2015-01-06 09:52:32

ብፁዕ አቡነ ቶሶ፦ ሰላም መብትና ክብር በሚመለከት ጉዳይ የዓለም መሪዎች ቅዱስ አባታችንን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያዳምጡ


እ.ኤ.አ. ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በወንድም ጃኮፓ እንደተለመደው የሰላም ትምህርት በሚል እቅድ መሠረት በየዓመቱ የሚካሄደው የሰላም ትምህርት መባቻ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የ 2015 ዓ.ም. ወንድማማቾች እንጂ ባሮች አይደለንም በሚል ርእስ ሥር ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ያስተላለፉት 48ኛው ኵላዊ የሰላም መልእክት ዙሪያ የተከናወነው ዓውደ ጉባኤ የቅድስት መንበር የሰላምና ፍትህ ጉዳይ ለሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ ባስደመጡት ንግግር መከፈቱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ በዚህ አጋጣሚም በቅርቡ ለደሞክራሲ ዳግም ብቁ ሆኖ መገኘት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ በቫቲካን ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃቱንም አስታውሰው ብፁዕነታቸው ከአውደ ጉባኤ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በዓለማችን ዙሪያ የሚታዩት አዳዲስ የባርነት ሥርዓት የሰው ልጅ ወደ ላይ ያቀናው የታደለው ባህርዩ የሚጻረር ብሎም የታደለውን ነጻነት የሚሰርዝ መሆኑ ገልጠው፣ በአዲስ ባርነት ሥርዓት የሚጠቃው ግለ ሰብ ብቻ ሳይሆን ይኽ ጸረ ሰብአዊ ተግባርና ክብር ሰራዥ ያንን በእኩልነት እርስ በእርስ መከባበር ላይ በጸናው ግኑኝነት የሚመራው ሱታፌ በሰዎ መካከል ግብረ ገባዊ አድነት ለመኖር የተጠራው መላ ኅብረተሰብ ጭምር ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው፣ በመሆኑም የባርነት ሥርዓት ባላባት ወይንም ገዥና ተገዥ ወደ ሚለው ወደ ጥንታዊው ኅብረተሰብ በደረጃ ወደ ሚከፋፍለው ተግባር የሚመራና ሰውን እንደ ግኡዝ የሚመለከት ባህል የሚያረማምድ ጸያፍ ባህል የሚያረጋግጥ ነው፣ ይኽ ባህል በብሄርም ሆኖ በግብረ ገብ ተቀባይነት የሌለው ለመረዳቱ የሚያዳግት ጸያፍ ተግባር ነው። በመሆኑም ይኽ ጸረ ሰብአዊ ባህል ከሥር መሠረቱ ነቅሎ ለማጥፋት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዳሉት ባስቸኳይ ግብረ መልስ የሚያሻው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በዓለም እጅግ ጎልቶ የሚታየው በዓለማዊነት ትሥሥር ሂደት አማካኝነት እየተስፋፋ ያለው የግድ የለሽነት ተግባር ማግለል፣ በግልም ሆነ በማኅበር ደረጃ ነቅቶ ይኸንን ባህል ለመቅረፍ መትጋት፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ምላሽ መስጠት በዓለም አቀፍም ሆነ በብሔራዊ ደረጃ የአዲስ ባርነት ሥርዓት ለይቶ ለመዋጋትና ብሎም ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን ከወዲሁ የዚህ ዓይነት ጸረ ሰብአዊ ተግባር ቀድሞ ለመከላከል የሚደግፍ መዋቅር መመሥረትና ክዚህ ጋር በማያይዝም ይኸንን ጸረ ሰብአዊ ተግባር በሕግ ደረጃ የሚቆጣጠርና የአዲስ ባርነት ተግባር የሚያረማምዱ የወንጀል ቡድኖች ለመከታተል በተገቢ መቅጫ ሕግ አማካኘንትም ለማረም የሚደግፍ ሕግ ማርቀቅ ያለው አስፈላጊነት አበክረው አያይዘውም በአዲስ ባርነት የተጠቁት ዜጎች ቀርቦ መደገፍ ከወደቁበት አደጋ ለማላቀቅ መረባረብ፣ ሰብአዊ ሥነ ልቦናዊና መንፈሳዊ ሕንጸት ማቅረብና ከወደቁበት የአዲስ ባርነት ቀንበር አላቆ ከኅብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው በሰላም ለመኖር እንዲችሉ መደገፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዴሞክራሲና የዴሞክራሲው ሥርዓት ዓለማዊነት ትሥሥር ሥር ማነቃቃትና ማስፋፋት፣ የሁሉም ዜጎች ሕንጸት ሥራ የማግኘት ጸጥታና ደህንነት ሕክምና የማግኘት መግብና መጠለያ የማግኘት ቀዳሚው መብት ማረጋገጥ፣ ይኽ ሁሉ የሚረጋገጥለት ዜጋ ለአዲስ የባርነት ሥርዓት ገዛ እራሱ አሳልፎ አይሰጥም፣ የአዲስ ባርነት ሥርዓት የሚያረማምዱ የወንጀል ቡድኖች ጭምር እንዳይኖሩ ያግዛል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በስትራበርግ በኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር የሰው ልጅ ካለው ውስንነት ማዶ ያቀናው ባህርዩ የሚያከብር የሕግ ሉአላዊነት በማረጋገጥ፣ የሚታየውና እየተስፋፋ ያለው የግድ የለሽነት የግለኝነት መንፈስ ሁሉን ነገር ከጥቅም አንጻር የሚመለከት ተጠቅሞ መጣል የሚለው ባህል ኅብረተሰብና የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት ሁሉ ለአደጋ የሚያጋልጡት በጠቅላላ ህልውናን የሚፈታተኑ ተግባሮች መዋጋትና እነዚህ ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች የሚቆጣጠር እንዳይኖሩ የሚደገፍ ሕግ ማቆም አስፈላጊ ነው ያሉትን ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰዋል።
በዓለማችን የሚታየው የሰላም እጦት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ሳይሆን አለፍ አለፍ ተብሎ በሚከናወን ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ያለ እንደሚያስመስለው ቅዱስ አባታችን ያብራሩት ሃሳብ ጠቅሰው፣ ጦርነት በሚለው በተለምዶ ዓይነት የሚፈጸም ሳይሆን ዓለማችንና ኅብረሰባችን ጥሮና ግሮ በመንግስታትና በኃያላን አገሮች መካከል ከብዙ ውጣ ወረድ በኋላ የተረጋገጠው መረጋጋት መልሶ ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁነት ነው፣ በጠቅላላ ዓለማችን ወደ ከፋው ሁኔታ የሚያጋልጠው ተግባር በአንድ አዲስ የላውቀ ክብር ያለው ፖሊቲካ እንዲተካ ለአንድ ለተስተካከለና የተከበረ ፖለቲካዊ ሕንጸት አስፈላጊ ነው። የተለያዩ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ ከወዲሁ ለመከላከል የሚያግዝ መንገድም ነው። እኩልነት ፍትህ በማረጋገጥ ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻል ነው። አለ እኩልነትና ፍትህ ሰላም አይኖርም፣ ይኽ ሲባል ደግሞ ሰው ማእከል ያደረገ ባህል ማስፋፋት ማለት ነው ብለው በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅርቡ ስለ ያካባቢ ተፈጥሮ(ሥነ ምኅዳር)ና ልማት ዙሪያ ዓዋዲ መልእክት ለንባብ እንደሚያበቁ አስታውቀዋል፣ ሥነ ሰብእና ሥነ ምግባር የሚመለከት ርእስም ነው፣ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት በትክክል ያሰመሩበት ሃሳብ የሚያስታውስና የተፈጥሮ አካባቢ እርሱ የአካባቢ ሥነ ምኅዳር ከሰብአዊ ሥነ ምኅዳር የተያያዘ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮና ሰው እርስ በእርሱ የተያያዘ ጥልቅ ውስጠ ትሥሥር ያለው መሆኑ የሚገልጥ ዓዋዲ መልእክት እንደሚሆን ከወዲሁ ለመገመቱ አያዳግትም ብለው፣ ዓዋዲ መልእክቱ በጉጉት እየተጠባበቅን ነው። በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ ይኸው ከወዲሁ ብዙ አስትያየት እየተሰጠበት ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.