2014-12-03 18:33:41

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ዝናምና ደመና የበዛበት ከበድ ያለ ቀን ይመስላል ነገር ግን እናንተ ብርታት የሞላችሁ ስለሆናችሁ እንዲህ ላለ ከበድ ያለ ቀን ፈገግ ማለት ያስፈልጋል፣ ዘወትር ዝናም ሲያጋጥም እንደምናደርገው የዛሬው አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ በሁለት ቦታዎች ይካሄዳል፣ አንዱ በዚህ አደባባይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እዚ ከመምጣቴ በፊት ሰላም ያልክዋቸው ሕሙማን በሚገኙበት ጳውሎስ ስድስተኛ አደራሽ በቪድዮ ይተላለፋል፣ እጆቻችን በማንጨብጨብ ሰላም እንበላቸው፣
ዛሬ ካለፈው ዓርብ እስከ እሁድ በቱርክ ስለፈጸምኩት መንፈሳዊ ንግደት ላካፍላችሁ እወዳለሁ፣ ገና ሓዋርያዊ ጉዞው በዕቅድ በነበረበት ጊዜ በጸሎት እንድናዘጋጀው እንድንሸኘው እንደጠየቅህዋችሁ አሁንም እግዚአብሔር ይህን ጉዞ የተሳካ በማድረጉ ሁላችን ምስጋና እንድናቀርብ ስጠይቅ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከወንድሞቻችን ኦርቶዶክሳውያንና ሙስሊሞች ያደርግናቸው ግኑኝነቶችና ውይይቶች ፍሬ እንዲኖራቸውና በሕዝቦቹ መካከል ሰላም እንዲገኝ እንድንጸልይ እጠይቃለሁ፣ በቱርክ ባደርግሁት ሓዋርያዊ ጉዞ በታላቅ ክብር ለተቀቡሉኝ እንዲሁም ሁሉ በሰላም እንዲሳካ ላደረጉ የሪፓብሊክ ቱርክ ፕረሲደትና ጠቅላይ ሚኒስተር እንዲሁም የሃይማኖታዊ ጉዳዮች ፕረሲደንትና ሌሎች ባለሥልጣኖች ምስጋናየን እንደገና ለማቅረብ እወዳለሁ፣ የቱርክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጳጳሳት እጅግ ጐበዝ ለሆነው የረኪበ ጳጳሳቱ ፕረሲደት በአገሩ ካሉ ካቶሊካውያን ማኅበረ ክርስትያን በመተባበር ላደረጉልኝ ሳመሰግን እንዲሁም ከዚህ ባላነሰ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያክ ብፁዕና ቅዱስ በርተለሜዎስ አንደኛ ስላደረጉልኝ ልባዊ አቀባበል አመሰግናለሁ፣ ከዓመታት በፊት አገሪቱን የጎበኙ ብፁዕ ጳውሎስ ስድተኛና ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዲሁም ያኔ በአገሪቱ የር.ሊ.ጳ እንደራሴ የነበሩ ቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ ይህንን ከእኔ በፊት የነበሩ በነዲክቶስ 16ኛ ካደረጉት ጉብኝት ስምንት ዓመት በኋላ ላከናወንኩት መንፈሳዊ ንግደቴን በመንግሥተ ሰማያት ሆነው እንደጠበቁት አምናለሁ፣ ይህች አገር ለሁሉም ክርስትያን ልዩ ትርጉም ያላት ናት፣ በመጀመርያ የቅዱስ ሓዋርያ ጳውሎስ ትውልድ አገር መሆንዋ እንዲሁም የመጀመርያዎቹ ሰባት ጉባኤዎች ያስተናገደችም ይህች አገር ናት፣ ከኤፌውሶን ወጣ ብሎ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቤት ይገኝበታል፣ የቤተ ክርስትያን ትውፊታችን መንፈስ ቅዱስ በእመቤታችን ድንግል ማርያምና በሓዋርያት ላይ ከወረደ በኋላ እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ ቤት እንደኖረች ይነግረናል፣
