2015-01-09 17:39:59

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ፓሪስ ላይ በግፍ ለተገደሉ ጋዜጠኞች ሥርዓተ ቅዳሴ ፈጽመዋል ፡


በፈረንሳ ፓሪስ ላይ የሚገኘ ምጸታዊ ምስሎችን በሚያወጣ ሻርሊ ኤብዶ የፈረንሳ ጋዜጣ ቢሮ ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ታጣቂዎች አስር የቢሮው አባላት እና ሁለት ፖሊሶች መግደላቸው ሌሎች ሶውስት ማቁሰላቸው ይታውቃል ።
ዚህ አስቃቂ ግድያ መንስኤ ሆነዋል ተብሎ የተነገረው ጋዜጣው ነቢይ መሐምድን የሚመለከት ምጸታዊ ምስሎች ማውጣቱ እና የእስላም አክራሪዎች ይህን ለመበቀል መሆኑ ነው ። የግድያ ተግባሩ ሲበዛ ያስቁጣቸው የምዕራቡ ዓለም መንግስታት የዲሞክራሲ መሰረት የሆነውን ሐሳብን በነፃ መግለጽ የሚጻረር አስከፊ እና አስቀያሚ እንደሆነ አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ ። የፓሪሱ ጥቃት በፈረንሳ ብቻ ሳይሆን በኤውሮጳ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነም ይናገራሉ ። የዓለም መሪዎች የሃይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የህብረተ ሰብ ክፍሎች ለፈረንሳ የሀዘን መግለጫ እያስተላለፉ እንደሆነም ተመልክተዋል።ፓሪስ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት እና ብሎም በፕረስ ነፃነት ላይ ያነጣጠረ እኩይ ተግባር መሆኑ በርካታ ይስማማሉ ። የፈረንሳ መንግት ፕረሲዳንት ፍራንስዋ ኦላንድ በተከሰተው ግድያ የተሰማቸውን ከፍተኛ ሐዘን ገልጠው መንግስታቸው አጸፋዊ ርምጃ እንደሚወስድ እና ወንጀለኞቹን እና ፈልጎ አግኝቶ ለፍርድ ለማቅረብ ሌት ተቀን እንደሚሰራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኤውሮጳ ሕብረት የፈረንሳ መንግስት ርምጃ ስሜታዊ እንድያሆን የኤውሮጳ ሕብረት ማመልከቱ ከከብሩሰል ተመልክተዋል ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት በየፓሪስ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሥርዓተ ቅዳሴ ፈጽመዋል።
ሥርዓተ ቅዳሴ ሲጀምሩ ፓሪስ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሰብአዊ ጨካን ተግባር የሚያሳስብ እና የሚያሳዝን እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በተናጠልም ሆነ መንግስታዊ የሽብር ተግባር መበራከቱ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነም ጠኡመዋል። በገፍ ለተገደሉ ሰዎች ሥርዓተ ቅዳሴ ከመፈጸማቸው በፊት አስከፊው ግድያ በአጽንኦት ኰንነው ፡ እግዚአብሔር በገፍ የተገደሉትን በመንግስተ ሰማያቱ እንዲቀበላቸው ለቤተ ሰቦቻቸው ጽናቱ እንዲሰጥ ተማጽነው የፈረንሳ ህዝብ እና መንግስት ሐዘን ተካፋይ መሆናቸው መግለጫ ሰጥተው ነበር። ይሁን እና በየፓሪሱ ግድያ የተጠረጠሩ ሁለት ውንድማማቾች መሆናቸውእና ትውልደ አልጀርያ እና የፈረንሳ ዜጎች መሆናቸው መልክተዋል። የፈረንሳ መንግስት ብሔራዊ ሐዘን አውጃለች ።








All the contents on this site are copyrighted ©.