2015-01-07 13:35:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የእግዚአብሔር ፍቅር በትህትና እንጂ በኃይለኝነት አልተገለጠም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በዓለ ግልጸት እርሱም ከምስራቅ ወደ ኢየሩሳሌም በከኮብ ተመርተው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ሊሰግዱለት የመጡት ነጋዲያን የኮዋክብት ተመራማሪዎች ንግደት የሚከበርበት ቀን ሲሆን፣ በዚህ ዓቢይ በዓለ ግልጸት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከውጭና ከውስጥ የመጡት በብዙ ሺህ የሚገመቱ ምእመናን የተሳተፉበት በካፐላ ሲስትና የመዘምራን ቡድን ታጅበው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በለገሱት ስብከት፦ “እግዚአብሔር መፈለግ ፍጻሜ የማያውቅ መሆኑ ሰብአ ሰገል ወደ እግዚአብሔር ምሥጢር ለመግባት የፈጸሙት ጉዞ ያመለክተናል፣ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ግርግም በተገኙት እረኞች አማካኝነት የተወከለው ለሕዝበ እስራኤል ብቻ ሳይሆን ለተወለደው ሕፃን ሊሰግዱ ከምስራቅ ወደ ኢየሩሳሌል በመጡት በሰብአ ሰገል አማካኝነት ለመላ ሰው ዘር መምጣቱን ተገልጦልናል፣ ሰብአ ሰገል በእምነትና በሃይማኖት እንዲሁም በመላ ዓለም ፍልስፍናዎች አማካኝነት እግዚአብሔር የምፈለጉን ሂደት ይወከላሉ። በኮከብ ምልክት ተመርተው ረዥም ተጉዘዋል፣ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው በጋራና በግል ከእውነተኛው እግዚአብሔር ጋር ተገናኝተዋል። ስንቴ ያንን በኮከብ የሚመለከተውን መንገድ ይሰወርብናል እንዘነጋለን፣ ኮከቡን ከማየት እንታቀባለን፣ በሄሮዶስ የማታለል ተግባር አማካኝነት የሚገለጠው የዲያብሎስ ፈተና ምክንያት ያንን እይታችን ከዚያ ወደ ጌታ ከሚመራን ኮከብ ይቆጠባል፣ ሄሮዶስ በተወለደው ሕፃን ይማርካል መማረኩ ሊሰግድለትና ሊያመልከው ሳይሆን ያንን ሕፃን ለማጥፋትና ለመግደል ነው። ሄሮዶስ የሥልጣንና ከሥልጣን በመሆኑ ተቀናቃኝነትን ነው የሚከታተለው፣ ሥልጣኑን የሚቀናቀነውን ነው የሚመለከተው፣ እግዚአብሔር የሥልጣኑ ተቀናቃኝ መሆኑ በልቡ ያውቃል፣ ሰብአ ሰገል በኮከብ ተመርተው ቤተ ልሔም በመሄድ እዛው ሕፃኑና እናቱን ማርያምን ያገኛሉ፣ በዚህ ወቅት የሚያጋጥማቸው ፈትና የአይሁድ ንጉሥ በትህትና የመገለጡ ሁነት ነው። ይኸንን ፈተናም አሸንፈው በመስገድ ሣጥኖቻቸውን ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ ዕጣን ከርቤም ያቀርቡለታል፣ እግዚአብሔአር በትህትና እንጂ በሥልጣነ ኃይል አልተገለጠም የእርሱ የመገለጥ መንገድ ከሰዎች መንገድ የተለየ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ትሁት ነው። ሰብአ ሰገል ወደ እውነተኛው እምነት የመለወጥ ትእምርት ናችው። በሥልጣን ሳይሆን በትህትና በተገለጠው እግዚአብሔር ዘንድ እመንታቸውን አኖሩ፣ እግዚአብሔር በትህትና የመገለጡ ምሥጢር ምንድር ነው? በዓለማችን ያለው ግጭት ጦርነት በሕፃናት ላይ በሚፈጸመው ግፍ የጦር መሣሪያ ንግድ ስቃይና መከራ በመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች ተከበናል ታዲያ እግዚአብሔርን እንዴትና የት ልገናኘው እችላለን? እዎ እግዚአብሔርን በእነዚህ በስቃይና በመከራ በተጠቁት ሰዎች ተጨባጭ ሁኔታ ዘንድ እናገናኘዋለን እዚያ ኢየሱስ አለ። የእግዚአብሔር የመገለጥ ሁነት ከዚያ ከዓለማዊነት የተለየ እርሱም ትህትና ነው፣ ብዙውን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚመራው ኮከብ የት አለ ወዴትስ ነው በማለት እንጠይቃለን እንጨነቃለን፣ በግርግም በተወለደው ሕፃን እንሰናከል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በትህትና ነውና የሚገለጠው” ብለው ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ጌታ የሚወስደውን መንገድ ታሳየን ዘንድ በእርሷ አማላጅነት ከመደናገር ከትዕቢት ከእራስ ብርሃን ከሆነው ሁሉ ርቀን በእምነት የትህትና ጽናት አማካኝነት እውነተኛውን ብርሃን እንገናኝ ዘንድ አማላጅነትዋን ተመጽነው ያስደመጡት ስብከት አጠቃለዋል።
ቅዱስ አባታችን ያሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዳበቃም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተገኘው በብዙ ሺህ የሚገመቱት መእመናን ጋር ከሐዋርያዊ መንበራቸው ባለው መስኮት ሆነው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው በፊት የእግዚአብሔር ፍቅር ማንንም የማያገል ለሁሉ መሆኑና ቅርብ ላሉት ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ርቀው ለሚገኙት በዚያ በታማኝና በትሁት ፍቅሩ አማካኝነት እነርሱን እንደሚፈልግ፦ ሰብአ ሰገልን የመራው ኮከብ ዛሬም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሆነው ኢየሱስ ይመራናል ብለው የላቲን ሥርዓት የምትከለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ግልጸት በምታከብርበት ቀን የምስራቅ ሥርዓት የሚከተሉ የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያንና የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን በዓለ ልደት የሚያከብሩበት ዕለት መሆኑ ዘክረው በዓለ ግልጸት ከሚከበርበት ዕለት ጋር ተያይዞ ዓለም ዓቀፍ የሕፃናት ቀን የሚዘከርበት ዕለት መሆኑም አስታውሰው ስለ ሕፃናት ጸልየው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.