2014-11-24 16:14:54

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ በወንጌል አማካኝነት ዓለም የመለወጡ ዓላማችሁ አደራ እንዳይሰረቅ


በሮማ አቅራቢያ በምትገኘው በሳክሮፋኖ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ብሔራው የወንጌላዊ ልኡክነት ዓውደ ጉባኤ ተሳታፍያን እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ተቀብለው፦ “ዓለምን በወንጌል የመለወጥ ጥልቅና አቢይ አላማችሁ አደራ እንዳይሰረቅ” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
ቤተ ክርስቲያን ወደ ተጨቆኑት ድኾች ተነጥለው ወደ ሚኖሩት ወደ ተናቁት ለማለት ከገዛ እራስዋ ለመውጣት የተጠራችና ለሁሉም ከሁሉም ጋር በመገናኘት የወንጌል ሃሴት ለማበሰር የተጠራች መሆንዋ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስደመጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን አበክረው፣ ወንጌላዊ ልኡክነት ለተወሰኑ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ክርስቲያን ጥሪና ኃላፊነት ነው። ስለዚህ ተልእኮው ሊያስፈራን አይገባም ምክንያቱም ታሪክን የእያንዳንዱን የአሕዛብ ታሪክ የሚለውጠው ሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት ነው። ከጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ክፍል በመጀመር በወንጌል እርሾ ዓለምን ለመለወጥ ያለው ጥልቅ ዓላማችሁ አደራ እንዳይሰረቅ፣ ከገዛ እራስ ወጥቶ ከሌላው ጋር ለመገናኘት ማለት የእግዚአብሔር ምህረትና አጽናኝ የተስፋ ቃል ከእኛ ለሚጠባበቁት መርሳት ከሚለው ፈተና መላቀቅ ማለት ነው” የኢየሱስ ወንጌል በታሪክ የሚከወን መሆኑና ኢየሱስ የጥጋ ጥግ ክፍለ ከተማ ዜጋ ነው። በዘመኑ ከሮማውያን ግዛት ይተዳደር ከነበረው ክልልና ከኢየሩሳሌልም ውጭ ከምትገኘው ከገሊላ ከተማ የመጣ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስታወስም፦ “ድኾች የታመሙት የሰይጣን መንፈስ ያደረባቸው ኃጢአተኞች ቀራጮችን ሴቶችና ወንዶች ሁሉ በዙሪያው በመጥራት ወደ ዓለም አንድ አዲስ መፍነሳዊና ሰብአዊ አብዮት በማስተዋወቅ፣ ይኽ አዲስ አብዮትም የሞቱና የትንሣኤው ብስራት ነው። ሞቱና ትንሣኤው ለእኛ ነው። ስለዚህ ይኽ ዓለምና ሰውን የሚለውጠው አዲስ ወንጌላዊ አብዮት ከሌሎች ጋር ልናካፍለው የተጠራን ነን” በመሆኑም በሚያጋጥምና ሊያጋጥም በሚችለው ፈተና መደናገጥ አንዳያጋጥም ሲያሳስቡ፦ “ጨለምተኝነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል ፈተና ነው። ይኽ ደግሞ ወንጌል ለሁሉም የማበሰሩ ዓላማ ግቡ ይመታል ብሎ ለማመን የመጠራጠርን ፈተና በቤተ ክርስቲያን ሊያጋጥም ይችላል፣ በተስፋ አደራ ወደ ፊት እንበል፣ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የእምነት ሰማእታት ልኡካነ ወንጌል እምነታቸው በሚሰዋ የፍቅር አገልግሎት አማካኝነት ፍቅር እሸናፊ መሆኑ የሚያረጋግጥ፣ ሕይወት ስለ ጌታና ስለ ወንድሞች ስለ ድኾች አሳልፎ መስጠት ለሚለው ፍቅር የላቀ የቃልና የሕይወት ምስክርነት ነው” ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ከገዛ እራስዋ ወጥታ ከሰው ጋር ለመገናኘት ለምትጓዘው ቤተ ክርስቲያን ሸኝ የጉዞ ጓደኞች መሆናቸውም ሲያብራሩ፦ “ከገዛ እራስ መውጣት፣ ከቸልተኝት ከከፋው ድኽህነት ከጦርነት ከአመጽ፣ በእድሜ የገፉትን ከመርሳቱ ተግባር ሌላውን ከማግለሉ ተግባር መላቀቅ። አዎ ይኽ ነው እውነተኛው ከገዛ እራስ መውጣት፣ ክርስቲያን በሆኑት ከተሞቻችን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕጻናት ትእምርተ መስቅል ጨርሰው የማያውቁ የሚገኙበት ሆኖዋል። ይኸንን ቸል የማለቱ ተለማምዶ የመኖሩ ድርጊት እናስወግድ” ከገዛ እራስ መውጣት ማለት የዚያ ዕለት በዕለት ጌታ ለሚጸግወን ሰላም መሣሪያ መሆን ሲያዝገነዝቡ፦ “ልኡካነ ወንጌል ሰላምን የመመኘቱና ሰላምን የማለሙ ተግባር የሚዘነጉ አይደለም፣ ዕለት በዕለት በሚያጋጥማቸው ችግር መከራ በእያንዳንድዋ ሰዓት የሰላም መሣሪያ መሆናቸው የሚዘነጉ አይደሉም። ባለፈው ሳምነት ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡት ብፁዓን ጳጳሳት ቆሞሶች ካህናት ጋር ተገናኝቻለሁ፣ እነዚህ ውጥረትና አመጽ ከተከናነባው ክልል የመጡት አገልጋዮች በእውነቱ ያሳዩኝ ደስታ፣ በቃልና በሕይወት የመሰክሩት ወንጌላዊ ሃሴት መስካሪያን ከመሆናቸው የመነጨ ነው። ስቃይና መከራ በሚፈራረቅበት ክልል የሚኖር ደስታ ከወንጌል የሚመነጭ ካልሆነ በእውነቱ የሚቻል አይደለም” ካሉ በኋላ የኢጣሊያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ይህች ቤተ ክርስቲያን ለምትሰጠው ካህናት ደናግል ልኡካነ ወንጌል ምክንያት ሁሉ አመስግነው፦ “ጌታ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ የልኡካነ ወንጌል ፍቅር ያቀጣጥል፣ በሁሉም ስድፍራ ፍቅሩና ምህረት እንዲደርስ ለሚያደርግ ወንጌላዊ ልኡክነት ፍቅር ቀናተኞች ያድርገን” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ያስደመጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.