2014-12-01 17:05:38

ሐዋርያዊ ጉብኝት ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በቱርክ፡



ቅድስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቱርክ ልሶውስት ቀናት ያካሄድት ሐዋርያዊ ዑደት አጠቃልለው ትናንትና አምሻቸው በሰላም ወደ መንበር ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ተመልሰዋል ።ቅድስነታቸው በየትይርክ ርእሰ ከተማ አንካራ ከመንግስት እና ከየሃማኖት ከፍተኛ ተቋም ባለ ስልጣናት ጋር ተገኛንተው ከተወያዩ በኃላ ወደ ኢስጣምቡል መጓዛቸው እና እዚያው እንደደረሱ ሰማያዊ መስጊድ መጐብኘታቸው አይዘናጋም የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቱርክ ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ እና አንካራ ላይ የሀገሪቱ መስራች እና የመጀመርያ ፕረሲዳንት የአታ ቱርክ ቤተ መዘክር የኢስጣምቡል መስጊድ ጉብኝት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።በባህል አኳያ ብቻ ሳሆን በመንፈሳዊ በኩ ሲታይም ጉብኝቱ እጂድ አስፈላጊ ነበር የሰማያዊ መስጊድ ዓቢይ ሙፍቲ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መስጊድ ውስጥ እንደገቡ የቁራን ይዘታ ገልጸውላቸዋል።ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እዚያው መስጂድ ውስጥ ለተወሰነ ግዜ በዝምታ መቆየታቸው ጠቅስው ቅድስነታቸው እና ሙፍቲ ክስርታኖች ይሁኑ ሙስሊሞች በየእምነታቸው እግዚብሔርን በነጻ እንድያመለኩ መግባባባትጋቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ምሎማባርዲ አመልክተዋል።ኢስጣምቡል ላይ የሚገኘው ትልቁ መስጂድ የክ ብቻ ሳይሆን የመካከለኛው ምስራቅ ባህል እና ልምድ የሚያንጸባርቅ እንደሆነ ቃል አቀባዩ በማይያዝ ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ንሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከሰማያዊ መስጂድ ሌላ ከተማይቱ ውስጥ የሚገኘው የቅድስት ሶፍያ ካተድራል መጐብኘታቸው እና ካተድራሉ እስከ ቁስጢንጢንያ ውድቀት የመካክለኛው ምስራቅ ክርስትያኖች ነገስታት ካትደራል የነብረ መሆኑ እና ቆይቶ ወደ መስጂድ የተቀየረ እንደሆነ ቃል አቀባዩ አስታውቅዋል።ይህ የመካከለናው ምስራቅ ጥንታዊ መንፈሳውነት እና የካሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ጥበብ እና ኃያልነት የሚያንጸባራቅ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ይሁን እና የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቱርክ ያካሄዱት ይሶውስት ቀናት ሐዋርያዊ ዑድት ስኬታማ መኖሩ እና ከእስላም ሃይማኖት የሚካሄደው ውይይት እየተራመደ እንደሆነ ገልጠዋል።በሌላ በኩል ከቅድስነታቸው ጋር ወደ ቱርክ የተጓዙ በቅድስት መንበር የክርስትያን አንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ፡ ቅድስነታቸው ፓናር በተለ መካን የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተ ክረስትያን ከፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎመዮ ጋር ተገናኝተው በስፊው ስለ ክርስትያን አንድነት እና ጳለም አቀፍ ሰላም ግትኩረት በመስጠት መወያየታቸ እና ውይይቱ ስኬታማ መኖሩ ገልጠዋል።
ከውይይቱ በኃላም ኢስጣምቡል ውስጥ ወደ ሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ካተደራል ተጉዘው ከተድራሉ ውስጥ በላቲን ቋንቋ በጋራ አባታችን በሰማይ የምትኖር ጸሎት መድገማቸው አስታውሰው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የቁስጢንጢንያ ቤተ ክርስትያን ግንኙነት በመልካም አኳሃን እንደሚገኝ ብጹዕ ካርዲናሉ አስታውቀዋል።ከ50 ዓመታት በፊት የቀድሞ የአብያተ ክርትያናቱ መሪዎች ይሄውም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድተኛ እና የቁስጢንንያ ኦሮዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ
