2014-12-27 18:42:31

የር.ሊ.ጳ የልደት መልእክትና ሐዋርያዊ ቡራኬ፤


RealAudioMP3 የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ፤ መልካም በዓለ ልደት!
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የዓለም መድኅን ስለ እኛ ተወለደ። የተነገረው ጥንታዊው ነቢያዊ ቃል በቤተ ልሔም ከአንዲት ድንግል በመወለድ ተከወነ፣ ድንግልዋም ማርያም ትባላለች እጮኛዋም ዮሴፍ ይባላል።
ትሁታን ሙሉ ተስፋ በእግዚአብሔር መልካምነት ያኖሩ ኢየሱስን ያስተናገዱና ያወቁ ሰዎች ናቸው። እንዲህ ባለ ሁኔታም የቤተልሄም እረኞች በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ተሞልተው ወደ ግርግም በመሄድ ለሕፃኑ ሰገደሉት፣ ቀጥሎም መንፈስ ቅዱስ ትሑታን ለሆኑ ስምዖንና ሃናን በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑ እንዲያውቁ አደረገ። “ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህ አይተዋል” ሲል ስምዖን ቃሉን ያስተጋባል።
አዎ ወንድሞቼ ኢየሱስ ለእያንዳንዱ ሰው ለእያንዳንዱ ሕዝብ ድኅነት ነው!
የዚህ የዓለም መድኅን የሆነው ኢየሱስን ዛሬ የምለምነው! በኢራቅና በሶሪያ ያሉት ገና አሁንም እልባት ያጣው ግጭት በሚያስከትለው መዘዝ ከሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችና ጎሳዎች ጋር በከፋ ስደት የሚሰቃዩትን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲመለከት እጠይቃለሁ። ልደት ለእነርሱ እንዲሁም በብዙ ለሚገመቱት ለዚያ ክልል ተፈናቃዮች ስደተኞች ሕፃናት ጎልማሶችና አረጋውያን በጠቅላላ በዓለም ለሚገኙት ሁሉ ተስፋ ያድርስ። ሁሉም በዚህ ሁኔታ የሚሰቃዩት የዚህ የክረምት ብርቱ ሁኔታ ለመወጣት የሚያስፈልጋቸው የሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት እንዲችሉ ግድየለሽነት በመቀራረብ ማግለል በማስተናገድ ጸጥ ይበል። ጌታ ልቦች ለታማኝነት እንዲከፈቱና ከዚያች በልደቱ ምክንያት ከተባረከቸው መሬት ጀምሮ በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል ፍቱን ውይይት እንዲረጋገጥ ለሚከናወነው አቢይ ጥረት በመደገፍ ሰላሙን ለመላ መካከለኛው ምሥራቅ ይለግስ።
ኢየሱስ የዓለም መድህን፣ በኡክራይን የሚሰቃዩት ተመልከት፣ ያች የተወደደቸው መሬት ተከስቶ ያለው ውጥረት ትወጣውም ዘንድ፣ ጥላቻና እመጽ በማሸነፍ አንድ አዲስ የወንድማማችነትና የእርቅ ጎዳና እንዲትከተል አድርግ።
ክርስቶስ መድኅን ለናይጀሪያ ሰላምን ስጥ። ብዙ ሰዎች ከሚያፈቅሩት ሁሉ አለ ምንም ፍትህ የተለዩት፣ የታገቱት ለእልቂት ለተዳረጉት ሰላም ስጥ። በተለይ ሊቢያን ደቡብ ሱዳን መካከለኛይቱ አፍሪቃ የተለያዩ የዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ክልሎችን በማሰብ ለሌሎች ለአፍሩቃ አህጉራትም ጭምር ሰላምን እማጠናለሁ። ፖለቲካዊ ኃላፊነት ያላቸው ሁሉ በውይይት አማካኝነት ልዩነቶች እንዲወገዱና ዘላቂ ወንድማዊ የጋራ ኑሮ እንዲገነባ ይጠመዱ ዘንድ አጠይቃለሁ።
