2014-12-09 12:24:58

የብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ ሓዋርያዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ፤


በቅድስት መንበር የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ማሕበር የበላይ ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ይፋ ለመጐብኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የግእዝ ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል ምስራቃዊት ቤተ ክርስትያን ስትሆን እንደ የቫቲካን የዜና ተቋም ብጹዕ ካርዲናሉ ሀገሪቱ ውስጥ ከተመሰረተ 50ኛ ዓመት ያስቆጠረ ረኪበ ጳጳሳት ትኩረት ሰጥተው ከሀገሪቱ ብጹዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጋር ይወያያሉ።
በዚሁ የዜና ተቋም ዘገባ መሰረት ብጹዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ ትናትና ጥዋት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ካተድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ካሳረጉ በኃላ፡ ካቶሊካውያን ቁምስናዎች ካቶሊካውያን ማሕበረ ሰቦች ካቶሊካዊ ሕክምና ቤቶች እየተዘዋወሩ ጐብኝተዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ በቅድስት መንበር የምስራቅ ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያናት ማሕበር የበላይ ሐላፊ በኢዮጵያ ቆይታቸው ከየሀገሪቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ከብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃለማርያም ደሳለኝ ጋር ይገናኛሉ።
ስለዚሁ ጉብኝት ከአዲስ አበባ የዘወትር የዜና ተባባርያችን የሆነችው ማክዳ ዮሐንስ የላከችልን ዘገባ ለማደመጥ፡ RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.