2014-11-03 15:02:23

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለቅድስና የማራቶን ውድድር ተሳታፊዎች ሰላምታ አቀረቡ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ቅዱሳን ዕለት አክብራ በዋለችበት ዕለት የዶን ቦስኮ ማኅበራት በዓለም እንዲሁም የትንሿ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ማኅበር በጋራ ያዘጋጁት የማራቶን ውድድር ለቅድስና እርሱም ስፖርት ክርስቲያናዊ ምስክርነትና በሰብአዊ አገልግሎት የተሰኙትን ዓላማዎችን በማጉላት መካሄዱ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ አጠናቀው እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው እንዳበቁ በዚያ የማራቶን ውድድር ለቅድስና በተሰኘው የስፖርት መርሃ ግብር ለተሳተፉት ሁሉ የሰላምታ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ የስፖርት ውድድር ውደራ ላይ ያተኰረ ሳይሆን ክርስቲያን በዚህ ምድራዊ ሕይወቱ ለቅድስና የተጠራ መሆኑ ተገንዝቦ ከዚህ ክርስቲያናዊ ጥሪው ጋር በሚመሳሰል ጎዳና ወደ ቅድስና በሚመራው መንገድ ዕለት በዕለት ሩጫውን እንዲያቀና እንዳለበት ለቡ የሚለውን ክርስቲያናዊ ጥሪና ኃላፊነት ለሁሉም ለመመስከር ያለመ እንደነበር ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ክርስቲያን በገዛ እራሱ ሳይዘጋ በሚኖርበት ኅብረተሰብ በዕለታዊ ኑሮው ክርስትናውን እየኖረ በቃልና በተግባር ለሁሉም ክፍት የሆነ ክርስትና በመኖር ለቅድስትና መጠራቱን እንዲመሰክር የሚያነቃቃ የስፖርት መርሃ ግብር መሆኑና ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ብላ ያወጀችላቸውን ተመስሎ የእነርሱን ሕይወት በድግግሞሽ አለ የገዛ እራሱ የጥሪ መለያ መኖር ማለት ሳይሆን ቅድሳን ቅድስና የሚደረስ ጥሪ መሆኑ የሰጡትን አብነት በመከተል እያንዳንዱ ክርስቲያን በሚሰጠው የጥሪ ጸጋ አማካኝነት እንዲመሰክረውና እንዲኖረው የሚያነቃቃ መርሃ ግብር መሆኑ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፦ ሁሉም ክርስቲያን ለቅድስና የተጠራ ነው፣ ስለዚህ የቅድስና ሕይወት በተለያየ መልኩ እግዚአብሔር በለገሰላቸ ጥሪ አማካኝነት በትጋት በመኖር ቤተ ክርስቲያን ቅድሳት ብላ ያወጀችላችው በዚህ ምድራዊ ሕይወት ክርስቶስን በመምሰል ለመኖር መጠራታችን እንድናስተውል የሚያነቃቁ አብነቶች ናቸው። በመሆኑም የተካሄደው የማራቶን ውድድር ያነገበውም ክርስቲያን ለቅድስና የተጠራ የሚል ዓላማ እንደነነበርም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.