2014-11-24 16:22:45

እ.ኤ.አ. የ 2014 ዓ.ም. የጆሴፍ ራትንዚንገር ሽልማት


ሁሌ በየዓመት በቲዮሎጊያዊ የሥነ ምርምር ጥናት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የሚሰጠው ጆሴፍ ራትዚንገር የተሰየመው ሽልማት ይኸው የዘንድሮው እ.ኤ.አ. የ 2014 ዓ.ም. የሽልማት ያሰጣጥ ሥነ ሥርዓት በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንፃ በሚገኘው ቅዱስ ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. መከናወኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ ገለጡ።
የእኚህ የቲዮሎጊያ ሞዛርት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. የ 2014 ዓ.ም. ሽልማት በፈረንሳይ የቅዱስ መጽሓፍ ሥነ ትንተናን ሥነ አገረጓጐም ሊቅ ፕሮፈሰር ኣነ ማሪያ ፐለቲየርና ለፖላንድ ተወላጅ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ በዚሁ የምርምር ዘርፍ አስተማሪ በካቶሊክና በአይሁድ እምነት መካከል በሚደረገው የጋራው ውይይት ንቁ ተሳታፊ ለሆኑት ለብፁዕ አቡነ ዋልደማር ክሮስቶቪስኪ መሰጠቱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ባርቢ አክለው፦ በተካሄደው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወክለው የተገኙት የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ገራሃርድ ልድዊግ ሚዩለር መሆናቸው ገልጠው፣ የዚህ የጆሰፍ ራትዚንገር ማኅበር ሊቀ መንበር የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልሂቅ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ የተሸላሚዎች የሥነ ምርምር ውጤትና እያካሄዱት ያለው ተክለ ምርምር ርእስ ዙሪያ ንግግር ማስደመጣቸው ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.