አተናጎራ በኢየሩሳሌም ተገናጠው መጸለያቸው አስታውሰው ግንኝነቱ ወትሩ መልካም መኖሩ አመልክተዋል። በነዲክት 15ኛ በየመጀመርያ የዓለም ጦርነት ለሰላም ያካሄዱት ትግል እና ጥረት በማመስገን እና በማወደስ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሱ ውልት ኢስጣምቡ ውስጥ እንደሚገኝ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ሌላ ቅዱስ ጳውሎስ ዮሐንስ ዳግማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብ አነዲክት 16ኛ አሁንም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኢስታምቡል መጐብኘታቸው የሁለቱ አብያተ ክረስትያናት ሸጋ ግንኙነት የሚያመላክት እንደሆነ ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኾክ አስገንዝበዋል።ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ስታከብር የቁስጢንጢንያ ቤተ ክርስትያን ልዑካን በክብረ በዓሉ ተሳታፊ እንደሚሆኑ በሌላ በኩል ደግማ የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በዓመት አንድ ግዜ ወርሀ ሕዳር የቅዱስ እንድርያስ በዓል ስታከብር የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ልዑካብ የክብረ በዓሉ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስታውሰዋል ።ትናትና ሕዳር 30 እኤአ አቁጣጠር ኢስጣቡል ላይ ተከብሮ የውለውን የቅዱስ እንድርያስ ዓመታዊ በዓል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ተከታዮቻቸው ብጹዕን ካርዲናላት እና ጳጵሳት ተስሳታፊ መሆናቸው ገልጠዋል።ሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ማለት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክድ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የክርስትያን አንድነት እንዲገኝ ያለሰለሰ ጥረት እያካሄዱ መሆንቸውም በተጨማሪ አመልክተዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎሎሞዮ አንደና በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን በጋራ መለኮታዊ ሥርዓተ አምልኮ ከፈጸሙ በየፓትርያርኩ አዳራሽ የአንድነት ቡራኼ ሰጥተው የጋራ መግለጫ ሰጠዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ፓትርያርክ ቀዳማዊ ባርቶሎሞዮ በሰጡት የጋራ መግለጫ የክርስትያን አንድነት እንዲገኝ እንዲጥሩ በመካከለኛው ምስራቅ እና በዩክሬይን ሰላም እንዲገኝ አጽንኦት ሰጥተው አሳሰበዋል ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ፓትርያርኩ ሁለቱ አብያተ ክርስትያናት አንድነት እንዳይፈጥሩ የገጠምዋቸው እክሎች ለማስወገድ ጥረታቸው ከፍ እንድያደርጉ የጌተቻን መድኀኑታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍላጎት ለሟሟላት የተቸላቸውን ሁሉ እንድያደርጉ ቃል ገበተዋል።ከ35 ዓመታት በፊት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ፓትርያሪክ ዲሚትርዮስ በሁለቱ አብያተ ክርስትያናት መካከል ሥነ መለኮታዊ ውይይት እንዲካሄደ ያቃቋሙት ሀገራት አቀፍ የጋራ ኮሚስዮን በሁለቱ አብያተ ክርስትያናት እንዲደገፍ በግራ መግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጵሳት ፍቭራንሲስ እና ፓትርያርክ ብ ኣርቶሎሞዮ በአጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ በተለይ በዒራቅ እና ሶርያ ውስጥ በተከሰቱ አስከፊ ሁኔታዎች በእጅግ እንዳሳሰባቸው እና በጋር ብለሰለም እንዲሰሩም አክለው ገልጠዋል።በዚሁ ክልል ሁሉም ያካተተ የዕርቀ ሰላም ውይይት እንዲከናወወንም ለዓለም ሕብረት ሰብ ባል በጎ ፈቃድ ሰዎች በጋራ ተማጽነዋል። ለሁለት ሺ ዓመታት የክርስትና እምነት የተከተሉ የመካከለኛው ምስራቅ ህዝቦች ሁኔታ አስከፊ በመሆኑ እንዳሳሰባቸውም በዚሁ የጋራ መግለጫ ተወስተዋል።
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የመካከለናው ምስራቅ ክርስትያኖች ለስደት እና ለእንግልት መዳረጋቸው አሳዛኝ እንደሆነ ጠቅሰው በመንፈስ ከነሱ ጋር እየተሰቃዩ መሆናቸው ቅድስነታቸው እና ፓትርያርኩ በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታውቅዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጵሳት ፍራንሲስ የቁስጢንጢንያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ባርቶሎሞዮ ላደረጉላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ከልብ አመስግነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.