2014-11-03 15:08:07

የብፅዕና አዋጅ


RealAudioMP3 በስፐይን የእርስ በእርስ ጦርነት ተፋፍሞ በነረበት ወቅት የደም ሰማዕትነት የከፈሉት የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ፐድሮ ኣሱዋ የክላሪቲያኑም ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል መንዲያ ቅድስት ቤተ ክስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ አማካኝነት በስፐይን በባስኪ ክልል ቪቶሪያ ከተማ በሚገኘው በንጽሕት ድንግል ማርያም ካቴድራል የቅድስና ጉዳይ በሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ተክተው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅድስና ንዳወጀችላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ ገለጡ።
ብፁዕ ካርዲናል አማቶ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፦ አባ ፐድሮ አሱዋ መንዲያ በሥነ ምህንድስና ሊቅነት ካስመሰከሩ በኋላ ካህን በመሆን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ እግዚአብእሔር የለገሰላቸው ጥሪ በመቀበል እ.ኤ.አ. በ 1942 ዓ.ም. አቢይ መሃላ ፍጽመው በነበራቸው የሥነ ሕንፃና ምህንድስና ሊቅነት መሠረት በስፐይን የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን በመገንባትም ሆነ ታሪካዊ ቅድሳት ሥፍራዎችንም በመንከባከብና በማደስ ተልእኮ ወደር የማይገኝለት አገልግሎት ያበረከቱና አገልግሎታቸውም በዚህ ብቻ ሳይታጠር በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ትምህርተ ክርስቶስ በማስተማር ወጣቶችን በማነጽ ክርስቶስን በመምሰል የኖሩ መሆናቸ ገልጠው፣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በስፐይ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክስቲያን ስደትና መከራ እንዳጋጠማትና የአምልኮና የስግደት ባጠቃላይ የሃይማኖት ነጻነት ታግዶ አቢያተ ክርስቲያን በማርከስ ወደ ብሔር የአገልግሎት መሳጫ ሕንፃ በመቀየር አሊያም በማፍረስ የደረሰባት ስደት የአባላቶቿ ሞትና ስቃይ ጭምር ምክንያት እንደነበርም አስታውሰው፣ አባ ፐድሮ አሱዋ መንዲያ የክህነት ጥሪያቸውን አለ ምንም ፍራት በመኖር ወንጌል በቃልና በሕይወት በመመስከር የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ የክላሪቲያን ልኡካን ማኅበር አባል መሆናቸው ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ሰማዕታትን የምታከብረውና የምታስታውሰውም ታማኝ የወንጌል ምስክሮች በመሆናቸውና ኢየሱስ በመስቀል ስለ ሰቀሉት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሲል ወደ አባቱ ያሳረገው ጸሎት የኖሩና ለሞት ለዳረጉዋቸው ሁሉ ምህረትን የጸልዩ የእምነት ጀግንነት መስካሪያን በመሆናቸው ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ በርቢ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.