2015-01-09 17:10:02

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ በሲሪላንካና በፊሊፒን ስለሚያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፓሮሊን የሰጡት አስተያየት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ በሲሪላንካና በፊሊፒን ስለሚያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፓሮሊን የሰጡት አስተያየት
ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በቅርቡ ከፊታችን እ.ኢ.አቆ ጥር 7 ጀምሮ እስከ 14 ኢትዮጲያ አቆጣጠር በሲሪላንካና በፊሊፒን የሚያካሂዱት ሐዋሪያዊ ጉብኝት አስመልክቶ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፓሮሊን በኤሽያ አህጉር የቤተክርስቲያን አገልግሎት አስተዋጾ ኃይል በሁለት ነጥብ በመክፈል ኃሳባቸውን ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ነጥብ በኤሽያ አህጉር ቤተክርስቲያን በምታደርገው የሐዋሪያዊ ተልዕኮ አስተዋጾ የተለያዩ ት/ቤቶችንና የጤና ጥበቃ ማዕከሎች በመመሥረት እርዳታን ስትሰጥ ይህም አገልግሎትዋ በነዋሪው ሕዝብና በተለያዩ መንግስታት እውቅናና ምስጋናን ማስገኙቱን ነው። ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ለሰላም መሠረታዊ ድልድይ መሆኑን በመጥቀስ ባሁን ወቅት ከምን ግዜም በበለጠ ለሰላም ሁሉም ሃይማኖቶች ተግተው መስራት እንዳለባቸውና ከዚህም ቀደም ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በሐዋሪያዊ ትህምርታቸው (ግዋዲዩም ኤቫንጄሊ) የሃይማኖት ሕብረትና ውይይት ለሰላም አስፋላጊነቱን በመጥቀስ አስገንዝበዋል።
ባሁን ወቅት በሲሪላንካ በንዑሳን ሐይማኖቶች ላይ የተለያዩ ችግሮች ይታያሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያን የተለያዩ ሃይማኖቶችና ምዕመናን እናት እንደመሆንዋ መጠን የልጆችዋን ችግርና የልባቸውን መሻት ስለምታውቅ በቀላሉ ለሰላምና ለሕብረት መስራት እንደምትችል አመልክተዋል።
በሲሪላንካ ታሚሊ አወራጃ የሚገኘው የማዱህ ቤተመቅደስ በካቶሊኮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ሃይማኖት ተከታዮች የሚጠቀሙባት ቤተመቅደስ የምንማረው ቤተክርስቲያን የሰላም ድልድይና ሰላምን ለመገንባት ምሳሌ መሆንዋን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ገልፀዋል።









All the contents on this site are copyrighted ©.