2014-11-28 16:13:00

በተስፋ መኖር እንጂ የሚታየው የክፋት መንፈስ ለሚያሳድረው ጭንቀት እጅ አለ መስጠት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ህንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በዕለቱ ምንባብ መሠረት፦ በተስፋ መኖር እንጂ የክፋት መንፈስ ለሚያስከትለው ጭንቀት እጅ አለ መስጠት” በሚል ሃሳብ ዙሪያ ሥልጣናዊ አስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቱ ገለጡ።
ቅዱስነታቸው የዕለቱ አንደኛው ምንባብ ከዮሓንስ ራዕይ እንዲሁ ከሉቃስ ወንጌል የተነበበው ቃለ ወንጌል መሠረት በማድረግ፣ ባቢሎንና ኢየሩሳሌምን ጠቅሰው እነዚህ ሁለት ከተሞች የዚህ ዓለም ፍጻሜ ላይ እናተኩር ዘንድ ይገፋፉናል፣ የሁለቱ ከተሞች ውድቀት መሠረቱ ምንድር ነው? አዎ ጌታን አለ ማዳመጥ መሆኑ ግልጽ ነው። ከእርሱ ራቁ፣ ባቢሎም የክፋት መንፈስ ምልክት፣ የዓለም ጌታ ነኝ ባይነት ትዕቢት የሙስና የሓጢኣት ከተማ። ሓጢኣት ሲከማች ከኃጢኣት ተጸጽቶ የመመለስ ፈቃድ ይበናል፣ ለምድር ነው ሙስና ደስታ የሚሰጠው፣ የሥልጣን ልዕልና እንዲሰማህ ስለ ሚያደርግ፣ ገደብ የለሽ በራስ ላይ የመተማመን እርካታ ስለ ሚያሰጥም ነው። ይኽ ሁሉ በልብ ውስጥ ሕይወትህ በጌታ ለመለወጥ ሥፍራ እንዳይኖርህ ስለ ሚያደርግ፣ ትወድቃለህ፣ ኤኮኖሚያዊ ሙስና ብቻ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣ የከፋው ሙስና ደግሞ የዓለም መሆን በጠቅላላ ሰብአዊ መንፈሳዊ ሙስና ነው” እንዳሉ ጂሶቱ አስታወቁ።
“ባቢሎን በተለያየ ዘርፍ በሙስና በመነከርዋ ወደቀች፣ ኢየሩሳሌም ሊያድናት ለመጣው ጌታ እምቢ በማለቷ ወደቀች፣ ምክንያቱ ድህነት የሚያስፈልጋት መሆኑ አይሰማትም ነበር፣ የነቢያት መጻሕፍትና የሙሴ ቃላት ነበራት፣ እዎ ይኽ ብቻ ይበቃኛል በማለትዋ ገዛ እራሷ ለድህነት ጸጋ ልቧን በመዝጋት ምክንያት ገዛ እራስዋ በቃላት ላይ አኖረች፣ ድህድነት ለመቀበል ለማዳመጥ በእርሱ ለመዳን ዝጉጅነት አላሳየችም፣ ስለዚህ ወደቀች” ብለው ከዚህ ጋር በማያያዝ፦ ምንም’ኳ ሓጢኣተኞችም ብንሆንም ታሪካችንን በማሰብ ጌታ በነጻ በሚያቀርበው ማዕድ ቀርበን ገዛ እራሳችንን ወደ እርሱ ቀና ስናደርግ ጭንቀት የሌላቸው ተስፈኞች እንሆናለን፣ አዎ ብዙ ከተሞች ሥፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ በስቃይ ይገኛል፣ ጦርነቶች ግጭቶች ምቀኝነት ቅናት የዓለም ሆኖ የመኖር ስሜት ሙስና ይታያል፣ ነገር ግን ይህ ሁሉ ይወድቃል፣ ስለዚህ በዚህች ሰዓት አንገታቸችንን ቀና በማድረግ ለጌታ ማዕድ ዝግጁዎች ሆነን እንገኝ ዘንድ ጸጋውን እንለምን” በማለት ያስደመጡት ሥልጣናዊ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.