2014-12-31 15:20:51

የስደተኞች ሳምንት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በምትገኘው ካቲሊካዊት ቤተ ክርስቲያን


RealAudioMP3 በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁላችን በእግዚአብሔር ህልውና አንድ ቤተሰብ ነን” በሚል መርሃ ቃል ሥር እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን እስከ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. የስደተኞች ሳምንት ቀን እንደሚከናወን የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። ዓላማው የአገሪቱ ካቶሊካውያን ምእመናን በአገሪቱ ለሚገኙት ስደተኞች ጽኑ ራእይ ያለው ወሳኝ ተግባር አማካኝነት ስለ እነርሱ በመታገል ወደ አገሪቱ የሚገቡት ስደተኞች ብሩህ መጻኢ እንዲረጋገጥ ካለ መታከት ምእመናን በመልካም ተግባር ጸንተው እንዲተባበሩና በተለያየ ግብረ ሠናይ ዓላማ እንዲተጉ የሚያነቃቃ መሆኑ የገለጠው የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ አክሎ፦ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አገሮች የሚኖሩት ስደተኞች በመጡበት አገር ከሚገኙት ቤተሰቦቻቸው ልጆቻችው ጋር ለመገናኘት እድል እንዲያገኙና በስደት ምክንያት የሚፈጠረው የባለ ትዳሮች የቤተሰቦች መለያየት የመሳሰሉት ማኅበራዊ ሰብአዊ ችግሮች ጭምር እንዲቀረፍ መንግሥት መፍትሄ እንዲያፈላልግ ለማነቃቃት ያለመ የስደተኞች ሳምንት እንደሚሆን ያመለክታል።
ለስደተኞች የገንዘብ እርዳታ እንዲደረግ የሚያነቃቃ በምክር ቤቱ ይፋዊ ድረ ገጽ አማካኝነት የተለያየ ጥሪ ተካቶ የሚገኝና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚገኙት ስደተኞች ዕለታዊ ኑሮ ምን ተምስሎው የሚገልጥ ዜና ስደተኛው ለመደገፍ ምን መደረግ እንዳለበትና ስደተኛው የሚመለከተው በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የስደተኛ መቆጣጠሪያ ሕግ በድረ ገጹ በማስፈር ስደተኛው መብትና ግዴታው እንዲያወቅ የሚደገፍ መሆኑ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።
በተጨማሪም ህጋዊነት ጸረ አዳዲስ ባርነት ለሚደረገው ትግል አቢይ ድጋፍ መሆኑና ስደተኞች አለ ፈቃድ በሕገ ወጥነት የሚኖሩት ለተለያዩ ጸረ ስብአዊ አደጋ የሚያጋልጠው ችግር እንዲቀረፍ ከዚህ ለአዳዲስ ባርነት ከሚያጋልጣቸው ወጥመድ እንዲላቀቁ መንግሥት ሕጋዊ እውቅና እንዲሰጥ በስፋት ጥሪ የሚቀርብበት ሳምንት ከመሆኑም ባሻገር ሃሴትና ተስፋ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሰነዶች እንዲሁም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት በስፋት ጠቀስ የተለያየ ጸሎት አስተንትኖና አስተምህሮ የሚቀርብበትና በዚሁ የስደተኞች ሳምንት ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው የሚያገለግሉት የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት አካላት ጭምር የሚያሳትፍ እንደሚሆን የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.