2014-11-07 18:59:50

የክርስትያን መከፋፈል ወንጌልን ስለሚያበላሽ እናስወግደው!


RealAudioMP3 ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና የዓለም አቀፍ ወንጌላውያን ጥምረት አባላት በመንበራቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነበር፣ ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ያተኰሩበት በክርስትያኖች መካከል ያለው መከፋፈል የወንጌል የምሥራችን ጣዕምን እንደሚያበላሽ ሲሆን ካቶሊካውያንና ወንጌላውያን በመካከላቸው ያሉትን መለያየቶች አስወግደው ወንድማማችነትንና መተበባርን እንዲያዳብሩ በመማጠን “ቤተ ክርስትያን በክርስቶስ ውስጥና ከክርስቶስ ጋራ እንትሆን እናግዛት” ሲሉ አደራ ብለዋል፣
“በመካከላችን ያሉ መከፋፈሎች የጌታ ኢየሱስ አንድያ ንጹሕ ቀሚስን ያቆሽሻሉ ነገር ግን በተጠመቁ የክርስቶስ አካላት የሆኑ ክርስትያኖች መካከል ያለውን ጥልቅ አንድነት አይደመስሰውም፣ ክርስትያኖች በመካከላቸው ያለውን መከፋፈል ቢያወግዱና ምሥጢራትን በኅብረት ቢያስተዳደሩ እንዲሁም ምግባረ ሠናይን በመመስከር በኅብረት ቃለ እግዚአብሔርን ቢሰብኩ የክርስቶስ ወንጌል ስብከት በታላቅ ፍጥነትና ችሎታ በተሳካ ነበር፣ በማለት ምኞታቸውን ከገለጡ በኋላ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በካቶሊካውያንና ወንጌላውያን መካከል በሚደረገው መተባበርና ወንድማማችነት እንዳረካቸው አመልክተው በተለይ ደግሞ ስለክርስትያን አንድነት የሚያገለግል የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጳጳሳዊ ምክርና በዓለም አቀፉ የወንጌላውያን ጥምረት የሚካሄደውን ጥረት አመስግነዋል፣ ለወደፊት ያላቸውን እምነትና ምኞትም እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፣ መንፈስ ቅዱስ ኃያልና ቻይ በሆነው አስተንፍሶው እና በያዘችበት ፍጥነት ወደፊት ለመራመድ ብርታት እንዲኖራትና አዳዲስ የስብከተ ወንጌል መንገዶች እንድታፈላልግ እና በወንጌላውያንና በካቶሊካውያን መካከል አዲስ የግኑኝነት ደረጃ እንድትጨምር ይረዳት ዘንድ በቤተክርስያን መንፈስ ቅዱስ እንደሚወርድ እምነቴ ነው፣ በግብረሓዋርያት 1፡8 እንደተመለከተውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወንጌልን ስበኩ ብሎ ጌታ የገለጠውን ፍላጎት እውን ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ደረጃ እንዲሆነን እመኛለሁ፣ ሲሉ እምነታቸውና ምኞታቸውን ገልጠዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በተሰኘው የመገናኛ ብዙኃን መንገድ ደግሞ “አንድ ክርስትያን ነኝ ባይ የተቸገሩ ሰዎች ሲያይ ቸል የሚል ከሆነ ልትቅበለው የሚያስቸግር ነው” ሲሉ የተቸገሩትን መርዳት እንዳለብን የሚያሳስብ አጭር መልእክት ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.