2014-11-19 17:13:33

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ካቀረበልን ስጦታዎች አንዱና ትልቁ ቤተ ክርስትያን በኅብረት የተመሠረተችና በሥልጣንና ውረድ ተዋረድ የምትደታደር መሆንዋን ነው፣ ይህም የተጠመቁ ክርስትያኖች ሁላቸው በጌታ ፊት እኩል መብታ እንዳላቸውና በተመሳሳይ ጥሪ እና ለቅድስና በመወሰናቸው አንድ ማኅበር ያቆሙ መሆናቸውን እንገነዘባለን (ብርሃነ አሕዛብ ቍ.39-42 ተመልከት)፣ ወደገዛ ራሳችን መለስ ብለን ይህ ማኅበራዊ የቅድስና ጥሪ እንዴት ይቆማል? እንዴት እውን ሊሆን ይችላል? ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ፤
ከሁሉ አስቀድመን ቅድስና እኛ በምግባራችን ወይንም በችሎታችን የምናገኘው አለመሆኑን ነው፣ ቅድስና ስጦታ ነው፣ ይህንን ስጦታ ጌታ ኢየሱስ ወደገዛራሱ በሚያቀርበንና እንደእርሱ እንድንሆን በጠራን ጊዜ ይሰጠናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌውሶን ሰዎች ሲጽፍ “ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት…. በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤”(5፡25-26) በማለት ይህንን እውነት ያረጋግጥልናል፣ ስለዚህ ቅድስና የቤተ ክርስትያን እጅግ ደስ የሚያሰኝ ገጽታ ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ሆኖ በሕይወቱ መሳተፍና በፍቅሩ መታቀፍ ምንኛ ያህል ደስ ያሰኛል፣ በዚህም ቅድስና የአንዳንድ የተመረጡ ወይንም የተለዩ ሰዎች ብቻ የተወሰነ አለመሆኑና ከዚህ ጥሪ የሚገለል ማንም እንደሌለ በመገንዘብ የእያንዳንዱ ክርስትያን ልዩ ምልክት መሆኑን እንገነዘባለን፣ ይህንም የሚያስረዳን ቅዱሳን ለመሆን ጳጳስ ወይንም ካህን ወይንም ውሉደ ክህነት መሆን የግድ አለመሆኑን ነው፣ ሁላችን ቅዱሳን ለመሆን የተጠራን ነን፣ አብዛኛውን ጊዜ ለቅድስና የተጠሩና ቅዱሳን የሚሆኑ በሁለመናቸው ለጸሎት እንዲያገልግሉ ከዚህ ዓለም ኑሮ የተለዩ መናንያን አድርገን እንገምታለን፣ ነገር ግን ይህ ስሕተት ነው፣ ምናልባትም ቅድስና ዓይንን ጨፍኖ ሌላውን ሁሉ ትቶ የሚታሰብ የሚመስላቸው አይጠፉም፣ ቅድስና ግን እንደዚህ አይደለም፣ ቅድስና እግዚአብሔር የሚሰጠን እጅግ የላቀና ጥልቅ የሆነ ጸጋ ነው፣ እንዲያው በዚሁ አስተያየት አንጻር ዕለታዊ ኑሮአችን ስናካሄድ በፍቅር የኖርንና በቅድስና ለመኖር የተጠራን መሆናችንን ለማሳየት ክርስትያናዊ ምስክርነታችን የሰጠን እንደሆነ የቅድስና ሕይወትን መጀመር እንችላለን፣ ይህንም እያንዳንዳችን በምንገኝበት የሕይወት ጥሪና በምንኖርበት የሕይወት መላ መሆን አለበት፣ ስለዚህ አንተ ለምንኵስና የተጥራህ ሕይወትህን በሚገባ በመኖር ቅዱስ ሁን! አንተ ለትዳር የተጥራህም ክርስቶስ ለቤተ ክርስትያኑ እንዳደረገላት ባለቤትህን በማፍቀርና በመንከባከብ የቅድስና ኑሮ አዘውትር፣ የተጠመቅህና ያላገባህ የሆንክ እንደሆነ ደግሞ ሥራህን በሚገባ በቅንነት እያከናወንክ ለጓደኞችህ አገልግሎት አውለው፣ ምናልባት ከእናንተ መካከል አባ እኔ በአንድ ፋብሪካ እሰራለሁ ወይንም በአንድ ሒሳብ ክፍል እሰራለሁ በእነዚህ አከባቢ መኪናዎችና ቍጥሮች እንጂ ጓደኞች አላይም እንዴት አድርጌ ራሴን መቀደስ እችላለሁ በማለት ሊጠይቀኝ ይችላል፣ እውነት ነው ግን እንዲህ ባሉ የሥራ ቦታዎች ቅዱስ ለመሆን ይቻላል፣ እግዚአብሔር እንድትቀደስ ጸጋውን ይሰጠሃል፣ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ሊወያይ ይችላል፣ ካንተ የሚያስፈልገው ለዚህ የእግዚአብሔር ጥሪ ልብህን መክፈት ብቻ ነው፣ እንደዚሁም ልክ ለወላጆችና ለአያቶችም ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው በታላቅ ፍቅር ትምህርተ ክርስቶስን በማስተማርና ጌታ ኢየሱስ እንዲከተሉ በማድረግ ሊቀደሱ ይችላሉ፣ ይህንን ለማድረግ ግን ታላቅ ት ዕግሥት ይጠይቃል፤ በተለይ መልካም ወላጆች መልካም አያቶች ለመሆን ታላቅ ትዕግሥት ያስፈልጋል በዚህም ትዕግሥት የቅድስና ዋና መሣርያ ነው፣ የትምህርተ ክርስቶስ መምህር ወይንም አስተማሪ ወይንም በነጻ ፍላጎት የምትሰራ ከሆንክም ልክ እንደዚሁ የምታደርገውን ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅርና የእርሱ ከእኛ ጋር መሆኑን የምታሳይ ተጨባጭ ምስክር በመሆን የቅድስናን ጐዳና መከተል ይቻላል፣ መንገዱ ብዙ ት ዕግሥት የሚጠይቅ ስለሆንም ተስፋ መቍረጥ የለባችሁም፣
እዚህ ላይ እያንዳንዳችን የኅልና መርመራ ማድረግ አለብን አሁኑኑ ጸጥ ብለን ኅልናችንን እንመርምር፤ መልሱንም ለገዛ ራሳችን ይሁን! ጌታ ላቀረበልን የቅድስና ጥሪ እስካሁን ምን ዓይነት መልስ ሰጥተናል? በዚሁ የቅድስና መንገድ ልገሰገስ ትንሽ ለመሻሻል እሻለሁን? ጌታ ለቅድስና ሲጠራን ለከባድ ነገር ሳይሆን ደስ ለሚያሰኝና በቀላሉ ምንም ሳንጨነቅ ለማድረግ የምንችለውን ነው የሚጠይቀን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.