2014-11-03 15:11:28

በሞት ከሕይወት ጋር እንገናኛለን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ሙታን ዘክራ መዋልዋ ሲገለጥ። በዚህ ክርስቲያናዊ ባህል መሠረትም ምእመናን በጠቅላላ ሕዝብ ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ጸሎት በማሳረግ ከዚህ ዓለም የተለዩትን ውዶቻቸውንና በሞት ከምድራዊ ሕይወት ለተሰናበቱት ሁሉ በመጎብኘት ቅዳሴ በማስቀደስ ሙታን ዘክሮ የዋለበት ቀን ሲሆን፣ ስለዚ በዓል በማስመልከት በጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ መምህር አባ ጁሊዮ ማስፐሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ሞት የሚዘነጋ ስለ ሞት እንዳይታሰብ የሚዳርግ የተለያየ ተግባር ይፈጸማል፣ ስለ ሞት እንዳይታሰብ በዓለም የሚከናወነው ተግባር ብዙ ነው። ሞት እንደሌለ እያሰብክ ትኖር ዘንድ የሚገፋፋ ሞትን የሚፈራ አደናጋሪ ባህል በዓለም የሚታይ ነው። ሞት የተረጋገጠ፣ አንድ የሕይወት ምዕራፍ እንጂ የሕይወት መደምደሚያ ወይንም የሕይወት ፍጻሜ አይደለም። ያንን መወለድ የሆነውን ሞት ላለ መፍራት ከተፈለገ የእምነት ጽናት ወሳኝ ነው። ሕይወት የእኛ እይደለችም ከሕይወት እንወለዳለን ወደ ሕይወት እንወለዳለን በሞት አማካኝነት ደግሞ በሰማያዊ ቤት እንወለዳለን ስለዚህ በዚያ ዘለዓለማዊ ሕይወት ስንገኝ በሰማያዊ ቤት እንወለዳለን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ አማካኝነት ወደ እውነተኛው ሕይወት እንድንገባ በሩን ከፍቶልናል፣ ስለዚ ሞት ሊያስፈራን አይገባም፣ ሞት ከሕይወት ጋር የምንገናኝንበት የሕይወት ምዕራፍ መሆኑ ሞታችንን በመሞት በትንሣኤው አረጋግጦልናል። ውዶቻችን ወደ ተቀበሩበት የመቃብር ሥፍራ በመሄድ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ዕረፍት ይስጣቸው ዘንድ እንጸልያለን፣ ዘለዓለማዊ ዕረፍት ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያመለክት ጸሎት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.