2014-11-03 15:20:27

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በቅድስት መሬት


RealAudioMP3 በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉኣድ ትዋል ባቀረቡት ጥሪ መሠረት የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ከሦስቱ ምክትሎቻቸው ብፁዕ ካርዲናል ጓልቴሮ ባሰቲ ብፁዕዕ አቡነ ቸሳረ ኖሲሊያ፣ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ ስፒኒሎ እንዲሁም ከዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኑንዚዮ ጋላንቲኖ ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ቅድስት መሬት መሄዳቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የተመራው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልኡካን የጋዛ ሰርጥ ክልል፣ በክልሉ ባለው ግጭት ሳቢያ የወደመው አካባቢ በዮርዳኖስ የሕክምና መስጫ ማእከል በዚያ የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በሚተዳረው ትምህርት ቤት እንደሚጐበኙና በቅዱስ ፐርፊሪዮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አለክሳንድሮስ ጋር እንደሚገናኙም የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ልኡካኑ በቅድስት ቤተሰብ ቁምስና የክልሉ ምእመናን የሚሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉም ጠቁሞ እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ብዙ ጊዜ ከፍልስጤም ክልል ለሚለቀቀው ተምዘግዛጊ ሮኬት ዒላማ የሆነው የእስራኤል ስደሮት የተሰየመው ክልል እንደሚጎበኙ ያመለክታል።
የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲረጋገጥ የተለያዩ ጅምሮች በማከናወን ሰላምና ስለ ሰላም የሚደረገው ጥረት ሁሉ በመደገፍና ሰላም እንዲረጋገጥ መካከለኛው ምስራቅ ለሰላም ለማነቃቃት ታልሞ የሚያከናወን መሆኑ በቅርቡ በመካከለኛው ምስራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በኢራቅ የኩርድስታን ክልል የሚገኘው መጠለያ ሰፈር የጎበኙት ብፁዕ አቡነ ጋላንቲኖ እንዳሳወቁ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ፦ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲርጋገጥ በማኅበራዊና ሰብአዊ ዓላማ አማካኝነት በኢጣሊያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ክልል ሕዝብ በተለይ ደግሞ ለሚሰቃየው ለስደት ለሚዳረገው ቤቱንና ንብረቱን ጥሎ ለሚፈናቀለው ቅርብ መሆንዋ ለመመስከር ታልሞ የሚከናወን ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.