2014-11-24 16:19:40

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የመላ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች የግልና የውህደት ህዳሴነትና የነጻነት ትእምርት ናቸው


የመላ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች በጋራ ለበሰለው ቤተ ክርስቲያናዊነት መንፈስ በሚል ሓሳብ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት “ወንጌል ኃሴት የወንጌላዊ ልኡክነት ኃሴት ነው” በሚል መርህ ቃል ያሰናዳው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የመላ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በጳጳሳዊ የቤተ ክርስቲያን እናት ቅድስት ማርያም መንበረ ጥበብ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።
ይኽ እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጠናቀቀው ዓውደ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት በደረሱት ሐዋርያዊ መልእክት አማካኝነት ደጋግመው ያሳሰቡት ወንጌላዊ ኃሴት ወንጌል በማበሰር መሆኑና ግምት ሰጥቶ ይኽ ተእlኮ በአሁኑ ወቅት የሚጋረጠው መሰናክል ሁሉ ለመለየት የመከረ ዓውደ ጉባኤ እንደነበር የገለጡት የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አክለው፣ በአውደ ጉባኤው በብዙ መቶዎች የሚቆጠጡሩ ከተለያዩ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች የተወጣጡ አምስቱን ክፍለ ዓለም የሚወከሉ በጠቅላላ 350 ልኡካን መሳተፋቸውና ቀዳሚው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. ሁለተኛውም እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. መካሄዱ አስታውሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተጋባእያኑን ተቀብለው፦ “ካቶሊካውያን እንቅስቃሴዎችና ማኅበራት ተነጣጥለው የሚከተሉት ዘይቤና ስርዓት ብቻ የሚንከባከቡ ከሆነ ከሁሉም ተነጥለውና ርቀው ከተጨባጩ ዓለም ተገለው የተቀበሉት መንፈሳዊ ዓላማ ርእዮተ ዓለም ሆኖ ነው የሚቀረው፣ ስለዚህ ለመንፈስ ቅዱስ ህዳሴ የተዘጉ የተቀበሉት እንዲቋቋሙ ያደረጋቸው መንፈሳዊ ዓላማ የሚያፍኑ ሆነው ነው የሚቀሩት፣ ስለዚህ በዓለም የሚያጋጥመው ተጋርጦ ተጋፍጠው ለማሸነፍ መሠረት ወደ ሆናቸው መንፈሳዊ መርሆ መለስ ብለው ታድሰው ለተቀበሉት ዓላማ መስካሪያን ሆነው መገኘት አለባቸው” እንዳሉ ዶኒኒ ገለጡ።
“ዘወትር ተጓዦች በመንገድ የሚገኙ የሚንቀሳቀሱ እግዚአብሔር ለሚያቀርበው ህዳሴ ክፍት የሆኑ በመስራቾች አማካኝነት እግዚአብሔር ለሰጠው መንፍሳዊ ዓላማ ታማኞች በመሆን ከዓላማው ጋር በመስማማት የሚኖሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል። እግዚአብሔር በትእግስቱ የሰውን ልጅ ይጠባበቃል፣ ትዕግስት ወደ ፍቅር የሚመራ መንገድ ነው። ጌታ ስለ ሚያፈቅረን ታግሶናል፣ ስለዚህ ክርስቲያናዊ ሕንጸት ይኸንን ትዕግስት ይጠይቃል። የእያንዳንዱ ጊዜ መጠበቅ የሚያውቅ ትእግስት ነው” ብለው፦ “ቤተ ክርስቲያናዊ ብስለት ለመቀዳጀት የተቀበላችሁት መንፈሳዊ ዓላማ ያለው ትኵስ መንፈሱን እትዘንጉ፣ የሌላው ነጻነተ አክብሩ ዘወትር ውህደትና ሱታፌ ፈልጉ። ውዶቼ ከእኔ ጋር አብራችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ተመጻኑ፣ እርሷ ከጌታ ጋር በመገናኘት ያሳየቸው ትህትና ዘወትር ልክ እንደተቀበለቸው በነበረው ስሜትና መንፈስ እንደኖረች ሁሉ የእርሷን አብነት በመከተል የሌላው ነጻነት በማክበር በትህትና እንጓዝ፣ ወንጌላዊ ልኡክነት ጥሪ አንዘንጋ” ብለው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.