2014-10-21 11:37:13

የእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ 6ኛ ሥርዓተ ብፅዕና


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴና በእኩለ ቀን ላይ ደግሞ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋዳያን ባስተማሩት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በሁለት ታላላቅ የዘመናችን ፍጻሜዎች ላይ በማትኰር ለመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እርካታ በሚሰጥ መንፈስ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነበሩ ጳውሎስ 6ኛ ሥርዓተ ብፅዕና በማወጅና በዘመናችን ታላቅ ችግር ሆኖ ላለው የቤተሰብ ችግር መፍትሔ ለማግኘት ለአንድ ዓመት በኋላ ለሚካሄደው አጠቃላይ ሲኖዶስ መሪ ሓሳቦች ለመለገስ የተጠራው ልዩ ሶስተኛ የመላ ካቶሊዊት ቤተ ክርስትያን የጳጳሳት ሲኖዶስ በመደምደም ብፁዕ ዮሓንስ 6ኛን በተመለከተ “የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ትሑት ምስክርና ነቢይ” በማለት ስብከትና አስተምህሮ አቅርበዋል፣
በአደባባዩ ከሰባ ሺ በላይ ምእመናን እንደነበሩ እንዲሁም በቤተ ክርስትያን ታሪክ ውስጥ ልዩ ትዕይትንት እየሆነ የሚታዘበው የልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ከቅዱስነታቸው ጋር አብሮ በትላላቅ ፍጻሜዎች መገኘት ደምቆ ውለዋል፣
ያለነው ዘመን እንደቅዱስነታቸው አገላለጥ “ተስፋቢስ ዘመን” ሆኖ ይታያል ነገር ግን እግዚአብሔር ቤተክርስትያኑን ትቶ ስለማይተው “በቤተሰብ ዙርያ በእውነተኛ ነጻነትና ትሑት ፈጠራ በዘመናችን ተስፋን እንደገና ለማብራት በተደረገው ልዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደምደም” እንዲሁም የዘመናችን “የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ትሑት ምስክርና ነቢይ” የሆነው የእግዚአብሔር አገልጋል ጳውሎስ 6ኛ ሥር ዓተ ብፅዕና መፈጸም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መሆንን አገንዝበዋል፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ለዕለቱ የቀረበው ቃለ ወንጌል የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ደግሞ ለእግዚአብሔር ስጡ የሚል ነበር፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ቃል የተናገረው ሊፈትኑት እና ስሕተት በማግኘት ሊከሱት በማቀድ ፈሪሳውያንና የሕግ ሊቃውንት ለቄሣር ግብር መክፈል የሚገባ ነገር ነው ወይ ብለው በተንኮል ለጠየቁት የሰጠው መልስ ሲሆን በወንጌሉ እንደሚያመለክተው “ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ። እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ? የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት። እርሱም። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው። የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ። እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው” (ማቴ 22፡20-22) የሚል ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ይህ ሁሌ የኅልና ችግር ያላቸው ሰዎች የሚያቀርቡት ጥያቄ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ይህ መልስ ጌታ የኅልና ችግር ላላቸው የሚሰጠው መልስ ነው ከሁሉ በላይ ደግሞ እንዲመቻቸው ብለው ለሃብታቸውና ለክብር ቦታቸው እንዲሁም ለሥልጣናቸውና ለዝናቸው ለሚታገሉት የሚሰጠው መልስ ነው፣ ይህም ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ እይሀኦነው ነው፣
ቅዱሳንና ብፁዓን የመምህራቸውን ፈር በመከተል ለዚህ ዓይነት ትግል እንዳሸንፉ በታሪክ በተደጋጋሚ የታየ ሲሆን በዕለቱ ሥር ዓተ ብፅ ዕናቸው የተፈጸመው ብፁ ዕ ጳውሎስ 6ኛ ገና ወጣት ሳሉ በፕዮስ 11ኛ እና 12ኛ ሥር ሆነው በአስቸጋሪው የፋⶥሽትና የሁለተኛ ያዓለም ጦርነት አስከፊ ስቃይዎች ሲያገልግሉ እንዲሁም በሚላኖ ሃገረስበብከት በታታሪነትና በእረኛ መንፈስ ተል እኮ አቸውን ሲወጡ በመጨረሻ ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በመጀመርያ እንደካርዲናል በሁለተኛ ደረጃም ቅ.ዮሓንስ 23ኛ ያቋረጡትን እሳቸው ር.ሊ.ጳ ሆነው ተመርጠው ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ለመፈጸም ያሳዩት ጥበብና የተሸከሙት መስቀል ቀላ አልነበረም ግን የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የቄሳርን ደግሞ ለቄሳር በማቅረባቸው ለዚሁ መዓርግ እንደበቁ ገልጠዋል፣
በዕለቱ የተፈጸመው የካቶሊካዊት ቤተክራይትን ልዩ ሲኖዶስም ተመሳሳይ ችግን እየገጠመው መሆኑንና ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት በኅበረት መጸለይ እንዲሁም በትሕትና መመለስ እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ ስለ ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ትሕትናና ጥበብ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፣ በአስቸጋሪ ጊዜ በት ዕግሥት በጸሎትና በታላቅ ትህትና ለጊዜው የሚሆን ሁነኛ እርምጃ ለወሰደው ለብፁዕ ጳውሎስ 6ኛንም ሳያመስገኑ ለማለፍ ስላልወደዱ በሰማይ ከመላእክት ጋር ሆኖ በዓሉን ለሚሳተፈው ብፁዕ እንዲህ ሲሉ አመስገነውታል፣
“እግዚአብሔር ይስጥልን! እግዚአብሔር ይስጥልን ውድና የተፈቀርክ ጳውሎስ 6ኛ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለቤተክርስትያኑ ፍቅር ባሳየኸው ትሑትና ትንቢታዊ ምስክርነት እናመሰግንሃለን እግዚአብሒር ይስጥልን ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.