2014-11-28 17:25:42

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በቱርክ የሶውስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከመንበረ ሐዋርያ ቅ.ጰጥሮስ ተነስተዋል :


ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በቱርክ የሶውስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከመንበረ ሐዋርያ ቅ.ጰጥሮስ ተንስተዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቱርክ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማከማወን ዛሬ ጥዋት ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ተንስተዋል። ይህ ዛሬበቱርክ የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኛት 6ተኛ ሀገራት አቅፍ ሐዋርያዊ ዑደት መሆኑ ነው ።ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቱርክ ርእሰ ከተማ አንካራ እንደደረሱየቤተ ክርስትያን እና የመንግስት ባለስልጣናት ደናቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል።
ቅድስነታቸው ከየአንካራ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 45 ኪሎሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው የአታ ቱርክ ቤተ መዘክር ተጉዘው ቤተ መዘክሩ ጐብኝተዋል።
አታ ቱርክ የረፓብሊክ ቱርክ መስራች እና የሀገሪቱ የመጀመርያ ፕረሲዳንት እንደሆኑ እንደ ኤውሮጳአቆጣጠር ከ1923 እስከ 1938 ቱርክን የመሩ መሆናቸው ይታወቃል። ከአታ ቱርክ በፊት ቱርክ በኦትማን አገዛዝ ስር መኖርዋ የሚታወስ ሲሆን ዘመናዊ እና ዓለማዊ ምህደራ ያስተዋወቁ ስማቸው እንደሚያምለክተው የቱርክ አባት ናቸው ።ይሁን እና ቅድስነታቸው አታ ቱርክ ቤተ መዘክር እንደ ደረሱ የቤተ መዘክሩ የበላይ ሐላፊዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል።እሳቸውም በቤተ መዘክሩ ጉንጉን አበባ አስቀጠዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከአታ ቱርክ ቤተ መዘክር ስምንት ኪሎሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው የፕረሲዳንት አዳራሽ የተጓዙ ሲሆን የሀገሪቱ ፕረሲዳንት ረሰፕ ኤርዶጋን እና የምነግስት ከፍተኛ ባላስልጣኖች አቀባበል አድርግውላቸዋል የቅድስት መንበር እና የቱርክ ብሔራዊ መዝሙር ከተሰማ በኃላ ፕረሲዳንት ረሰፕ ኦርዶጋን የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል።በቤተ መንግስቱ ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ከፕረሲዳንቱ እና ከየቱርክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አህመት ዳቩቶግሉ ጋር ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከየቱርክ መንግስት ባለ ስልጣናት ፕረሲዳንት ረሰፕ ኤርዶጋን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አህመት ዳቩቶግሉን ተሰናብተው ዲያነት ተብሎ ወደ ሚጠራው የሀገሪቱ የሃይማኖት ጉዳይ ተቋም ተጉዘዋል። እዚያው እንደደረሱ የዲያነት ፕረስዳንት ፕሮፈሶር መህመት ጎርመዝ እና የተቋሙ የበላይ ሐላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።ዲያነት የእስላም የሃይማኖት ከፍተኛ ተቋም እንደሆነ እና የቱርክ ህዝብ በመቶ 98 የእስላም ሃይማኖት እንደሚከተል እስልምና ግን የመንግስት ሃይማኖት እንዳልሆነ ይታወቃል።ከአታ ቱርክ በፊት የሸሪዓ ሚኒስቴር መኖሩ የሚታወስ ሲሆን ዲያነት የሃይማኖት ከፍተኛ ተቋሙ በአታ ቱርክ በ1924 እንደ ኤውሮጳ አቆጣጠር መመስረቱ ተመልክተዋል።
ይሁን እና የዲያነት ፕረሲዳንት እና የአስላም ሃይማኖት ባለስልጣናት እንዲሁም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ተከታዮቻቸው ተቋሙ ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ተቀምጠዋል የዲያነት ፕረሲዳንት ፕሮፈሶር መህመት ጎርመጽ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል። ቅድስነታቸውም ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነዋል። በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቱርክ የእስላም ሃይማኖት የበላይ ተቋም አውራ ሐላፊ ጋር በግል ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከየቱርክ የእስላም ሃይማኖት ከፍተኛ ተቋም የባለይ ሐላፊ ከፕሮፈሶር መህመት ጎርመጽ እና የተቋሙ ባለ ስልጣናት ተሰናብተው በርእሰ ከተማ አንካራ ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ቤተ ጵጵስና ተጉዘዋል ።በግል ለእራት ቀርበው ሌሊቱ እዝያው እንደሚያስላፉ ተመልክተዋል። ነገ በቱርክ የጀመሩትን ሐዋርያዊ ዕደት በመቀጠል ቅዳሜ 29 ቀን እኤአ በጥዋቱ ከአንካራ ተነስተው ወደ ኢስጣምቡል ይበራሉ ። ኢስጣምቡል ከተማ ከርእሰ ከተማ አንካራ 450 ኪሎ ሜትር ርቃ ትገኛለች ፡ ኢስጣምቡል በኤስያ እና ኤውሮጳ ክፍለ ዓለሞች መካከል እንደምትገኝ







All the contents on this site are copyrighted ©.