ኢየሱስ ብዙውን ጊዜ የአመጽ ሰለባ የሚሆኑትን ሕፃናትን አስብ፣ በሰው ልጅ ንግድ እንደ ግኡዝ ዕቃ የሚታዩትን የሰው ልጅ በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ ለሚያንቀሳቅሱ የሚደረጉት ተግደው በውትድርናው ዓለም የሚዳረጉትን አስብ። አዎ ሕጻናትን የብዙ ዓመጽ ሰለባ ለሆንትን ሕጻናት አስብ! ባለፈው ሳምንት በፓኪስታን ለተገደሉት ሕፃናት ቤተሰቦችና በወረርሽኝ የኤቦላ በሽታ በተለይ ደግሞ በላይበሪያ በሰራሊዮንና በጊኒ ሞት ላጋጠማቸው ለሙታን ቤተሰቦች መጽናናቱን ለግስ፣ በበሽታው ለተጠቁት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውንም ጭምር በጽናት ድጋፍና አስፈላጊው የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙት ሁሉ ብርታቱን ስጥ።
ኢየሱስ ሕጻን! ስለኢየሱስ ሕጻን ሳስብ ቀልቤን በሙሉ የሚሰመው በዛሬው ዕለት ለሚገደሉና ለሚጨፈጨሩ ሕጻናት ላይ ነው፤ እነኚህ ሕጻናት ገና የዚህ ዓለም ብርሃን ለማየት ያልታደሉ የወላጆች ፍቅር የተነፈገባቸው ሕይወትን በማያፈቅር በራስ ወዳድነት ባህል ጨለማ የተቀበሩ እንዲሁም በውግያና በስደት ምክንያት የተፈናቀሉና የተመዘመዙ ይህም በፊታችን እያየነውን ከአመጸኞቹ ጋር በሚያስማማን ዝምታችን የተሸፈነ ሲሆን በተለያዩ ድብደባዎች ጌታ በተወለደው ቦታም ሳይቀር ስንት በደል እየተፈጸመ ነው፣ ዛሬም ሳይቀር የእነዚህ ንጹሓን ኃይል አልቦ ሕጻናት የዝምታ ልቅሶ በብዙ ሄሮዱሶች በተመዘዘው ሰይፍ ስር እየተሰማ ነው፣ በንጹሕ ደሞቻቸው ላይ የዘመናችን ሄሮዶሶች ጥላ እያንዣበበ ነው፣ እውነት እላችህዋለሁ፤ ልክ ከሕፃን ኢየሱስ እንባ ጋራ በዚህ በበዓለ ልደት ብዙ እንባ እየፈሰሰ ነው።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በቤተልሔም ከድንግል ማርያም እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ለእያንዳንዱ ሰው፣ ለመላ ዓለም ሰዎች በተወለደው ሕጻነ ኢየሱስ የለገሰው ድኅነት እንድናውቅ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ያብራ። የኢየሱስ ኃይል አርነትና አገልግሎት ነውና በጦርነት በስደተ በባርነት ለሚሰቃይት ሁሉ ይሰማ። ይኽ መለኮታዊ ኃይል የደነደነው የብዙ ወንዶችና ሴቶች ልብ ከተነከረበት ዓለማዊነትና ግዴለሽነት በጥበቡ ያውጣ። አዳኝ ኃይሉ የጦር መሳሪያ ወደ ቀንበር የማውደም ተግባር ወደ የፈጠራ ተግባር ጥላቻ ወደ ፍቅርና ርህራሄ ይለውጥ። እንዲህ ሲሆን በደስታ፦ ዓይኖቻችን ማዳንኅን አይተዋል” ለማለት እንችላለን።
ለሁሉም መልካም ልደት!








All the contents on this site are copyrighted ©.