2015-01-06 09:57:08

የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር፦ ጸረ ወንጀልና የወንጀል ቡድኖች ትግል ቆራጥና ወሳኝ ጥረት ይጠይቃል


የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በዓለማችን በተለያየ መልኩ በአዳዲስ የባርነት ሥርዓት ሥር የሰውን ልጅ ለክብር ዘራዥ ጸያፍ ተግባር የሚዳርገው ጸያፍ ተግባር የወንጀል ብድኖች የሚገለገሉባቸው ያመንዝራነት ሕይወት፣ አድልዎ፣ ብዝበዛ፣ የሰውን ለጅ በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ ሙስና ምግባረ ብልሽት የመሳሰሉት የወንጀል ብድኖች በገንዘብ ሃብት የሚያደልበው ኢሰብአዊ ተግባር ለማጥፋት ለሚያበቃው ቆራጥና ወሳኝ ጥረት ኃይል ማስተባበር ያለው አስፈላጊነት የተሰመረበት መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባሮች ሳንሆን ወንድማማቾች ነን በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ያስተላለፉት 48ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት ምክንያት ለቅዱስነታቸው ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጃንፒየሮ ጕዋዳኚ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ እ.ኤ.አ. ለ 2015 አዲስ ዓመት መግቢያ ምክንያት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 31 ቀን 2014 ዓ.ም. ለኢጣሊያና ለመላ የኢጣሊያ ሕዝብ በመገናኛ ብዙኃን አመካኝነት ባስደመጡት መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ መወገድ ያለበት የግድ የልሽነት ዓለማዊነት ትሥሥር ያለው አስፈላጊነት ያሰመሩበት ሃሳብ እርሱም የግድ የለሽነት ባህል መዋጋትና ማጥፋት እንደየ ኃላፊነቱ የሁሉም ግዴታ መሆኑ ጠቅሰው በኢጣሊያና በዓለም የሚታዩት ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች ሁሉ ለማጥፋት ቅዱስነታቸው ያመለከቱት መንገድ ወሳኝ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጒዋዳኚ አያይዘው፣ ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጥሪ በማስደገፍ ዓለማዊነት ትሥሥር ወደ አወንታዊ የትብብር ሃይል መለወጥ አለበት ብለው፣ ልዩነት የሚያገል በሃብታምና በድኻው መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት የሚያስተካክል፣ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ መዛባት ለማግለልና የሰው ልጅ መሠረታውያን መብቶችም የሚያነቃናና የሚያረጋግጥ ዓላም ሊኖረው ይገባል እንዳሉ የመልክታሉ።
ለሥራና ለሕንጸት ተገቢ ትኵረት እንዲሰጥና የሕንጸት ባህል ሕገ ወጥነት የወንጀል ቡድኖችን ለመዋጋት የሚደገፍ ሕጋዊነትና የሕጋዊነት ባህል የሚያስፋፋ መሆን እንዳለበት ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት አሳስበው፣ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት የሰላም መልእክት ያኖሩት ሓሳብና ምዕዳን የኢጣሊያና የኤውሮጳ ተቀዳሚ ዓላማ መሆኑ ስደተኞችን ማስተናገድ የተናቁት ተነጥለው በከተሞቻችን ጥጋ ጥግ በህልውና ጥጋ ጥግ የሚኖሩትን ቀርቦ መደገፍና ይኸንን ባህል ማስፋፋት ፍትህ ሰላም ሕጋዊነት እኩልነት ማረጋገጥ ከሚለው ዓላማ አንጻር አረጋግጠው፣ በመጨረሻም በዚህ በተጠቀሰው እቅድ ተጠምደው የሚያገለግሉ መንፈሳውያን ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን በጠቅላላ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማኅበራት ሥር በመታቀፍ የሚያገለግሉት ዜጎች የሚሰጡት የቃልና የሕይወት ምስክርነት የሚደነቅና ማበረታታት የሚያሻው ነው በማለት ያስተልለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ጒዋዳኚ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.