2015-01-09 14:34:11

ቅ.አ..ር.ሊ.ጳ.፦ እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚያበቃ መንገድ ፍቅር ነው፣ የአዕምሮ ብቃት ለብቻው በቂ አይደለም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እ.ኤ.አ. የተገባው የ 2015 ዓ.ም. አዲስ ዓመት ጥር 8 ቀን የመጀመሪያው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው የዕለቱ ምንባብ አስደግፈው እግዚአብሔር ዘወትር በፍቅር የሚቀድመንና የሚመራን መሆኑ ገልጠው፣ ክርስቲያናዊ ፍቅር ቃል ብቻ ሳይሆን ግብረአዊም ነው፣ በግብር የማይኖር ክርስቲያናዊ ፍቅር ባዶ ነው፣ ፍቅር እግዚአብሔር ለማወቅ የሚያበቃ ልዩ መንገድ ነው፣ በመሆኑም እግዚአብሔር ለማወቅ የአዕምሮ ብቃት ለብቻው በቂ እንዳልሆነ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“በፍቅር መንገድ ብቻ ነው እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚቻለው፣ እርሱን የማወቅ መንገድ ፍቅር መኖርን ይጠይቃል፣ ኢየሱስ በልደቱ ተገለጠ፣ ሊሰግዱለት ለመጡት ሰብአዊ ሰገል ተገለጠ፣ በጥምቀቱም ተገለጠ፣ በቃና ዘገሊላ ተገለጠ። ገዛ እራሱን በመግለጥ እርሱን ለማወቅ የሚያበቃው መንገድ እርሱም ፍቅር መሆኑ በተግባር አሳየን፣ የዕለቱ አንደኛው ምንባብ አንደኛይቱ የዮሐንስ መልእክት እግዚአብሔርን ለማወቅ ያለን የአዕምሮ ብቃት ለብቻው በቂ አንዳልሆነ በመግለጥ እንዲሁም ጌታን በሙላት ለማወቅ ከእርሱ ጋር ግላዊ ግኝንነት ብቻ በቂ አይደለም፣ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በመሆኑም በፍቅር ጎዳና ብቻ ነው በሙላት ለማወቅ የሚቻለው፣ በአዕምሮ ብቃት የተሸኘ ፍቅር እግዚአብሔርን ለማወቅ ይመራናል። የማላውቀውን ሰው እንዴት ላፈቅረው እችላልሁ? የማታውቀው ማለትም እሩቅ ያለውን አፈቅራለሁ ሳይሆን፣ የሁለቱ አበይት ትእዛዞች መሠረታዊ ትምህርት፣ እግዚአብሔር አፍቅር፣ ባለንጀራህን (ጐረቤትህን) አፍቅር፣ የሚል ነው፣ ወደ የመጀመሪያው ትእዛዝ ለመድረስ በሁለተኛው ትእዛዝ ማለፍ ግድ ነው። እግዚአብሔር እንደማፈቅር የምመሰክረው ጎረቤቴን በማፍቅር ነው፣ በዚህ ዓይነቱ ምስክርነት የሚኖር ፍቅር በአዕምሮ ብቃት ቢደገፍ መልካም ነው። ፍቅርን በአዕምሮ ብቃት ብቻ ማብጠርጠሩ እግዚአብሔር ለማፍቀራችን ዋስትና አይሆንም፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ልበ ወለዳዊ ፍቅር አይደለም፣ እንዲህ አለ መሆኑም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ የሚለው ጌታ የሰጠን ትእዛዝ ያረጋግጠዋል፣ ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው፣ የሚያፈቅር ከእግዚአብሔር ነው፣ እግዚአብሔርን ለማወቅ ማፍቅር ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
“የሚያፈቅር እግዚአብሔርን ያውቃል የማያፈቅር እግዚአብሔርን አያውቅም፣ በቃልና በተግባር የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር እያከበርንበት ባለው በዚህ በአሁኑ የሊጡርጊያ ወቅት እግዚአብሔር ሊያድነን በላከው በአንድ ልጁ አማካኝነት የሚገልጠው ፍቅር እያከበርን መሆናችን ያረጋግጣልናል፣ ሁሉም አፍቅር የሚለው፣ ለሚወዱህ ለሚጠሉህ ሁሉ አፍቅር የሚል ፍቅር ነው። ከዚህ ውጭ እግዚአብሔር ለማወቅ የሚያበቃን ሌላ ፍቅር የለም” ብለው ፍቅር የሚሰጠው ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር እንጂ እኛ እንዳልሆን ሲያብራሩ፦ እኛን ስላፈቀረን እንድ ልጁን ለእኛ ቤዛ እንዲሆን ላከ፣ በማለት እግዚአብሔር በኢየሱስ አማካኝነት የገለጠው ፍጹም ፍቅር ላይ በማተኰር፦ “የእግዚአብሔር ፍቅር የምናስተነትነው በኢየሱስ መገለጥ የመሰከረው ፍቅር በቃልና በሕይወት በመኖር ነው። ነቢይ ኤርሚያስ እግዚአብሔር በፍቅሩ ይመራናል፣ እኛን እርሱን ገና ከመፈለጋችንን እርሱ ቀድሞ አፍቅሮናል፣ ልክ በጸደይ ወቅት ቀድሞ እንደ ሚታየው አበባ ነው። በመጀመሪያ ያፈቀረን እርሱ ነው። እግዚአብሔርን በምንኖረው ግብረ ሠናይ በጸሎትና በቃሉ ሱታፌ ፍቅሩን እንገልጣለን፣ በዚህ ሁነትም ቀድሞ ከሚጠባበቀን ፍቅር ጋር እንገናኛለን። ዘወትር ሳይታክት የሚጠባበቀን ፍቅር ነው። የዕለቱ ወንጌል ጌታን የዳቦና የአሳ የማብዛት ተአምር ያወሳል፣ ኢየሱስ ያንን አረኛ የሌለው የጠፉው ይከተለው የነበረው ብዙ ሕዝብ ሁነታ በማየት ተነካ፣ አዘነለትም፣ ከተሞቻችን አሁንም በዚህ ዓይነቱ ሕዝብ ብዛት የተሞሉ ናቸው፣ ለዚያ ሕዝብ ኢየሱስ ትምህርቱን ይለግሳል በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርት የሚበሉት እንዲሰጡዋቸው ይጠይቃቸዋል፣ የዘገዩ፣ አሁንም የእግዚአብሔር ፍቅር ይቀድማል፣ የደቀ መዛሙርት ፍቅር ግን የዘገየ ነበር፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ቃልና ተግባር ያካተተ ነው። እንዲህ ባለ ሁኔታ ዘወትር የጌታ ፍቅር እፊታችን ነው፣ ቀድሞ ያፈቀረን እርሱ ነው፣ ሊምረን ዘወትር ዝግጁ፣ እንድ ጊዜ ሳይሆህ 70 ጊዜ 7 ሊምረን ዝግጁ ነው፣ ዘወትር እንደ አንድ አባት ፍቅሩ ሙሉ ነው። ለጐረቤታችንን ለእኛ ቢጤ በምንኖረው ፍቅር አማካኝነት ለጌታ ያለን ፍቅር እንኖራለን፣ ለጌታ ያለን ፍቅርና ለባለ ንጀራችን ያለን ፍቅር የማይነጣጠሉ ፍቅር ናችው፣ በዚህ የጌታ መገለጠ በቤተ ክርስቲያን በምናከብርበት በአሁኑ ወቅት እርሱን በፍቅር መንገድ እናውቀው ዘንድ ጸጋው ይስጠን” በማለት ያስደመጡት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.