2014-11-28 16:09:41

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ፦ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን የብሥራት ቃል አብሣሪዎች ናቸው


RealAudioMP3 ክርስቲያኖች ማንም ሳይነጥሉ ለሁሉም ወንጌል ሊያበስሩ የተጠሩ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ጳውሎስ የገዳማውያን ማኅበር አባላት በብፁዕ ጃኮሞ አልበሪዮነ የተመሠረተው ማኅበራቸው ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት ለመንፈሳዊ ንግደት ሮማ የገቡት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የማኅበሩ አባላት ተቀብለው በለገሱት መሪ ቃል አሳስበው፣ የማኅበራችሁ ዝክረ መቶኛው ዓመት ምሥረታ በእውነት እምነት ለመኖርና ለሌላ የማካፈል ጥሪያችሁ የሚታደስበት ወቅት እንዲሆንላችሁና በተለይ በመገንኛ ብዙሃን ላይ ያተኰረው አገልግሎታችሁ የአስፍሆተ ወንጌል መሣሪያ ከመሆኑ ዓላማ እንዳይቦዝን አድበማለት ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎ ሞናኮ ገለጡ።
“ወንጌልን በወንጌላዊ ሕይወት አማካኝነት ማወጅ እርሱም በነጻ በሚሰዋ ፍቅር አለ ምንም የገበያ መንፈስ፣ በነጻ በንጽሕና ሙሉ ፍቅር አማካኝነት የተቀበልነውን በነጻና በሚሰዋ ፍቅር አማካኝነት ማካፈል ያለው ደስታ መኖር፣ የዚህ ዓይነቱ ወንጌላዊ ኃሴት ተመክሮ የሚያደርግ ብቻ ነው ወንጌል በኃሴት ለማካፈል የሚችለው፣ ወንጌላዊ ኃሴት የሚኖር ወንጌል በኃሴት ላለ ማካፈል አይቻለውም፣ ምክንያቱም ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ ወንጌል ማካፈል የወንጌል እምቅ ኃይል ነውና” አለ ምንም ገደብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለላወቅቱ ወይንም ልባቸውን ላደነደኑት ሁሉ ወንጌል ማካፈልና ማድረስ፦ “እነዚህ ሁሉ በውስጣቸው እግዚአብሔር የሚፈልጉ ናቸው፣ ሰው እግዚአብሔር ፈላጊ ነው። በእነዚያ ጥንታውያን ክርስቲያን አገሮችም የሚኖሩና በጠቅላላ ሰው የእግዚአብሔር ጥማት አለው፣ ስለዚህ ሁሉም ወንጌል ሊደርሳቸው ይገባል፣ መብታቸውም ነው። ክርስቲያን ደግሞ አለ ምንም ገደብና አድልዎ ወንጌል ለሁሉም የማድረስ ግዴታ አለባቸው። ተጓዥ ቤተ ክርስቲያን መሆናችን ክርስቶስንና ፍቅሩ ለሁሉም ሰው ዘር በማበሰር ላይ የጸና ነው። ይኽ ደግሞ ምድራዊና ዓለማዊነት ለተጠቁት መዋቅሮች ተገዥ ከመሆን ተግባር ይገላግለናል፣ ምክንያቱም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተነገረው የተራራው ስብከት ክፍት የሆነ መንፈስ የሚኖሩና በዚህ ብፁዓን ናቸው በሚለው የተራራው ስብከት አማካኝነት መጻኢን ለመወጠን እያንዳንድዋ ጊዜ ለዚያ የብፅዕና ጥሪ ያተኮረ ስለ ሚሆን ነው” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎ ሞናኮ ገለጡ።
“ሥራችሁ አገልግሎታችሁ ሐዋርያዊ ቀናተኛነታችሁ ለአንድነት የሚል ፍቅር የተሞላ እንዲሆን አደራ፣ በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የምትሰጡት አገልግሎት የዚያ የግጭቶችና የውጥረቶች ትርኢት የሚሹ በእያንዳንዱ ሰው መንፈስ እንቅፋት የሚያሳድሩ ዓለማውያን የመገናኛ ብዙኃን የሚከተል እንዳይሆን፣ ዘወርት ለዚያ ክርስቶስ በጸሎቱ ለአባቱ አንድ እንዲሆኑ በማለት ለጸለየላት ለቤተ ክርስቲያን ውህደት የሚበጅ ይሁን። አሁንም ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ በጉጉት ይጠባበቃሉ፣ ስለዚህ የሚሰዋ ፍቅር አገልግሎት በእውነቱ ያለው የፈጠራ ብቃት ገደብ የሌለው ገዛ እራሱ ለሁሉም ክፍት የሆነ ነው። በሁሉም ባህሎችና ማኅበረሰብ ዘንድ የወንጌል እስትንፋስ አለ፣ ተልእኮአችሁ ከዚህ አንጻር ሲታይ አቢይና ጥልቅ ነው። ሁሉም በግልና በማኅበር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዲገናኝ መደገፍ ነው። ለዚያ ወቅታዊ ምልክቶችና ሁኔታዎች በማንበብ ተስፋና ሰላም ለሚሻው ሕዝብ ሁሉ የተስተካከለ መልስ ለመስጠት እንዲቻል ለሚያበቃው ለመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ልባቸው ክፍት በማድረግ ብቻ ነው ሁሉም ከጌታ ጋር እንዲገናኝ ለመደገፍ የሚቻላቸሁ” በማለት ያስደመጡት መሪ ቃል ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎ ሞናኮ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.