2014-11-28 16:05:37

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ማኅበረ ውፉያነ አባላት መዋቅራዊ ኅዳሴ ሊያስፈራቸው አይገባም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚዘልቀው አዲስ ወይን፣ አዲስ ስልቻ በሚል ርእስ ሥር የመናንያንና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማሕበራት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር እ.ኤ.አ. እሁድ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ የሚጀመረው የመናንያንና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ዓመት ምክንያት ያሰናዳው ዓመታዊ ይፋዊ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በይፋ መጀመሩ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጋባእያኑን ተቀብለው፦ “ማኅበረ ውፉያን መዋቅራቸውን ለማደስ አይፍሩ” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ የመንፈስ ቅዱስ አስተንፍሶ እጅግ አይሎ ሁሉም ገዳማውያን መንፈሳዊ እንዲሁም የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት መንፈሳዊ መዋቅራቸውን ባጠቃላይ የተቀበሉት መንፈሳዊ መርሆ መሠረት ለማደስ ማነቃቃቱ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፣ ሁሉን ነገር ትተው ኢየሱስን ለመከተል የተጠሩት አዲስ ብስራት ለማበሰር የተሰማሩት ሴቶችና ወንዶች ለወቅታዊው ዓለም ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሚችል ፈር ማኅበራቸው ለማደስ መቼም ቢሆን መፍራት እንደሌለባቸው ሲያሳስቡ፦ “አሮጌውን ስልቻ ልማዶችን ጥንታውያን መዋቅሮቻችን ትተን ቤተ ክርስቲያናችንና መንፈሳዊ ማህበራት ዛሬ እግዚአብሔር በዓለም መንግሥቱን ለማስፋት እነዚያ የፍቅር ሥራን የሚገድቡ የሃሰት ትንቢት እርሱም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ብሥራት ለማዳመጥ እሮሮ ለሚያሰሙ መልስ ለመስጠት እንዲችሉ የሚያበቃቸው ኅዳሴ ለማረጋገጥ መፍራት አይገባም ለማደስ መፍራት አይገባንም” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
“እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔርን ለማገልገል ጥሪ ያላቸው ለይቶ መምረጥ፣ ለተጠሩት የተስተካከለ ብቁ ሕንጸት ማቅረብ የሚል መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችን፦ “የተጠሩት የመምረጥ ብቃትና ሕንጸት እጅግ ወሳኝ ነው። እንዲሁም እጅግ የሚያሳስበኝ ድኽነት የድኽነት ማህላና ምርጫ ነው። ቅዱስ ኢግናዚዩስ ድኽነት ‘እናትና የውፉይ ሕይወት ከለላ ነው’ ይላል፣ አዎ ድኽነት ሕይወት እንደምትሰጥ እናት ነች፣ ከለላ ሲባል ደግሞ የዓለም ከመሆን በዓለም ከመሳብ ፈተና የሚጠብቅ ነው። ውፉይነት ጌታን ለመኖርና በጌታ ቃል ሌሎችን ለማገልገል መጠራት ማለት ነው፣ ስለዚህ አደራ ለአዲስ የመናንያን ሕይወት አባላት መጸለይ ጌታን ማምለክ በቅዱስ ቁርባን ፊት መጸለይ ጌታን ማወደስ ጊዜ ማባከን እንዳልሆነ በጥልቀት አስተምሩዋቸው፣ እኛ ሕይወታችን ለጠራው ጌታ የሰጠን ውፉይነት ጸጋ በነጻነት በጌታ ፊት ዘወትር ቆም ብለን በመጸለይ በማስተንተን የማንኖረው ከሆን ወይኑ ኰምጣጤ ይሆናል” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ “የውፉያን ዓመት ለማክበር በምንዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት በእውነቱ ሕይወታችን አዲስ ወይንና አዲስ ስልቻ ይሆን ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ትርዳን በዚህ በውፉይ ሕይወታችን እርሷ ትሸኘን አዲስ ብቃት ያለው መንገድ ለመለየትና ትንሣሴ በአዲስ የጋለ ስሜት ለመኖር በእርሷ አማላጅነት ጌታ ጸጋው ያድለን” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.