2014-12-12 18:15:10

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣(10.12.2014)


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ስለቤተክርስትያን ባህርይ አንድ የጥናት ዙርያ አካሄደናል፣ ይህንን የቤተ ክርስትያን መልካም ባህርይ ለማጥናትና የሁላችን ቤተ ክርስትያን በመሆንና ቤተ ክርስትያን የምንባል እኛ ራሳችን መሆናችን በማወቅ ኃላፊነታችን እንድናውቅና እንድንለብስ ላስቻለን እግዚአብሔር እናመስግን፣ ዛሬ አዲስ ም ዕራፍ እንጀምራለን፣ የዚሁ የትምህርተ ክርስቶስ ዙር መሪ ርእስ ቤተ ሰብ ይሆናል፣ አጋጣሚ ሆኖ ይህ ርእስ ስለእርሱ በሚያጠኑ ሁለት ሲኖዶስች መካከል እናካሄደዋለን፣ ስለሆነም ስለቤተሰብ ያሉትን አር እስቶች ከመጀመር በፊት በዛሬው ዕለት ባለፈው ወርኃ ጥቅምት በዚሁ በመንበረ ጴጥሮስ “የቤተ ሰብ ስብከተ ወንጌል ተግዳሮች በአዲሱ ስብከተ ወንጌል” በሚል መሪ ሓሳብ ስለተካሄደው ልዩ የሲኖዶስ ጉባኤ ለመናገር እወዳለሁ፣ እንዴት ተካሄደ ምንፈስ አፈራ ብሎ መጠየቅና ማስታወስ አስፈላጊ ነው፣
በሲኖዶሱ ጊዜ መገናኛ ብዙኃን ሥራቸውን ሠርተዋል፣ ምክንያቱም ከሲኖዶሱ ብዙ ነገሮች ይጠባበቁ ስለነበር ትልቅ ሽፋን ሰጥተውታል ለዚህም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፣ ብዙ ዜና ተሰራጨ፣ እንዲህ የሆነውም የቅድስት መንበር ዜናና ኅትመት ክፍል በየዕለቱ ባቀረበው የዜና መግለጫ ስለሆነ ለዚህም አመሰግናለሁ፣ ነገር ግን መገናኛ ብዙኃኑ ይህንን ዜና ያሰራጩት እንደ የስፖርትና የፖሎቲካ ዜና ዓይነት ነው፣ በሲኖዶሱ ሁለት ቡድኖች ማለት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ገስጋስያንና ዓቃባውያን ወዘተ እየተባለ ይወራ ነበር፣ ዛሬ አጠር ባለ መንገድ በሲኖዶሱ ምን ተደረገ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እወዳለሁ፣
ከሁሉ አስቀድሜ የሲኖዶስ አባቶችን ያለውን ሁኔታ ቅንነት ብርታት አንግበው እንዲናገሩ ሌሎችንም በትሕትና እንዲያዳምጡ ማለትም በልባቸው የሚሰማቸውን ሁሉ በድፍረት እንዲናገሩ አሳሰብክዋቸው፣ በሲኖዶሱ ውስጥ የሰንሱር ነገር አልነበረም ስለዚህ እያንዳንዱ አባት በልቡ ያለውን መናገር የሚሰማውንም በንጽሕና ማለት እንዳለበት ነበር፣ ይህ እርምጃ ብዙ እንደሚያከራክርም ግልጽ ነበር፣ እርግጥ ነው ነገር ግን ሓዋርያት እንዴት ይወያዩና ይከራከሩ እንደነበሩ አይተናል፣ በግብረ ሓዋርያት “ኃይለኛ ክርክር ነበረ” ይላል፣ ይህም የሆነበት ምክንያት ክርስትና በተቀበሉ አይሁድና አሕዛብ መካከል ባህል ነክ ግዝረትንና አመጋገብን የመሰሉ ኅዲገ ልማድ ጽኑዕ ውእቱ የሚያሰኙ ክርስትናን ከአይሁድ ባህል ጋር የሚያያዙ ሁኔታዎች ኃያል ክርክር በመነሳቱ ነበር፣ እዚህ ላይ የሓዋርያቱ ችግር የእግዚአብሔር ፍላጎት ነበር፣ እንዲህ ዓይነት ችግር አዲስ ነገር ሲገኝ ሁሌ ያጋጥማል፣ በአበው ሲኖዶስም ያጋጠመው ይህ ነበር ባሉን በተለያዩ አስተያየቶች የእግዚአብሔር ፍላጎትን ለማወቅ መወያየት መጥፎ አይደለም፣ ነገር ግን ሁሌ በትሕትናና ወንድሞችን ለማገልግል ዝግጁ በመሆን መደረግ አለበት፣ ምናልባት ቍጥጥር ወይንም ሰንሱር የተደረገ ቢሆን የባሰ ነበር፣ እንዲህማ አይሆንም እያንዳንዱ በልቡ ያለውን መናገር ነበራቸውና፣ ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ ካቀረቡት የመጀመርያ ረቂቅ ሁላቸው የተናገሩት ስለቀረበ ከበድ ያለ ነበር ነገር ሁሉንን ማዳመጥ ስለነበራቸው ይህ ድርጊት መልካም ነበር፣ እያንዳንዱ የሲኖዶስ አባት ቅኑ በሆነ መንፈስ በመተማመን በልባቸው የሚሰማቸውን የተናገሩበት ታላቅ የነጻነት ግዜም ነበር፣ ለዚሁ መሠረት የሆነው ደግሞ ከሲኖዶሱ በፊት ከመላዋ ቤተ ክርስትያን በተሰበሰቡ አስተያየቶች የቆመ መወያያ ሰነድ ኢንስትሩመንቱም ላቦሪስ ነበር፣ ለዚህም የሲኖዶሱ ጽሕፈት ቤት ሲኖዶሱን ለማዘጋጀትና በሲኖዶሱ ግዜ ላደረጉት አስተዋጽኦ እናመሰግናቸዋለን፣ እውነትም ጎበዞች ናቸው፣ በሲኖዶሱ ሂደት ውስጥ የቃል ኪዳን መሠረታዊ እውነትን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ አልነበረም ማለትም ቃል ኪዳን የማይፈታ እንዲሁም በቃል ኪዳን ያለው አንድነትና መተማመን ለሕይወት ክፍተቱን የነካ የለም፣ እነኚህ ነጥቦች አልተነኩም፣
አባቶች ያቀረቧቸው ነጥቦች ሁሉ በጽሑፍ ላይ ሰፍረው ሁላችን ካየናቸው በኋላ ከውይይት በኋላ የቀረበ ዘገባ በሚለው በሁለተኛ ድረጃ ተጠቀለሉ፣ ይህም ዘገባ በብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ ነበር የተዘጋጀው፣ በሶስት ነጥቦች ላይም አትኵረዋል፤ አንደኛው የቤተሰብ ተግዳሮችንና ሁኔታዎችን ጸጥ ብሎ ማዳመጥ ሁለተኛ ትኵረታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተሰብ ወንጌል መሆን እንዳለበት ሶስተኛም ያለውን ሁኔታ ከቤተ ክርስትያን የእረኝነት ተል እኮ ጋር መወዳደር የሚሉ ነበሩ፣
በዚሁ ነጥቦች ላይ የትናንሽ ቡድኖች ውይይት ተካሄደ፣ ይህ ሶስተኛ ደረጃ መሆኑ ነው፣ ቡድኖቹ በየሃገሮቻቸው በሚጠቀሙት ቋንቋ ነበር የተቋቋሙት ማለትም በጣልያንኛ በእንግሊዝኛ በእስፓኒሽ እና በፈረንሳየኛ፣ እያንድናዱ ቡድንም ከውይይት በኋላ የየራሱ ጥናታዊ ሰነድ አቅርበዋል እነኚህም ሰነዶች በአንድነት ታትመዋል፣ ሁሉም እንዲያነባቸውና ግልጽ እንዲሆኑም ለሁሉ ተሰጥተዋል፣ ከዚህ የሚከተለው አራተኛ ደረጃ ሲሆን ይህም እነኚህን ሰንዶች ባጠቃላይ አጥንቶ የመጨረሻውን ረቂቅ ለሲኖዶስ አባቶች የሚያቀርብ ኮምሽን ተቋቍመዋል፣ በመጨረሻም አባቶች በኅብረት አጥንተው ከተወያዩና ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ የመጨረሻው የሲኖዶስ መል እክት ተዘጋጅተዋል፣ ይህም ለጥናት በመላው ዓለም ባለችው ቤተ ክርስትያን ይሰራጫል፣ ስለዚህ የቤተሰብ ሲኖዱሱ ሂደት እንዲህ ነበር፣ ምናልባት ከእናንተ መካከል “አባቶቹ ተጋጭተዋል/ተጣልተዋል ወይ?” ብሎ ሊጠይቀኝ ይችላል፣ ነገር ግን እንደተጋጩ ወይንም እንደተጣሉ እንኳ ለመናገር ባልችልም በሲኖዶሱ ኃይለኛ ክርክር እንደነበረ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፣ ይህም በቤተክርስትያናችን ውስጥ ያለው ነጻነት ነው፣ ሁሉ ግን ከጴጥሮስ በጴጥሮስ መሪነት እንደተካሄደም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣ ይህ ማለትም ር.ሊ.ጳ እንደ የቤተክስትያን የበላይ ኃላፊ በጉባኤው ውስጥ ነበር ይህም የነጻነትና የመተማመን ዋስትና በመሆን የአንቀጸ እምነት ዋስትናም ነው፣
ስለዚህ ከሲኖዶሱ የተላኩ ይፋዊ መል እክቶች ሶስት ናቸው፣ እላይ የጠቀስኩት የመጨረሻው መል እክት፤ ኮሚሽኑ ያቀረበው አጠቃላይ ዘገባ እና የር.ሊ.ጳ የመዝግያ ንግግር ናቸው፣ ሌላ ምንም ነገር የለም፣
ሲኖዶሱ የደረሰው የመጨረሻው መልእክት ትናንትና ታትመዋል አሁን በመላው ዓለም ላሉ ረኪበ ጳጳሳቶች ይላካል፣ እያንዳንዱ ረኪበ ጳጳሳትም በመል እክቱ ይዘት ይወያያል እፊታችን ጥቅምት ወር 2015 ዓም ለሚካሄደው አጠቃልይ የጳጳሳት ሲኖዶስ እንዲያገልግልም የውይይቶቹ ውጤት ወደ መንበረ ጴጥሮስ ይላካል፣ ትናንትና ታትመዋል የምላችሁ መልእክት ውስጥ ለሚመጣው ሲኖዶስ መሪ ሓሳቦች የሚሆኑ ጥያቄዎችም ከሰነዱ ጋር ይላካሉ፣ እነኚህ ጥያቄዎች ደግሞ ለሚመጣው ሲኖዶስ መርኃ ግብር ለማዘጋጀት ይጠቅሙናል፣
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ሲኖዶስ ሲባል እንደ አንድ ፓርላመንት ሆኖ የዚች ቤተ ክርስትያን ተወካይ የዛኛዋ ቤተ ክርስትያን አባል በማለት የሚደረግ አይደለም፣ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ስር የሚተዳደር ሆኖ መለያየት የሌለበት በጳጳሳት መካከል ከብዙ ዝግጅትና ጸሎት በኋላ ለቤተሰብ ለቤተክርስትያን ብሎም ለመላው ማኅበረሰብ የጋራ ጥቅምና መንፈሳዊ በጎ ነገር የሚካሄድ ጉባኤ ነው፣ ስለሆነም በዚሁ ልዩ ሲኖዶስ የተዘጋጀው ዘገባ ለጥናትና ለአስተንትኖ ወደ አብያተክርስትኖች ይመለሳል እሳቸው ጸልየው አስተንትነው ከተወያዩ በኋላ ለሚመጣው ሲኖዶስ ይጠቅማል ያሉትን ይልኩልናል፣ የጳጳሳት ሲኖዶስ ትርጉሙ ይህ ነው፣ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ጥበቃ እናማጥነው፤ እርሷ የእግዚአብሔር ፍላጎትን ለመረዳት ትረዳን ዘንድ እንዲሁም ለቤተሰብ የሚያገልግሉና የሚረዱ ሁነኛ እርምጃዎች ለመውሰድ ትርዳን፣ እስከሚመጣው ሲኖዶስ ይህንን ሂደት በጸሎት እንድትሸኙት እማጠናለሁ፣ እግዚአብሔር ብርሃኑን ይሰጠን ዘንድ ለሁሉም አብያተ ክርስትያናት ማለት ያለብንን ነገር በደንም እንድናውቅ ይረዳን ዘንድ ጸሎታችሁ እጅግ አስፈላጊ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.