2014-11-26 16:41:21

ር.ሊ.ቃ.ጳጳሳት ፍራንሲስ የኤውሮጳ ፓርላማ እና ምክር ቤት ጐብንተዋል ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በየኤውሮጳ ፓርላማ ፕረሲዳንት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ትናትና በፈረንሳ ስትራስበርግ ከተማ ላይ የሚገኙ የኤውሮጳ ፓርላማ እና የኤውሮጳ ምክር ቤት ይፋ ጐብኝተዋል።ይህ ትናትና በስትራስበርግ ያደረጉት አጭር ጉብኝት አምስተኛ ሀገራት አቀፍ ዑደት መሆኑ ይታወሳል ።ይሁን እና ቅድስነታቸው ትናንትና ጥዋት ወደ ስትራስበርግ ተጉዘው መጀመርያ የኤውሮጳ ፓርላማ የጐበኙ ሲሆን ፓርላማው እንደደረሱ የፓርላማው ፕረሲዳንት ማርቲን ሹልጽ እና የፓርልማው አባላት ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል።ቅድስነታቸው ለኤውሮጳ አባላት ባድረጉት ንግግር ኤውሮጳ የህዝቦች ቤተ ሰብ መሆንዋ እና ህዝቦችን የመንከባከብ እና ሰብአዊ ክብራቸው የመጠበቅ ሐላፊነት እንዳላት አመልክተው ሰው እንደ ሰው እንጂ እንደ የኤኮኖሚ ባለበት መታያት እንደሌለበት አስገንዝበዋል። ኤውሮጳ ነፍስዋ መልሳ ካገኘች የሰብአዊነት ማእከል እና መጣቀሻ ትሆናለች በዚህም የሰው ልጅ ግርማ ክብር የመጠበቅ መሪነትዋ መልሳ ትያዛለች ብለው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቀደምት የኤውሮጳ አባቶች የሰው ልጅ ክብር እና የትብብር እሴቶች ቀዳምነት መስጠታቸው አስታውሰዋል።በማያያዝ የሐሳብ መግለጽ ነፃናት እምነትን የመከተል እንቅፋት ካለ የሰው ክብር እና ግርማ አለ ብሎ መናገር አዳጋች እንደሆነ ባሰሙት ንግግር አመልክተዋል።ለምሳሌ በአንድ ሰው መድልዎ የሚፈጸም ከሆነ ወይም የዕለት ምግብ የማያገኝ ከሆነ የሰው ክብር ተጣሰ ማለት ነው በማለት ቅድስነታቸው በማያያዝ ተናግረዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ በፍረንሳ ስትራስበርግ ላይ በሚገኘው የኤውሮጳ ፓርላማ ተገኝተው ለፓርላማው አባላት ባሰሙት ንግግር ሰብአዊ ክብር ሲነሳ ሰውን ግዑዝ ሳይሆን የሰው ፍጥረት መሆኑ እና ሰብአዊ ክብሩ የማይጣስ መሆኑ እና መጣስ እንደሌለበት ማለት እንደሆነ አስገንዝበዋል።በአሁኑ ወቅት ኤውሮጳ ውስጥ ብቸኝነት የኤኮኖሚ ቀውስ ድኽነት ስደተኞች በጉልህ እንደሚታይ ጠቅሰው ይህ ሆኖ ግን የኤውሮጳ ፖሊቲከኞች ስለ ተክኒካዊ እና ኤኮኖሚካዊ ጉዳዮች ሲናገሩ ይስተዋላሉ ግን ስለ ሥነ ሰብእ ሰብአዊ ጉዳዮች ማእከል ያደረገ ርእሰ ጉዳይ ለማየት አጋግች የሆነበት ግዜ እንደሆነ ገልጠዋል። ስራ አጥነት የስደተኞች ጉዳይ የአከባቢ ጥበቃ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች መሆናቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመያያዝ ለኤውሮጳ ፓርላማ አባላት ባሰሙት ንግግር አስገንበዋል።ክርስትና እና ኤውሮጳ የሁለት ሺ ዓመት ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱ ቅድስነታቸው ክርስትና የክፍለ ዓለሚቱ ማሕበራዊ ባህል እሴት መሆኑ ጠቅሰው ክክርስትና መራቅ አይገባም ብለዋል። ክርስትና ለኤውሮጳ እድገት እና መጻኢ ግዜ መስረት እንደሆነም በማያያዝ ገልጠዋል።