2015-01-09 14:30:11

ቅዱስ አባታችን በቀጣይነት ለሚሰጡት መንፈሳዊና ሰብአዊ ድጋፍ ከያዚዲ ማኅበረሰብ ምስጋና


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢራቅ ኩርድስታን የሚኖሩት የያዚዲ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የበላይ መሪ ታሂሽ ሳይድ አሊ በግና የዚህ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ሸይክ ካቶ የተመመሩት በኢራቅ የሰሜን ክልል ለሚገኘው ለያዚዲ ማኅበረሰብ ወኪል፣ በጆርጂያና በጀርመን የሚገኙት የያዚዲ ስደተኞች ማኅበረሰብ ወኪል በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ መጻሕፍት የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ሲያመልክቱ፣ በጠቅላላ በዓለማችን የያዚዲ ማኅበርሰብ ብዛት አንድ ሚሊዮን ከግማሽ ሲሆን ግማሽ ሚሊዮን በኢራቅ፣ የተቀሩትም በጆርጂያ በቱርክ በአርመኒያናና ሌሎችም በተለያዩ አገሮች በስደት የሚኖሩ መሆናቸው አስታውቀዋል፣
የያዚዲ ማኅበረሰብ ከክርስቲያን ማኅበረሰብ ጋር በኢራቅ የሚኖሩ ውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ በኢራቅ የእስላማዊ አገር ጅሃዳውያን ታጣቂ ኃይሎች አማካኝነት ለስቃይና ለስደት የሚዳረጉና በሚደርስባቸው አመጽና ቅትለት ምክንያት ከሚኖሩበት ከነነዌ ክልል መፈናቀላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ሎምባርዲ በሰጡት መግለጫ አስታውሰው፣ ልኡካኑ በተካሄደው ግኑኝነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዚህ ማኅበረሰብ ካለ መታከት የሚሰጡት ዘወትር መንፈሳዊና ሰብአዊ ድጋፍ ምክንያት ማመስገን ቅዱስነታቸው ለዚህ ለስደት ለመከራና ለሞት አደጋ ለተጋለጠው ለያዚዲ ኅብረሰብ የሚሰጡት ድጋፍ ያላቸው ቀጣይ ቅርበት የሚያረጋግጥ መሆኑ የገለጡት ልኡካን ቅዱስ አባታችንን የድኾች አባት በማለት እንደገለጡዋቸው አስታውቀዋል።
የያዚዲ ልኡካን በኢራቅ እስላማዊ አገር ጅሃዳውያን ታጣቂ ኃይሎች በሚቆጣጠሩት የኢራቅ ክልል አምስት ሺህ የዚህ ማኅበርሰብ አባላት ሴቶች ለባርነት አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙና በኢራቅ በሚገኙት ንኡሳን የኅብርሰብ ክፍል አባላት እርሱም በያዚዲና በማኅብረ ክርስቲያን መካከል ያለው የእርስ በእርስ መደጋገፍ መልካም የተዋጣለት መሆኑ ለቅዱስ አባታችን ከገለጡ በኋላ፣ ቅዱስነታቸው በበኩላቸውም ለልኡካኑ ለሚሰቃየው ኅብረሰብ ያላቸው መንፍሳዊ ቅርበት በማረጋገጥ በተለይ ደግሞ በዚህ ለተለያየ አደጋ በተጋለጡበት በአሁኑ ወቅት በበለጠ ቅርብ መሆናቸውና ፍትህ አማካኝነት በነጻነትና በሰላም ለመኖር የሚያበቃቸው ሁነት እንዲረጋገጥላቸው ተመኝተው ሁሉም ለሚስቃየው ውሁዳን ኅብረተሰብ ቅርብ ይሆንም ዘንድ ጥሪ ማስተላለፋቸው አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.