2014-10-27 15:44:55

የሥነ ጾታዊ ስሜት ትምህርት በቤተሰብ ላይ የሚሰነዘር የጥቃት ኅልዮ


RealAudioMP3 ጋዜጠኛና ደራሲ ማሪዮ አዲኖልፊ አምነስት ኢንተርናሽናል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር ስለ ፆታዊ ስሜት ትምህርት በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም አቢያተ ትምህርት ስለ ፆታዊ ስሜት ለሚሰጠው ትምህርት እንዲከተሉት በማለት አንዳዊ ፆታዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች ስለ ሚኖሩት ዓይነት ፆታዊ ስሜትና ወንዳ ገረድ ፆታዊ-ስሜት ያላቸውን የሚጠላና የሚያገል ባህል በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመቃወም” በሚል ርእስ ሥር ያወጣው አጭር የመመሪያ ጽሑፍ አስመልከተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ቤተሰብ ለአደጋ ከሚያጋልጠው ኅልዮ መከላከል አስፈላጊ ነው። ይኽ የአምነት ኢንተርናሽናል መመሪያ አደገኛ ኅልዮ ነው” በማለት ገልጠው በፆታና ፆታዊ ስሜት መካከል ምንም ዓይነት ግኑኝነት የለም የሚለው ሃሳብ የተኖርበት የመመሪያ ጽሑፍ በእውነቱ መሆናዊ መግለጫ የሚጻረር ኅልዮ ነው። ሌላው አሳሳቢው በዚህ የመመሪያ ጽሑፍ የሰፈርው እርሱም ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል የሚል መሠረታዊ ባህርይ በማካተት አንዳዊ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል ሊጸና የሚችልና እነዚህ አንድ ዓይነት ፆታዊ ስሜት ያላቸው ዜጎች ወላጃ አልባ የሆኑትን ለማሳደግ ይችላሉ የሚለው የአሳዳጊ ወላጅ መብትና ኃላፊነት የሚፈቅድ በእውነቱ የሰብአዊ መብትና ክብር ብሎ በመግለጡ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰው የዚህ ዓይነት አመለካከት የሚቃወም ከሆነ እንደ አምነስት ኢንተርናሺናል አገላለጥ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር ተብሎ ይገለጣል ማለት ነው።
አንዳዊ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ አለ መቀበል ወይንም መቃወም የዚህ ዓይነት ፆታዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች ጠላት መሆን ማለት አይደለም፣ ስለዚህ የዚህ ዓይነቱ ጋብቻ የሚቃወም አብላጫው የዓለም ሕዝብ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር ነው ብሎ መግለጡ በእውነቱ ስህተት ነው። የዚህ ዓይነቱ ጋብቻ መቃወም ወንዳ ገረ ወይንም አንዳዊ ጾታ ስሜት ያላቸው ሰዎች መጥላት ወይንም ማግለል ማለት አይደለም ብለው፣ በቅርቡ እሳቸው ያነሳሱት መስቀል የሰየሙት ዕለታዊ ጋዜጣ ለኅትመት እንደሚበቃ ገልጠው ይኽ እለታዊ ጋዜጣ አምነስት ኢንተርናሺናል ያወጣው የሥነ ፆታ ትምህርት አሰጣጥ መመሪያ በጥልቀት በመመርመር ኅልዮ እንጂ መሠረት ያለው ሃሳብ አለ መሆኑ የሚያብራራና ከዚህ ጋር በማያያዝም ባጠቃላይ የሞት ባህል እርሱም ጽንስ ማስወረድ ገና መድሃኒ ባልተገኘለት በሽታ የተጠቃው ጣፋጭ ሞት በሚል ውሳኔ መሠረት ለሞት መዳረግ የተሰኙት አመለከታቶች በተመለከተ ጽሑፍ የሚያቀርብ የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ መሆኑ ገልጠው፣ ጋዜጣው መስቀል የሚል መጠሪያ የሰጡበት ምክንያትም ሕይወት ባጠቃላይ ሰብአዊነት የሚመለከትና ሕይወት ከሞት ወዲያ ትንሣኤ እንደሚጠብቅ በመገንዘብ መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.