2014-12-31 17:25:47

ወርሀ የካቲት 11 ቀን እኤአ የበሽተኞች ቀን ታስቦ ይውላል ፡
የር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ መልዕክት ፡


RealAudioMP3 ፊታችን ወርሀ የካቲት 11 ቀን እኤአ 20015 ዓለም አቀፍ የበሽተኛ ቀን ተከብሮ እንደሚውል የሚታወስ ሲሆን ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዕለቱ ትኩረት በመስጠት መልዕክት ማስተላለፋቸው ቫቲካን ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል። የዓለም አቀፉ የበሽተኛ ቀን ርእስ ከኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ ከ29 እስከ 15 ሆኖ ለዓይነ ስዉር ዓይን ነበርኩኝ ለአንካሳ እግር ነበርኩኝ የተሰየመ እንደሆነ መግለጫው አመልክተዋል።ለሕሙማን የሚጠፋ ግዜ ቅዱስ ግዜ መሆኑ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልዕክት ጠቁሞ ፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊገለገል ሳይሆን ለማገልገል ከሰማየ ሰማያት መውረዱ እንደሚያስገነዝብ ተገልጠዋል። ሕሙማን ሁለ ገባዊ እንክብካቤ ያገኙ እንደሆን መልካም ይሰማቸዋል እንክብካቤ ካጡ ግን በብቸኝነት ይጠቃሉ ያለ የቅድስነታቸው መልዕክት ፡ በከባድ የታመሙ ሰዎች መኖራቸው ጥቅም የለውም እንደሚባል አስታውሰው ክፋት ሐሰት እና ኢ ሰብአዊነት እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው በመልዕክታቸው ላይ ማስፈራቸው ተገልጠዋል። አብዛኛው ግዜ ሕሙማንን የመንከባከብ ፍላጎት እና ትዕግስት ሲያንስ ይታያል ያሉት ቅድስነታቸው ይህ እምነት ከማነስ ሊሆን እንደሚችል እና ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ስራ ስትሰሩ ለኔ እንዳደረጋችሁት ነ ብሎ ያለውን መዘንጋት ነው ማለታቸው ተመልክተዋል። ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር የሰጠን ጸጋዎች ሁሉ በነጻ እንደሰጠን ሁሉ እኛ ለሰው ልጅ በደስታ መስጠት መንከባካብ ይጠበቅብናል ሕሙማንን መጐብኘት መንካባከብ ሞራል መስጠት መቻል አለብን ለነሱ የምናደርገው መልከም ስራ ለመድኅን ክርስቶስ እንዳደረግነው ማሰብ እና ከሕሙማን ጋር የምናጠፋው ግዜ ቅዱስ ግዜ ነው ሲሉ በመልዕክታቸው ላይ ማስፈራቸው ተገልጠዋል።የመሰቃየት ሚስጢር በየኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደሚገለጥ እና ይህ የእግዚአብሔር ምሕረት እንደሚያመለክት ጠቅሰው ፡መሰቃየት የእምነት መረጋገጫ እንደሆነ ማምልከታቸውም የቫቲካን መግለጫ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልዕክት ዋቢ በማድረግ አስገንዝበዋል።የሚገጥመን ሕመም እና ስቃይ ሁሉ እምነታችን በጽኑ እምነት ላይ የተመሰረተ አቀባበል ካደረግንለት ስቃያችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቃየው ስቃይ ለመመሳሰል ይችላል እምነት አልባ ስቃይ ለመሸከሙ ከባድ መሆኑ ጠቅሰው ፡ በስቃይ እና መከራ ግዜ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን የማለት ተክህሎ እንዲኖር ያሻል በማለት መጻፋቸው ተገልጠዋል። ለሕሙማንን ለቀናት ለወራት ለዓመታት ሁለገባዊ እገዛ የሚሰጡ የሚንከብባከቡ ሰዎች የሕክምና ባለ ሙያዎች ዘመድ ወዳጅ ሁሉ የተመስገኑ ይሁኑ በማለት ፊታችን የካቲት ወር 11 ቀን ተስታውሶ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀን የጻፉት መልዕክት ማስገንዘቡም ተመልክተዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.