2014-12-10 18:57:28

ቤተ ክርስትያን እናት ስለሆነች ፍጹም የሆነ መዋቅራዊ የአስተዳደር ሰንጠረዥ አያስፈልጋትም፣


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እንደተለመደው ትናንትናም በቅድስት ማርታ ቤተ መቅደስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ “የቤተ ክርስትያን ደስታ የጠፉ በጎችዋን በመፈለግና በማግኘት የሚገኝ ደስታ የሚሰጣት እናት መሆን ነው” ሲሉ ቤተ ክርስትያን እንደ እናት በፍቅርና እርኅራኄ ልጆችዋን በማገልገል እንጂ መዋቅራዊ የሆነ ቢሮክራስያዊ አስተዳደር መጠጋትና መተማመን እንደሌለባት ምክንያቱም በወታደራዊ ዓይነት ሕግ መጓዝ በገዛ ራስዋ የተወሰነችና ዝግ ሆና ኃዘን ውስጥ ስለሚከት እያንዳንዱ ክርስትያን በጌታ ኢየሱስ ምሕረትና ርኅራኄ በሚያገኘው መጽናናት ደስተኛ መሆን አለበት ሲሉ ስብከዋል፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ ትናንትና የተነበበው የመጀመርያ ንባብ ከትንቢተ ኢሳይያስ 40፡1-11 “አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ።
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ እግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።
የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።” ሲሆን ቅዱስነታቸው ከዚህ በመነሣት “በንባቡ እንደሰማነው ያኔ በባሊሎን ስደት ለነበረው ሕዝብ የእግዚአብሔር ማጽናናትና የእርሱን በመካከላቸው መኖር ማወቅ እንዳሻቸው በፈተናና በችግር በምንገኝበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ማጽናናት በሮችን መክፈት ያስፈልጋል፣ አብዛኛውን ጊዜ ፈተና እና ችግር በሚገጥመን ጊዜ ከፈተናውና ከችግሩ መሸሽ ብቻ እንጂ ስለ እግዚአብሔር መጽናናት ከቶም አናስብም፣ እንድያው መተማመን አጥተን በገዛ ራሳችን ጉዳዮች እና ችግሮችና ኃጢአት ታጥረን ለመቅረት እንወዳለን፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስና መጽናናት አብረው በሚመጡን ጊዜ ልንቆጣጠረው የማንችለው የጌታ መጽናናት ይዘውልን ይመጣሉ፣ ከሁሉም የሚበልጠው መጽናናት ደግሞ የምሕረትና ኃጢአትን ይቅር የማለት መጽናናት ነው፣ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን በትንቢተ ሕዝቅኤል 16 ላይ የሕዝበ እስራኤል ኃጢአት ዝርዝር ካቀረበ በኋላ እንደማይተዋት ቃል ኪዳኑም እንደሚያስታውስ በማመለከት በም ዕራፉ መጨረሻ ላይ “ስላደረግሽውም ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ ታስቢ ዘንድ ታፍሪም ዘንድ ስለ እፍረትሽም ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ፥ ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አጸናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፥” በማለት የእግዚአብሔር ምሕረትና ይቅር ባይነት ምንኛ ያህል እንደሚያጽናና ያመለክተናል፣ አብዛኛውን ግዜ በገዛ ራሳችን በፈጠርናቸው ትናንሽ መጽናናቶች እንደሰታለን ግን ወዲያውኑ ይበናሉ፣ የእግዚአብሔር መጽናናት ግን ታላቅና ለዘወትር ስለሆኑ እሱን እንሻ” ሲሉ ስለአንደኛው ንባብ ካሳሰቡ በኋላ በዕለቱ ስለተነበበው ቃለ ወንጌል ማቴ. 18 የተወሰደው ስለ ጠፍታ የተገኘች በግ ምሳሌ መለስ ብለውም በጥያቄ መልክ “የቤተ ክርስትያናችን መጽናናት ምን ይሆን” ብለው ይጠይቃሉና “አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ምሕረትና የኃጢአት ይቅሬታ ሲሰማው ታላቅ ማጽናናት ያገኛል ቤተ ክርስትያንም በዚሁ ታላቅ በዓል ታደርጋለች፣ ከገዛ ራሷ ወጣ ብላ የጠፋችውን በግ አግኝታ ቤትዋ ስትመልሳት ታላቅ ደስታ ይሰማታል፣ በወንጌል እንደተገለጸው 99 ትቶ የጠፋችውን አንዲት ለመፈለግ እንደተሰማራው መልካሙ እረኛ ቤተ ክርስትያንም እንደዛው ታደርጋለች፣ ነገር ግን እንደነጋዴዎች አስተሳሰብ ቢሆንና በትርፍና ኪሳራ ዓይን የተመለከትን እንደሆነ 99 ከአንዲት በ99% ስለሚበልጥ ችግር አይደለም ብለን ዝም ማለት ይቻላል፣ የመልካም እረኛ ልብ ላለው ግን እንደዚህ አይደለም ሁሉን ትቶ የጠፋችውን ለማግኘትና ካገኛትም ድግስ ደግሶ ደስታውን ይገልጣል፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን ደስታ ከገዛ ራስዋ ወጣ ብላ የጠፉትን ወንድሞችንና እኅቶችን ስትፈልና ስታገኛቸው ነው፣ እንዲህ በማድረግም ቤተ ክርስትያንዋ እናት ትሆናለች ፍሬም ታፈራለች፣ ይህንን የማታደርግ ቤተ ክርስትያን ምንም እንኳ በአስተዳደር መዋቅር ሁሉ በየቦታውና በየዘርፉ የሚንቀሳቀስ ቢመስልም የዚች ዓይነት ቤተ ክርስትያን በገዛ ረሷ የተዘጋች ከሁሉ በላይ ደግሞ ደስታ የሌላት ኃዘንተኛ መተማመን የጐደለባት የማትረባ እናት ሆና ቤተመዘክር ትሆናለች፣ የቤተ ክርስትያን ደስታ እንደ እናት አዳዲስ ልጆች መውለድ የጠፋውን መፈለግ የመልካሙ እረኛ ፈር መከተል ሲሆን ጌታ ደግሞ ለዚህ የሚሆን ጸጋ ይሰጠናል” ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.