2015-01-05 16:56:39

ሲመተ አዲስ ካርዲናሎች:


RealAudioMP3 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና እንደተለመደ ሁሉ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ በሺ ከሚቆጠሩ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።
ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፍጽሜ በኃላ ፊታችን ወርሀ የካቲት 14 ቀን ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሀያ አዲስ ካርዲናሎች እንደሚኖርዋት ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከሃ አዲስ ካርዲንሎች 15ቱ የመምረጥ መብት ያላቸው እንደሆኑ አምስት የመምረጥ መብት የሌላቸው ማለትም በዕድሜ የገፉ እንደሆኑ እና ለቤተ ክርስትያን ከፍ ያለ አገልግሎት የሰጡ መሆናቸው ተመልክትገዋል።
20 አዲስ ካርዲናሎች ከሁሉም ክፍለ ዓለሞች ከ14 ሀገራት የተውጣጡ እንደሆኑ ይታውቃል ። ይህ የሮም ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በዓለም ዙርያ ካሉ አብ ይሃተ ክርስትያናት ጋ ያላትን ትስስር የሚገልጥ እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አስታውቀዋል።
አዲሶች ካርዲናላቱ ፊታችን ወርሀ የካቲት 12 እና 13 እንደ ግሮጎርያን አቁጣጠር
ቀን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት በጉባኤ ተቀምጠው የቅድስት መንበር ሕዳሴ ትኩረት በሰጠ ርእስ እንደሚወያዩ 15 ቀን በቅዱስ ጰጥሮስ ባሲሊክ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሁባሬ
እንደሚቀድሱ ተመልክተዋል።
ለሲመተ ካርድናልነት ከበቁ ብጹዓን ጳጳሳት ሶውስት ከአፍሪቃ አህጉር ከኢትዮጵያ ሞዛሚቢክ እና ከይፕ ቨረደ ይገኙባቸዋል። ኬይፕ ቨረድ ቶንጋ እና የቀድሞ በርማ ማይንማር አብያተ ክርስትያናት ካርዲናል ሲሰየሙባቸው ይህ የመጀመርያ ግዜ እንደሆነ ይታውቃል ።
ይሁን እና ካርዲናል ከተሰየሙ 20 ብፁዓን ጳጳሳት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳት እና የረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብጹዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ይገኙባቸዋል ፡
ስለ አባታችን ብጹዕ አቡነ ብርሃነ የሱስ ሱራፊኤል ካርዲናል መሰየም ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የደረሰን ዘገባ የሚከተለው ነው።።








All the contents on this site are copyrighted ©.