2014-11-12 19:25:02

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ባለፈው ትምህርተ ክርስቶስ ጌታ ኢየሱስ የሕዝበ እግዚአብሔርን እረኝነት ጳጳሳት በካህናትና ዲያቆናት እየተረዱ በሚያደርጉት ተልእኮአዊ አገልግሎት እንደሚያከናውኑት አይተናል፣ ጌታ ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእነዚሁ አማካኝነት በመካከላችን በመገኘት ቤተክርስትያን በእምነትና በተስፋ እየመገበ የፍቅር ምስክር እንድትሆን ያደርጋታል፣ የጌታ ኢየሱስ ህላዌና ፍቅር ምልክት ስለሆኑም እነኚህ አገልጋዮች ለማንኛው ማኅበረ ክርስትያንና ለመላዋ ቤተ ክርስትያን ታላቅ ስጦታ ናቸው፣
በዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ደግሞ እነኚህ የአገልግሎት መልእክተኞች ተልእኮአቸውን በሚገባ እንዲወጡና በእውነት እንዲኖሩት ምን ማድረግ አለባቸው ብለን እንጠይቃለን፣
ሓዋርያዊ መልእክቶች ፓስቶራል ለተርስ በማለት በሚታወቁት ቅ.ጳውሎስ ተከታዮቹ ለነበሩት ጢሞቴዎስና ቲቶስ በጻፋቸው መልእክቶች ጳጳሳት ካህናትና ድያቆናት ምን ማሟላት እንዳለባቸው እንዲሁም ም እመናን ሽማግሌዎችና ወጣቶች እንዴት መኖር እንዳለባቸው በሰፊው ይገልጣል፣ እያንዳንዱ ክርስትያን በቤተ ክርስትያን እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለልዩ ተልእኮና አገልግሎት ከተጠሩ ጳጳሳት ካህናትና ዲያቆናት እንዴት መመረጥ እንዳለባቸው ይገልጣል፣ በእምነትና በመንፈሳዊ ሕይወት መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ለመግለጥ ያህል በሰው ልጅ አመለካከት እንደ መልካም ጠባይ የሚቆጠሩትን ነገሮች፤ እንግዳ መቀበል ትዕግሥት ትሕትና ታማኝ መሆን ባለበጎ ልብና ፍላጎት መሆን በማለት ይዘረዝራል፣ እነኚህ የአገልግሎት ሀሁ ሆነው የእያንዳንዱ ተልእኮ መሠረታዊ ሰዋስው ናቸው፣ የእያንዳንዱ ጳጳስ ካህንና ዲያቆን መሠረትም መሆን አለባቸው፣ አለ እንዲህ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሰዎችን ተቀብሎ ማነጋገር ማወቅና መወያየት እንዲሁም ከወንድሞች ጋር መገናኘት እና ማድነቅ አይቻልም፣ መከባበርና ንጽሕና የለበሰ ግኑኘት ለመፍጠርም አይቻልም፣ ደስታ የሞላው እና ታማኝ ምስክርነት እና አገልግሎት መስጠትም ፈጽሞ የማይቻል ይሆናል፣
2. ቅዱስ ጳውሎስ ለተከታዮቹ አደራ ያለው እላይ ከጠቀስናቸው ጠለቅ ያለ ሌላ ነገርም አለ፣ ይህ ደግሞ ለሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ አገልግሎት ለተጠሩ ሁሉ ጳጳሳትም ይሁኑ ካህናት እንዲሁም ዲያቆናትን የሚመለከት ነው፣ ሓዋርያ ጳውሎስ “በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል” (1ጢሞ 4፡14. 2ጢሞ 1፤6) በማለት አደራ ይላል፣ የዚህ ትርጉም ደግሞ ጳጳሳት ይሁኑ ካህናት እንዲሁም ዲያቆናት ከሌሎች የበለጡና አዋቂዎች ሆነው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፍቅር የመነጨው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስጦታ መሆኑን ሁሌ ማስታወስ ያለባቸው ጉዳይ ነው፣ ይህም ለሕዝበ እግዚአብሔር በጎ ነገር ለማገልገል የሚሰጥ ጸጋ ነው፣ ይህንን ማወቅና ማስታወስ መሠረታዊ ነው ስለሆንም ይህንን ጸጋ በየዕለቱ መለመን ያስፈልጋል፣ የአገልግሎት ሥልጣኑ ከእግዚአብሔር ምሕረትና ልብ እንደሚመንጭ የሚያስታውስ እረኛ ሁላቸው በእግሩ ሥር ሆነው ማኅበሩም እንደየግሉ ንብረት በማሰብ ሥልጣኑን በአምባገነንነት ሊጠቀም ፈጽሞ አይችልም፣
ሁሉ ሥጦታና ጸጋ መሆኑን ማወቅ ለአንድ እረኛ ብዙ ይረዳዋል እንዲሁም የሁሉ ማእከል የመሆንና በገዛ ራስ ከመተማመን ፈተና እንዳይወድቅ ይረዳዋል፣ እነኚህ ፈተናዎች የከንቱነት የእብሪትና የትዕቢት ፈተናዎች ናቸው፣ ሁሉም የሚያውቅ ለሚመስለው ጳጳስም ይሁን ካህን ወይንም ዲያቆን ወዮለት! የጥያቄዎች ሁሉ ትክክለኛ መልስ የሚያውቅ ለሚመስለውና የሌሎች እርዳታ እንደማያስፈልገው ለሚገምትም ወዮለት! በተቃራኒው እርሱ ራሱ የመጀመርያ የእግዚአብሔር እርኅራኄና ምሕረት ተጠቃሚ በመሆን የቤተ ክርስትያን አገልግሎትን እንዲያራምድ የተጠራ መሆኑን አውቆ ዘወትር ትሑትና ከሌሎች ጋር የሚግባባ መሆን አለበት፣ እንዲሁም ጳውሎስ “የተሰጠህን አደራ ጠብቅ” (1ጢሞ 6፡20) እንደሚለው የእምነት መዝገብን በብርታት ለመጠበቅ የተጠራ ነው፣ ሕዝቡን ጸጥ ብሎ በትሕትና ያዳምጣል፣ ከሕዝቡ የሚማረው አንድ አዲስ ነገር እንዳለ ማስታወስ አለበት፣ ከእምነትና ከቤተ ክርስትያን ርቀው ከሚገኙም ሳይቀር ሊማር ይችላል፣ በክህነታዊ አገልግሎት ወንድሞቹ ከሆኑ ጋር ደግሞ አዲስ ዝንባሌ በመፍጠር ሁሉን የመከፋፈል በአንድነት ኃላፊነትን የመሸከም እንዲሁም የማኅበሩ አንድነትን መጠበቅ ያስፈልጋል፣
ውዶቼ! ጌታ በጳጳሳት በካህናትና በዲያቆናት አማካኝነት ቤተ ክርስትያኑን እየመራ እያነጸና በቅድስና ጐዳና እንድታድግ ስላደረጋት ጌታን ሁል ጊዜ ማመስገን አለብን! እንዲሁም በተመሳሳይ መንገድ የማኅበረክርስትያኖቻችን እረኞቻች የእግዚአብሔር አንድነትና ፍቅር ነጸብራቅ እንዲሆኑ ስለእነርሱ ዘወትር መጸለይ አለብን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.