የክርስትና ሃይማኖት በይኤውሮጳ ዓለማዊ ምህደራ ወይም በየኤውሮጳ ተቋማት ነፃነት የሚያሳርፈው አሉታዊ ተጽዕኖ የለም ሞራላዊ ሀብት ይሰጣል እንጂ በማለት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አስገንበዋል። የኤውሮጳ ሀገራት ሕግ አውጪዎች የክፍለ ዓለሚቱ ህዝቦች በሰላም እና በመተባበር የሚኖሩበት የኤውሮጳ ማንነት ጎልቶ የሚታይበት የኤውሮጳ መልካም መንፈስ አዳሽ የሕግ አውታሮች እንዲዘረጉ ጠይቀዋል ። በዚህም ንግግራቸው አጠቃልለዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና የኤውሮጳ ፓርላማ ብቻ ሳይሆን የኤውሮጳ ምክር ቤትም የጐበኙ ሲሆን ፡ የምክር ቤቱ አዳራሽ እንደደረሱ የምክር ቤቱ ፕረሲዳንት ያግላንድ እና የምክር ቤቱ አባላት ሙቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነው ለምክር ቤቱ አባላት ባሰሙት ንግግር መጻኢ እና ዓለም አቀፍ ሰላም ለማነጽ ኤውሮጳ ምንጭዋ ዳግም ማግኘት አለባት ምክር ቤቱ እውነትን ለማወቅ መሰማራት አለበት ሐቅ ከሌለ በሽተኛ ዲሞክራሲ ይናራል ይህም አለም አቀፍ ግድ የለሽነት ያስከትላል ካሉ በኃላ ቤተ ክርስትያን የጦር መሳርያ እና የሰዎች ዝውውር እንዲገታ አቤት ካለች ግዜ መቆጠሩ አስታውሰዋል።ጤናማ ነፃ እና ሰብአዊ ሕብረተ ሰብ እውን ለማድረግ የሕብረት ሰቡ ምንጭ እና እሴቶች ገቢራዊ ማደረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በአሁኑ ግዜ ኤውሮጳ ባለፈ ታሪክዋ እና በአሁኑ ወቅት ባለው ቀውስ የቆሰለች ቀድሞ የበራትን ኀይል ያጠፋች የተዳከመች ኤውሮጳ እንደምትታይ ያመለከቱ ቅድስነታቸው ኤውሮጳ በአዲስ መንፈስ ትነሳ ዘንድ አሳስበዋል።ለኤውሮጳ ያ ኀይልሽ ያ መልካም ታሪኽሽ የሐቅ ጥማትሽ የት ገባ ብሎ መጠየቅ ይቻላል ብለው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀድሞ እሴቶችሽ የቀድሞ መሰረታዊ የሆነ የትብብር የማስተዋል ክርስትያናዊ ምንጪሽ መልሺ ሊባል ይቻላል ብለዋል ለኤውሮጳ ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር ።በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በዓለም እና ኤውሮጳ ውስጥ ሰላም እየደበዘዘች በግጭት እና በሽብረተኛነት ንጹሐን ሰዎች ሕይወታቸው ሲጠፋ ይስተዋላል ካሉ በኃላ ኤውሮጳ ለሰላም ትቆም ዘንዳ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።በእጅጉ የሚያሳዝነው የሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር ዘመናዊ ባርነት ተከስቶ ይታያል ይህ ለምሳሌ መገታት ያለበት አሳዛኝ እና አሳፋሪ ተግባር መገታት ያለበት ሰው እንደ ቁሳቁስ የሚቆጠርበት ሰብአዊ ፍጡር በሌላ ሰብአዊ ፍጥረት ላይ ከፍተኛ ዓመጽ የሚፈጸምበት አሳዛኝ ተግባር መሆኑም አውስተዋል።
የጦር መሳርያ እሽቅድድም እንዲገታ ቤተ ክርስትያን ከርጂም ግዜ በፊት አቤት ማለትዋ እና ይህ ራሱ በድሀ ሕብረት ሰቦች ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ከባድ እንደሆነ አመልክተዋል።
ሰላም ለማነጽ ከባድ ቢሆንም ሰላም አልባ መኖር ግን ቀጣይ ስቃይ እንደሆነ ቅድስነታቸው በማያያዝ አስገንዝበዋል።ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የኤውሮጳ ምክር ቤር በየሰው መብት ጥበቃ ማሕበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና በተመሳሳይ ርእሰ ጉዳዮች ተባብረው ለመስራት እንደሚችሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አመልክተዋል።ኤውርጳ ውስጥ በጣም ብዙ ድሆች እንደሚኖሩ እና ሰብአዊ ክብራቸው እንዲመለስላቸው የምክር ቤቱ አባላት ያለሰለሰ ጥረት እንድያካሄዱ ተማጽነው ንግግራቸው አጠቃልለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.