2014-12-31 15:13:16

አባ ስፓዳሮ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ማራኪነትና ሥልጣን ለሕዝብ እጅግ ቅርብ ከመሆናቸው የሚመነጭ ኃይል ነው


RealAudioMP3 በቅርቡ አንድ የኢጣሊያ ዕለታዊ ጋዜጣ ተጨባጭ የዓለምና ብሔራዊ ዓቀፍ ጉዳዮች በአኃዝ ትንተና የሚያቀርብ ደሞስ የተሰየመው ድርጅት የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ማራኪነትና ኵላዊ አወንታዊ ሥልጣናዊ ተጽእኖ መሠረት ምን ይሆን በሚል ጥይቄ ሥር ባካሄደው የሕዝባዊ አስተያየት ክትትል ያጠንቀረው ዘገባ በማደገፍ በሰጠው ዜና እጅግ ለሕዝብ ቅርብ ከመሆናቸው የሚመነጭ ኃይል ነው የሚል መልስ በስፋት ድምጽ የተሰጠበት መሆኑ ሲያመለክት፣ ይኸንን ጉዳይ በማስመልከት በኢየሱሳውያን ማኅበር በሁለት ሳምንት አንዴ ለሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ አንቶኖዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ዓለማችን የታማኝነት እማኔ የሚያኖሩባቸው አካላት ግሽበት እጅግ የተጠቃና የመተማመን ያሳማኝነት እውነተኛ በቃልና በሕይወት የተመራ ተግባር እጥረት የተሞላ በሆነበት በዚህ በአሁኑ ወቅት ቅዱስ አባታችን ለሕዝብ ቀርብ በተለይ ደግሞ ለተናቁት በጥጋ ጥግ የከተሞቻችን ለድኾች ለህልውና ጥጋ ጥግ ሰብአዊ ጉዳይ ቅርብ በመሆን በሁሉም ዘንድ ታማኝና ከዚህ ቅርበት የመነጨ አሳማኝና ታማኝ እንዳደረጋቸውና ከዚህ ጥልቅ ቅርበት የመነጨ ሥልጣናዊ ኃይል እንዳላቸው አብራርተዋል።
ሁሌ እንደምናየው የሥልጣን ኃይል ይኸውም በዓለም ዓይን ከህዝብ ርቆ በመኖር ተከቦና ታጥሮ በጥበቃ ኃይል ተከቦ ከመኖር ተግባር የሚመነጭ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ኃይል ሳይሆን ድካምነት ነው፣ ቅዱስ አባታችን ለሕዝብ ያላቸው ቅርበት ይኽ እውነተኛው መንፈሳዊነት ሰብአዊነት የተጠማው ዓለም በሳቸው ላይ ያለው እማኔ ከፍተኛ መሆኑ ያመለክታል። ስልጣናቸውም ይኽ የሰብአዊነት ቅርበት ነው ብለዋል።
በቅርቡ ጋዜጠኛ ደራሲ ካቶሊካዊ ምእመን ቪቶሪዮ መሶሪ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለሚያነቃቁት የኅዳሴ መርሃ ግብር በተለያየ መስክ ለመቀበል የሚያዳግታቸው አካላት እንዳሉ ይናገራሉ፣ በርግጥ እውነት ነው፣ ይኽ ደግሞ የቅዱስነታቸው ኅዳሴ ውጤታማነት የሚያረጋግጥና ኅዳሴው እውነት መሆኑ የሚያመለክት ሁኔታ ነው። ቅዱስነታቸው ነጻ በሳል ክርስትና የሚያነቃቁ ናቸው፣ እንዲህ በመሆኑም ከማናኛውም አካልና ሁኔታ ጋር ቀርቦ መወያየት የማያዳግታቸው ናቸው፣ ቤተ ክርስቲያን ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ ያነቃቃችው ኅዳሴ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እያመለከቱት ባለው ጎዳና የሚከወን መሆኑ አብራርተዋል።
ቅዱስ አባታችን የሥነ ግብረ ገብ ሰባኪ አይደሉም አለ መሆናቸው በተለያየ መድረክና መንፈሳዊ ርእስ ሥር በሚሰጡት ምዕዳንና አስተምህሮ በሚያስደምጡት ንግግሮች በቃልና በሕይወት የሚያረጋጋጡት እውነት ነው። ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት አበይት የቤተ ክርስቲያን ባለ ስልጣናት ለበዓለ ልደት ምክንያት ባስደመጡት ንግግር የተመሰከረ እውነትም ነው። ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግኑኝነት እንመርምር ዘንድ የሚያነቃቃ ክርስቶሳውያን እንሁን የሚል ነው። መንፈሳዊነት ተዘክሮ ማጥፋት እንዳያጋጥም አደራ የሚል ጥሪ ነው። ስለዚህ ያንን ከክርስቶስ ጋር የተገናኘንበት ያ ሕይወታችን የለወጠው ግኑኝነት መለስ ብለን እንድናስታውስ የምናደርገው ህያው የተዘክሮ ጉዞ ፍጹማን ባለ መሆናችን የተነካ ነው። በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ፍጹማን አለ መሆናችን ወደ ምግባረ ብልሽት እንዳይመራን አንድ አዲስ የታደስ ህሊና እንድናጎለብት አደራ ያሉበት መልእክ እንጂ የሚወቅስ እጅ የሚቀስር መልእክት አይደለም፣ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመመስከር የተጠራች ነች፣ ስለዚህ ይኽ የምሥረታዋ ምክንያት የሆነው እውነት እንዳይዝል አደራ ብቻ ሳይሆን በጽናት ያሳሰቡበት መልእክትም ነው። ከዚህ እውነት ያራቃት ምን መሆኑ ለይተው በመተንተን እንድንጠነቀቅ ጥሪ አስተላልፈዋል። የሚገርመው ይኽ መልእክት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስትያን ውጭና በጠቅላላ ከክርስትናው ዓለም ርቀው በሚኖሩት አካላት ማኅበራትና ኅብረተሰብ ጭምር ሙሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ አድርገዋል። ምክንያቱም የታደሰ ኅሊና ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም የሚመለከት ጥሪ ነው። የቅዱስነታቸው ኃይል ወንጌላዊው ሕይወት ነው ብለዋል።
ቅዱስነታቸው መልካም አፍቃሪ የሁሉ ወዳጅ ናቸው፣ ልበ ርህሩህ ደግ ናቸው ሆኖም ግን ያላቸው ርህራሄ መልካምነት ደግነት ወንጌላዊ ነው። ስለዚህ ወንጌላዊ በመሆኑም ምክንያት ብዙ እንቅፋት ያጋጥመዋል፣ ወንጌልና ክርስቶስን በትክክልና በእውነት በቃልና በሕይወት ስትኖር የሚያጋም ችግር መዘርዘሩ አያስፈልግም፣ ግልጽና የታወቀም ነው። የወንጌላዊነት ሕይወት ምስክር ወንጌል እንጂ ሰው አይደለም፣ ለምትኖርነው ወንጌላዊ ሕይወት ምስክር ወንጌል ከሆነ ማንኛውም ዓይነት መሰናክል ችግር ቢያጋጥምህ እትወድቅም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.