2014-12-31 15:14:04

የቅዱስ አባታች ትኩረትና ዓላማ የልብ ኅዳሴ የሚል ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. 2014 ዓ.ም. ጠቅለል ባለ አነጋገር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባካሄዱት ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ ስለ ሰላም፣ ለሞትና ለስደት ስለ ሚዳረጉት ማኅበረ ክርስቲያን ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ፣ የግኑኝነት ባህል ለማስፋፋት በተሰኙትና በተለያዩ አበይት ርእሰ ጉዳዮች ላይ በማተኰር በቃልና በሕይወት ምስክርነት አስተምህሮ መሪ ቃል የሰጡበት ዓመት መሆኑ የሚዘከር ሲሆን፣ እኚህ የአርጀንቲና ተወላጅ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በቅርብና እሩቅ በሚኖሩት የዓለም ሕብረተሰብ ዘንድ የሚደመጡ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን አቢይ ትኵረት የሚሰጡባቸው መሆናቸው በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ በሚገኘው ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ የታሪክ መምህር የሥነ ታሪክ ሊቅ አጎስቲኖ ጆቫኞሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የእኚህ ር.ሊ.ጳ. ማራኪውና እጅግ ቅርብና እሩቅ ያለው የሚስበው የተካኑት ጸጋ የማይካድ ነው፣ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. የህዳሴ ዓመት መሆኑ ቤተ ክርስቲያን እሳቸውን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ በመምረጥዋ በማስተዋወቅ በ 2014 ዓ.ም. ኅዳሴው ቀጥሎ ገና አሁንም ቀጣይነት ያለው እቅድ መሆኑ እየታየ ነው። ስለዚህ ቀጣይ የኅዳሴ ር.ሊ.ጳ. በማለት ቅዱስ አባታችንን ገልጠው፣ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሁሌ ጠዋት መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው የሚለግሱት ዕለታዊ አስተንትኖ ኅዳሴ መዋቅራዊ ውጫዊ ከመሆኑ በፊት ልብን የሚመለከት የልብ መታደስ ማለት መሆኑ ያረጋግጣሉ፣ ስለዚህ ልባዊ መታደስ ለውጫዊ መታደስ መሠረት መሆኑ ያስተምራሉ፣ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በዓለማችን በተለያየ መስክ ኅዳሴ ያለው አስፈላጊነት እርግጠኛነት በተሞላው የቃልና የሕይወት ምስክርነት አማካኝነት እያስተጋቡ ናቸው። ይኽ ደግሞ እንደ አብነት በሳቸው ልዩ ፍላጎት የተጠራው በቅርቡ የተከናወነው ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የመከረው ሲኖዶስ መጥቀስ ይቻላል ብለው፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ቅዱስነታቸው ካለ መታከት ያነቃቁት የግኑኝነት ባህል የቅድስት መንበር የዲፕሎማሲያዊ ሂደት መርህ ሆኖ ይኸው የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በሁሉም የቅድስት መንበር ቋሚና በተለያዩ አገሮች በሚገኙት ሐዋርያዊ ልኡካን አማካኝነት እየተመሰከረ ነው ብለዋል።
የዚህ ያነቃቁት የግኑኝነት ባህል ውጤትም በቅርቡ ማንም ሳያስበውና ሳይጠብቀው በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና በኩባ መካከል ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው ዲፖሎማሲያዊ ግኑኝነት መቋረጥ ተወግዶ የተነሳሳው አዲስ የግኑኝነት ተስፋ መጥቀስ ይቻላል፣ እርቅ ውይይት ይቅር በመባባል ከቲዮሎጊያዊ አብዮት ወደ ቲዮሎጊያዊ ነጻነት እንድንሸጋገር እያደረጉ ናቸው፣ በሁለቱ አመሪካዎች መካከል አንድ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍተዋል፣ ይኽ ምዕራፍ ቤተ ክርስቲያንና ፖለቲካ የሚመለከት ነው ብለዋል።
ኢራቅ ናይጀሪያ ፓኪስታን በጠቅላላ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች በማኅበረ ክርስቲያን ላይ የሚከስተው የመብት ረገጣ ለስደት የሚዳርግ አድልዎና አመጽ በተመለከተ ያየሁሉም የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነት አክብሮት እንዲረጋገጥና በሃይማኖት ስም በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመው ቅትለት የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ እንዲወገድ ትክክለኛው የሰብአዊ መብትና ክብር ትንታኔ በመስጠት ይኽ የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ዓለም በግድ የለሽነት ከመመልከቱ የተባባሪነት ልምድ እንዲላቀቅ እያስተማሩ ናቸው፣ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመ በደል አመጽ ስደት ሁሉ ምዕራቡ ዓለም በግድየለሽነቱ ከመመልከቱ ተግባር እንዲላቀቁ በማሳሰብ የግድየለሽነት ተግባር ታሪክን ያግታል ስለዚህ፣ ከዚህ ዓይነቱ ታሪክ ከማገት ተግባር ለመላቀቅ የግኑኝነት ባህል በማስፋፋት እርቅ ይቅር መባባል መተሳሰብ ፍትህ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ሰፊ ጥልቅ ትምህርት በቃልና በሕይወት ያስተጋቡበት ዓመት መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.