2014-11-24 16:09:49

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የሰው ልጅ ማኅበራዊ-ተገናኝ ባህርይ በሚያዛባ በሽታ ለሚሰቃው ቅርብ መሆን


እ.ኤ.አ. ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የጤናና የጤና ባለ ሙያዎች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሰው ልጅ ማኅበራዊ-ተገናኝ ባህርዩ የሚያዛባው በሽታና ታማሚው፦ ተስፋን ማነቃቃት” በሚል ርእስ ዙሪያ ሊወያይ የጠራው 29ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በዚህ በሽታ የተጠቁት ሕፃናት በቤተሰቦቻቸው ተሸኝተው በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በመገናኘት የጸሎት የመዝሙር የተለያዩ መንፈሳዊ መግለጫዎች ቀርቦ ቅዱስነታቸው በለገሱት መሪ ቃል መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
የሰውል ልጅ ማህበራዊ-ተገናኝ ባህርይ በሚያዛባው በሽታ የተጠቃ ዜጋ ለሚኖርበት ቤተሰብና ኅብረተሰብ ቅንዋትና እንዲሁም ታማሚው የሚገኝበት ቤተሰብ ለብቻው ተትዎ እንደሚኖርና ይኽ አይነቱ ታማሚው የሚገኝበት ቤተሰብ የመነጠሉ ተግባር በማስወገድ ለታመመው ድጋፍ ለቤተሰቡ ትብብርና ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ምዕዳን ገልጠው መንግሥታትና የህክምና ተቋማት ለዚህ ተግባር እንዲተጉ ጥሪ በማቅረብ፦ “ለታማሚው የተሟላ በተለይ ደግሞ ተስፋ ኅያው በሚያደርግ መስተንግዶ ድጋፍ በማቅረቡ ረገድ ሁሉም መትጋት ይኖርበታል፣ ይኽ ድጋፍ እነዚያ በበሽታው የተጠቁት ለብቻቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ለብቻቸው ነጥሎ መኖር የሚታየው ሁኔታ በእውነቱ ለታማሚውና ታማሚው ለሚገኝበት ቤተሰብ ቅንዋት ነው፣ ስለዚህ ታማሚው መልከአ ሞት አድርጎ የመመልከቱ ጨካኝ ድርጊት አደራ ይወገድ” ያሉት ቅዱስ አባታችን በሽታው መስቀል በማለት ገልጠው በሽታው እንደ ሁሉም የተለያዩ በሽታዎች ተገቢ እውቅና ያገኘ ቢሆንም ቅሉ በሽታው ለመፈወስ ጥረት ማረግ ብቻ ሳይሆን ታማሚው የሚገኝባቸው ቤተሰቦች አለ ምንም ሃፍረት ወይንም በገዛ እራስ ከመዘጋት ፈተና እንዲላቀቁና የሁሉም በተለይ ደግሞ የማኅበረ ክርስቲያን ቅርበትና ደጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ሲያሳስቡ፦ “በዚህ የሰው ልጅ ማኅበራዊ-ተገናኝ ባህርዩ የሚያዛባው በሽታ የተጠቃውን ለመደገፍ በሁሉም አካባቢ ድራዊ ግኑኝነት ማለትም ታማሚው በሚገኝባቸው ቤተሰቦች መካከል ከዛም ሁሉም ድጋፍና ትብብር በመስጠት የሚሳተፉበት እንዲሁም በሰበካዎችና ቁምስናዎች በበሽታው ለተጠቁትና ለቤተሰቦቻቸው ልዩ ትኵረት የሚሰጥ የተገባ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት መወጠን ወሳኝ ነው። እንዲህ ባለ አቀራረብና ትብብር ብዙዉን ጊዜ በበሽታው የተጠቃው ሰው የሚገኝባቸው ቤተሰቦች ታማሚውን ተገቢ ድጋፍ ለማቅረብ ብቃት የሌላቸው የሚሰጡት አገልግሎት ስኬታማነት የሌለው እንደሆነ ተሰምቷቸው ለባቻቸው ተነጥለው ለመኖር የሚገፋፋቸው ፈተና ለማሸነፍ ያግዛቸዋል። የቤተ ክርስቲያን የመንግሥት ተቋማት ቅርበትና ትብብር እንዳይለያቸው አደራ” እንዳሉ የቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.