2014-10-27 15:50:52

በኤውሮጳ ምስራቃውያን አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ


RealAudioMP3 የመላ ኤውሮጳ አገርች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሚያቅፈው የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት ሥር የሚተዳደረው በኤውሮጳ የሚገኙት የምስራቅ ሥርዓት የሚከተሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ በኡክራይን የምትገኘው የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት የተጠራው ጉባኤ የኪየቭና ሃልየ ክቡርነታቸው አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ሸቭቹክ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በንግግር እንዳስጀመሩ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ይኽ በኡክራይን ለኦፖሊ ከተማ የምስራቃውያን አቢያተ ክርስቲያን በኤውሮጳ ተልእኮና ሚና” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በመካሄድ ላይ ባለው የኤውሮጳ ምስራቃውያን አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ ከ 20 የኤውሮጳ አገሮች የተወጣጡ 45 የምሥራቅ ሥርዓት ለሚከተሉት ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት እያሳተፈ ሲሆን፣ ክቡርነታቸው አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሸቭቹክ በጉባኤው መክፈቻ ባሰሙት ንግግር፣ ጉባኤ በኡክራይን የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊነቷ ተቀባይነት ያገኘበት ዝክረ 25ኛው ዓመት በሚታሰብበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ድርብ ትርጉም ያለው ነው ሲሉ በኡክራይን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ኤድዋርድ ጉሊክሶን ባሰሙት ንግግር፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንዲሁም እኔ ልኡካቸው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በኤውሮጳ የሚገኙት የምስርቅ ሥርዓት የሚከተሉት አቢያተ ክርስቲያን ሚናና ተልእኮ ያለው አስፍፈላጊነት አቢይ ነው። ስለዚህ ይኽ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተረጋገጠ ነው” እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ለአንድነት ታልሞ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚካሄደው የጋራው ውይይት ርእስ ዙሪያ የሚመክርና ክርስቶስ እግዚአብሔር የተመኘው ጸሎት ያደረገበት የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን አንድነት የሚለው ቅዱስ ፍላጎት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማሳሰብ የአቢያተ ክርስቲያን አድነት በማነቃቃት ያስጀመረው ጉዞ ቀጣይ መሆኑ ሁለተኛው የቫቲካን ጉብኤ ስለ አቢያተ ክርስትያን አድነት ባመለክተው ሃሳብ ዙሪያ ጭምር ውይይት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ በለኦፖሊ የላቲን ሥርዓት የምተከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማይዝይስላቭ ሞክዝይቺክ ለተገባእያኑ ሰላምታ በማቅረብ ቤተ ክርስትያን እንዲት ቅድስት ካቶሊካዊትና ሐዋርያዊት ነች የሚለው አንቀጸ እምነት በማበከር ለሁሉም ተጋባእያን ወንድማዊና ልባዊ ሰላምታ እንዳቀረቡ ሲር የዜና አገልግሎት ገልጦ፣ የሮማኒያ የኦራደአ ማረ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቪርጊል በርቸአ፦ የክርስትናው እምነት በግልና በማሕበራዊ ሕይወት የሚገለጥ ነው። ስለዚህ በግል ሕይወት ብቻ ታጥሮ እንዳይቀር፣ በማሕበራዊ መድረክ የእሴቶች የሥነ ምግባርና ግብረ ገብ እሴቶች የሕይወት ክቡርነት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር በቃልና በሕይወት መስካሪ መሆን አለበት” እንዳሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.