በሓዋርያዊ ጉዞየ የመጀመርያ ቀን የአገሪቱ መሪዎችን ሰላም አልኩኝ፣ ምንም እንኳ አብዛዎቹ ሙስልሞች ቢሆኑም የአገሩ ሕገመንግሥት ግን ከሃይማኖት ገለልተኛ ነው፣ ከመንግሥት ባለልሥልጣናት ጋር ስለዓመጽ ተወያይተናል፣ ዓመጽ ከእግዚአብሔር ጥላቻ እንጂ ለእርሱ ክብር ከማቅረብ አይወለድም፣ ስለዚህ ክርስትያኖቹም ይሁኑ ሙስሊሞች በአጋርነት ለሰላምና ለፍትሕ እየሰሩ ለሁሉም ዜጋና የሃይማኖች ማኅበሮ እውነተኛ የእምነት ነጻነት ያረጋግጡ፣
ዛሬ ሕመምተኞቹን ሰላም ለማለት ከመሄዴ በፊት ብፁዕ ካርዲናል ቱራን እየመሩት ያሉት በውስጠ ሃይማኖታዊ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተዘጋጀ በክርስትያኖችና በሙስልሞች መካከል ስላለው ግኑኝነትና አንድነት የሚያጠና ቡድን ተቀቤ አነጋገርኩ፣ እነኚህም እዚህ ላይ የጠቀስኩትን የእምነት ነጻነት ሰላምና ፍትሕ እንደሚያፈልግ ገለጡልኝ እኔም በዚሁ መንፈስ በካቶሊካውያን ክርስትያኖችና ሙስሊሞች መካከል ውይይቱ እንዲቀጥል አደራ አልክዋቸው፣
በሁለተኛ የጉብኝቴ ቀን በአገሪቱ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ትልቅ ትርጉም ያላቸው ምሳሌ የሚሆኑ ቦታዎችን ጎበኘሁ፣ይህን ሳደርግ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ መሓሪው እግዚአብሔር ጥሪ እና የመላው የሰው ልጅ ጸሎት በልቤ ይሰማኝ ነበር፣ የዚሁ ቀን አንኳር መሥዋዕተ ቅዳሴው ሲሆን በዚሁ ሥርዓት የአገሪቱ የተለያዩ ሥርዓተ አምልኮ የሚከተሉ ካቶሊካውያን እረኞችና ም እመናን ተገኝተው ነበር፣ በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ኤኩመኒካዊው ፓትርያርክ የአርመን ሓዋርያዊት ፓትርያርካዊት ቤተ ክርስትያን ኅየንተ እና የሲሮ ኦርቶዶክስ መትሮፖሊታ እንዲሁም የፕሮተስታንቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል፣ ሁላችን አብረን ደግሞ በቤተ ክርስትያን አንድነትን የሚሰጥ የእምነት የፍቅርና የውሳጣዊ ውህደት አንድነት የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስን ለምነናል፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ባጠቃላይ ሃብታም ከሆኑ ባህሎቹና ትምህርቶቹ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ እንዲመራ መፍቀድ አለበት በዚህም ቀጣይ የሆነ የልብ ክፍተትን እንዲሁም ትሕትናና መታዘዝ ይወለዳል፣ የአንድነት ውይይታችን አንድነታችን ነው፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አንድነትም ነው ይህንን የሚያደርገው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ እኛ ማድረግ ያለብን እንዲመራን ልንፈቅደው እና እርሱ ያስተንፈሰልንን መቀበልና መከተል ያስፈልጋል፣ በሶስተኛውና የመጨረሻ ቀን ደግሞ የቅዱስ እንድርያስ ሓዋርያ ክብረ በዓል በመኖሩ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሆነው በሮማው ጳጳስና የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም የሆነው የቍስጥንጥያን ቤተ ክርስትያን የመሠረተ ቅዱስ እንድርያስ ተከታይ በሆነ በቍስጥንጥንያው ኤኩመኒካዊ ፓትርያርክ መካከል ያለውን ወንድማማዊ ግኑኝነትን ለማጠንከር ምርጥ ጊዜ ነበር፣ ከቅዱስነታቸው በርተለሜዎስ 1ኛ በካቶሊኮችና በኦርቶዶክሶች መካከል ፍጹም አንድነት እስኪሆን ድረስ በብርታት እንደምንሰራ ቃላችን አሳደስን፣ በኅብረት ደግሞ አንድ አዋጅ በማጽደቅ ፊርማችንን አኑረናል፣ ይህ ታሪካዊ ፍጻሜ እኔም በተሳተፍኩት እና የቍስጥንጥንያ ፓትርያርክና የሮማ ጳጳስ አንዱ ለሌላው በሰጠናቸው መንታ ቡራኬዎች በተደረገው የቅዱስ እንድርያስ ክብረበዓል ሥርዓተ አምልኮ ፍጻሜ መደረጉም ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል፣ ስለሆነም ለማንኛው የአንድነት ውይይት አንድነት በሚሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንዲካሄድና ፍሬ እንዲያፈራ ጸሎት የግድ ያስፈልግል፣
የመጨረሻው ግኑኝነት ደግሞ ሆኖም ባንድ በኩል መልካም ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝኝ ግኑኘት ሆኖ በሳለዝያን ቤት ውስጥ በእንግዳነት ያሉ ወጣት ስደተኞችን ተቀብዬ አነጋገርኩ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ተከስቶ ካለው ውግያ የተሰደዱትን ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነበር ባንዱ በኩል ቅርቤቴና የቤተክርስትያንቻንን ቅርበት ለመግለጥ በሌላ በኩል ደግሞ ስደተኞችን ተቀብለው በመርዳት የሚገኙ ሰዎች የሚያበርክቱትን ምግባረ ሠናይ ለማሞገስ ሲሆን ቱርክ በዚህ ሥራ ብዙ እያበረከተች ነው፣ በዚህ አጋጣሚም ቱርክን ስለዚህ የስደተኞች መቀበልና እርዳታ እንደገና ሳመሰግን በእስጣንቡል የሚገኙ የሳለስያን ደናግልን ከልብ አመሰግናለሁ፣ ሳለስያውያን ስደተኞችን በመርዳት ብዙ እያበረከቱ ናቸው፣ ጐበዞች ናቸው፤ ሌሎች ካህናትም አግኝቼአለው እነኚህ ከጀርመን የመጡ ሲሆኑ አንድ ኢየሱሳዊ ካህናም ነበራቸው፣ ሌሎችም ከሳለዛያን ጋር በመተባበር እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀው ስንት መልካም ሥራ እየሠሩ ነው፣ ለእነዚሁ ሰዎች ለስደተኞች በሚያደርጉት እርዳታ እጅጉን አመሰግናለሁ፣ ይህ አሰቃቂ የስደት መስቀልን እንዲያቀልላቸው ስለስደተኞችና ጥገኞች እንጸሊ፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ሁሉ ቻይና መሓሪ የሆነው እግዚአብሔር የቱርክ ሕዝብ መሪዎችንና የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮችን ይጠብቅ፣ እነኚህ ሁሉ አብረው ሰላም የሰፈነበት መጻኢ እንዲያንጹ በዚህም ቱርክ በተለያዩ ሃይማኖቶችና ባህሎች መካከል ተቻችሎው በሰላም የሚኖሩባት አገር በመሆን ለሌሎች ምሳሌ ትሁን፣ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ይህ ሐዋርያዊ ጉዞየ ፍርያም ሆኖ ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮዋን በማሳደስ ያ እውነት ሰላምና ፍቅር የሆነውን ክርስቶስ በመከባበርና በወንድማዊ ውይይት ለሕዝቦች ሁሉ ታበስር፣ ኢየሱስ ብቻ ነው ጌታ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.