬት


RealAudioMP3 በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልዩ ፍላጎትና ውሳኔ መሠረት ሃይቲ ድኅረ አምስተኛው ዓመት ክስተት ርእደ መሬት ርእሥ ዙሪያ የቅዱስ አባታችን የቅርብ ተባባሪዎች የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ዓበይት አካላት የጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት የበላይ ተጠሪዎች የተለያዩ የመንፈሳዊና የገዳማት የደናግል ማኅበራት የበላይ አለቆች የተለያዩ ዓለም አቀፍና ብሔራው ዓቀፍ የግብረ ሠናይ ማኅበራት ተጠሪዎች በማሳተፍ የመከረው ዓውደ ጉባኤ መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያት ገለጡ።
የዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሃይቲን በእጅግ ያጥቃው ርእደ መሬት 300 ሺሕ ለሞት ስምንት ሚሊዮን ደግሞ ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ለዚህ አደጋ የተጋለጠቸውን ሃይቲንና ሕዝብዋን ለመደገፍ ለዳግመ ግንባታ የተከናወነውና እየተከናወነ ያለው የግብረ ሠናይ ድጋፍ የገመገመ ዓውደ ጉባኤ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የላቲን አመሪክ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኡለት፦ ዓውደ ጉባኤ እይታው ተስፋ ላይ በማኖር የሃይቲን ሕዝብ ርእደ መሬት ባስከተለው አቢይ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ምክንያት ተስፋውን ሳያጨልም የተያያዘው ሰባአዊ ክብርና በእምነት ጸንቶ እያከናወነው ያለው የዳግመ ግንባታ ሂደት ለማበርታታትና የመላ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ድጋፍ በማረጋግጥ እስካሁን ድረስ የተካናወነው ድጋፍ ጭምር የገመገመ መሆኑ ሲያብራሩ፣ በሃይቲ ርእሰ ከተማ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ማከሚያ ቤት ዳግመ ግንባታው ተጠናቆ፣ ይኸው በዚህ እ.ኤ.አ. ጥር ወር 2015 ዓ.ም. ውስጥ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊና መንፈሳዊ ብሎም ሥነ ልቦናዊ ሕንጸት ጭምር እየተከናወነ መሆኑ የውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የሥርዓተ አምልኮና የቅዱሳት ሚሥጢራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ህየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራሕ በበኩላቸው ገልጠው፣ አለ ሰብአዊ ሕንጸት ቁሳዊ ሕንጸት ለብቻው ምሉእ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህ የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ይኸንን መሠረት በማድረግ በሰብአዊ ዳግመ ሕንጸት አማካኝነት ቁሳዊው ሕንጸት በማከናወን የአገሪቱ ተስፋ ለማነቃቃት ቤተ ክርስቲያን እያካሄደቸው ያለው ትብብር የገመገመና የተለያዩ የግብረ ሠናይ ማኅበራት በሃይቲ የሚያካሂዱት የዳግመ ሕንጸት ግንባታት ጭምር ምን ተመስሎው ያጤና ጉባኤ መሆኑ ገልጠዋል።
በመጨረሻም በሃይቲ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልኡካንን የመሩት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጂብልይ ላንግሎይስ እንዳመለከቱትም ሃይቲ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች አገር ብትሆንም የአገሪቱ ሃብት ከአገልግሎት ለሕዝብ ጉዳይ እሩቅ በመሆኑ የሕዝቡ መሠረታዊ ፍላጎት ከማርካት የራቀ ነው። አገሪቱ ያላት የወጣት ትውድ ኃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የውጭ ጎብኝ መስኅቦ ለኤኮኖሚው እድገት ወሳኝ መሆኑ ገልጠው፣ ለዳግመ ግንባታ ብዙ ተከናውነዋል ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ለተናቁትና በከፋ ድኽነት ሥር ለሚኖሩት ያላት ቅርበትና ድጋፍ መቼም ቢሆን የማያቋርጥ መሆኑ የመሰከረ ዓውደ ጉባኤ ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.