2014-10-22 18:41:47

ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ ሰውነት ናት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስለቤተክርስትያን ማንነትና ባህርያት ለረዥም ግዝያት በሳምንታዊው የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ የሚያስተምሩትን ትምህርት በመቀጠል ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዱስ ጳውሎስ “የክርስቶስ ሰውነት” ብሎ ቤተ ክርስትያንን በሚሰይመው ርእስ ሰፊ ትምህርት አቀረቡ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ ሰውነት ናት ሲል ምን ማለት ይሆን በማለት ትምህርታቸውን የጀመሩ ቅዱስነታቸው ወደ ሰውነታችን መለስ በማለት በመጀመርያ አንድነትን የሚያመለክት ሲሆን በሌላው በኩል ደግሞ ብዙ አካላትና ሕዋሳት እንዳሉት ለማመልከት ነው ብለው፣ በትንቢተ ሕዝቅኤል እንደተመለከተው እግዚአብሔር ሕዝቅኤል ነቢይን በደረቁ አጥንቶች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲወርድና ሕይወት እንዲዘሩ በትንቢት ሊናገር እንደጠየቀው እና ሕዝቅ ኤል በትንቢት በተናገረበት ጊዜ ደረቅ አጥንቶቹ መጀመርያ ሥጋና ቆዳ መልበሳቸው በመጨረሻም በእግዚአብሔር መንፈስ ሕይወት መዝራታቸው የቤተ ክርስትያን ምሳሌ መሆኑንም ገልጸዋል፣ ቤተ ክርስትያን በመንፈስ ቅዱስ ሕይወት አግኝታ በአዲስ መልክ ከክርስቶስ ጋር ሕያው የሆነችና በመከተሉና በፍቅሩ ከእርሱ ጋር የተዋሃሃደች ስለሆነች በምሥጢረ ጥምቀት እኛ ሁላችን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በመንፈስ ቅዱስ የዚሁ በክርስቶስ የሚገኘው አዲስ ሕይወት ተካቫዮችና ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ራሷ በሆነችው በቅድስት ቤተ ክርስትያን ከእርሱ ጋር አንድነት አግኝተናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ የዚህ መተሳሰርና ፍቅር ኃያልንትን ለመግለጥ በሙሽራና ሙሽሪት መካከል ያለው ፍቅርና መተሳሰርን እንደምሳሌ በማቅረብ ቤተ ክስትያንም ከክርስቶስ ጋር ያላት አንድነት እንደዚሁ ባልና ሚስት አንድ አካል ይሆናሉ እንዳለው ቅዱስ መጽሓፍ መሆኑን ይገልጣል፣ የዚህ አንድ አካል አባሎች በመሆናችን መጠንም ለመለያየትና ለመጣላት የሚቀርቡንን ፈተናዎች በማሸንፍ በአንድነት መኖር አለብን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተረድተን እና የተለያዩ ስጦታዎቹን በምስጋና ተቀብልን የክርስቶስ ሰውነት የሆነችውን ቤተክርስትያን አንድነት ለመገንባት ያስችለን ሲሉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባጭሩ አስተምረዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ እፊታችን ኅዳር ወር ከ28 እስከ 30 በቱርክ ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣ መርሓ ግብሩ እንደሚያመለክተውም በቱርክ ሰዓት አቆጣጠር አንድ ሰዓት ላይ ኅዳር 28 ቀን በአንካራ ተገኝተው የአታቱርክ መታሰቢያ ቦታን ጎበኝተው ከመንግሥት ባለስልጣናትና ከአገሪቱ ፕረሲደንት ጋር ይገናኛሉ፣ በነገታው ኅዳር 29 ቀን ደግሞ ወደ እስታምቡል በመጓዝ የቅድስት ሶፍያ ቤተ መዘክርና የሱልጣን አሕመድ መስጊድ ጐበኝተው በከተማው በሚገኘው የመንፈስ ቅዱስ ካተድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በመሥዋዕተ ቅዳሴው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፓትርያርክና ተክታዮቻቸው እንደሚሳተፉና ከቅዳሴው በኋላ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በርጠለሜዎስ አንደኛ እንደሚገናኙም ተምልክተዋል፣ በሚቀጥለው ዕለትም እሁድ ኅዳር 30 ቀን ቅዱስነታቸው በፓትርያርካዊትዋ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን በሥር ዓተ ጸሎት እንደሚሳተፉና ከፓትርያርክ በርጠለሜዎስ አንደኛ በአንድነት የኅብረት መግለጫን ፈርመው ያቀርባሉ፣ በዕለቱ ማምሻም በሮም ሰዓት አቆእጣጠር ስድስት ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ቻምፒኖ አየር ማረፍያ ሮም እንደሚመለሱ ተመልክተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.