2014-10-20 16:28:02

ሲኖዶስ
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የቤተ ክርስቲያን በር ዘወትር ክፍት ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተሰብ ዙሪያ የመከረው ልዩ ሦስተኛው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መዝጊያ ምክንያት ተገኝተው፦ “የርክስቶስ ቤተ ክርስቲያን በሮችዋን በርግዳ ክፍት አድርጋ መኖር አያስፈራትም የተከፍቱ በሮች ነው ያሉዋት” በማለት በተካሄደ የሲኖዶሱ ውይይት አልፎ አልፎ የጦፈ ውጥረት ያለው የሚያስመስለው ውይይት ቢታይበትም ምክክር ጸጋና ውበት የተረጋገጠትና ቤተ ክርስቲያንና ብፁዓን ጳጳሳት የእግዚአብሔርን መንጋ መጋብያን የጠፋውን የሚፈልጉና የሚያስተናግዱ መሆናቸው እንዳብራሩ የቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ አስታወቁ።
“በተቀለመው በተጻፈው እርሱም በቃላት በተደረደረው ሕግ ላይ መዘጋት ለእግዚአብሔር አግርሞት ገዛ እራስ ክፍት አለ ማድረግ ይሆናል፣ ለእግዚአብሔር ግርምቶች ክፍት አለ መሆን ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት አለ መሆን ያስከትላል። በሕግ ብቻ በመታጠር በሕግ ውስጥ ብቻ በመኖር ሕግ በሚያጸናው እርግጠኛነት መጽናት ከጥንት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን ጀምሮ የነበረ ዓቢይ ፈተና ነው፣ ይኽ ደግሞ ቅጥ የለሽ ቀናተኞች ይኖሩት የነበረ ሕይወት እና የሊቃውንት ፈተናም ጭምር ነው ለማለት ይቻላል” ከዚህ ጋር በማያያዝ የሚያጎበድድ ትህትና በአጎብዳጅነት የሚኖር የዋህነት ከዚያ ገንቢ ከሆነው ትህትና ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት እንደሌለው አብራርተው፣ ተራማጆችና በገፍ ባይ ነጻነት በመከፋፈል በቅርቡ በሲኖዶስ አበው የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ሲሰጡት የሰነበተው አገላለጥ በውስጥ ታዋቂነት በማስመልከትም፦ “አታላይ የሆነ ምህረት እርሱም የታመመውን እንዲድን በሽታው ከሥር መሰረቱ ለማጥፋት ጥረት ከማድረግ በመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ አቅርቦት ማሰናበት የሚል ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከማስቀደምና ይኸንን ከመኖር ይልቅ እንዲነጻና ለእግዚአብሔር መንፈስ እንዲገዛ መመራት የሚገባውን ሰው ለማስደሰት እየተባለ ለዓለም መንፈስ መገዛት ፈጽሞ አይገባም። ድንጋዮችን ወደ እነጀራ የለወጠው የጌታ ተአምር ዘክረው “ዳቦውን ወደ ድንጋይ በመለወጥ ኃጢአተኞችን መውገሪያ የምንጠቀምበት እንዳንሆን። ይኽ ደግሞ ከመስቀል የመውረድ ፈተና ነው የሚመስለው። እቃቤ እምነት አዎ የእምነት አቃቤነት ባህርይ የእምነት ጠባቂነት የሚያመለክት በተጨባጩ ሁነት ለመጠቀም እየተባለ መሠረታዊ ይዞታው ችላ በማለት እንዳሻህ ለመጠቀም አደጋ ማጋልጡ አይገባም” በቅርቡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመካሄድ ላይ የነበረው ሲኖዶስ በማስመልከት ይሰጡት የነበረው ዜናና መግለጫ በእውነቱ የእርስ በእርስ መጣላት የሚኖርባት ቤተ ክርስቲያ ያስመሰለና በዚህ መፍነስ ቤተ ክርስትያንን ሲያቀርቡ እንደታየም ዘክረው፣ የተካሄደው ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን ዓንቀጸ እምነት እጥያቄ ውስጥ አለማስገባቱ ያለው አንገብጋቢነት አስታውሰው፣ ምስጢረ ተክሊል የማይፈታ የታማኝነት ቃል ኪዳን ለሕይወት ክፍት የሆነ የሚለው በአንቀጸ እምነት የተመለከተው እውነት እጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሲኖዶስ እንዳልሆነ ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን እጅጌዋን አጥፋ የሰዎችን ቁስል ለመፈወስ ጥሪያ መኖር አያስፈራትም ሕይወትዋም እርሱ መሆኑ አብራርተው፣ በሚያምር የመስታወት ቤት ውስጥ ተቀምጣ የምትፈርድ ሰዎችን ደረጃ በደረጃ የምታስቀምጥ እንዳልሆነች ገልጠው “ቤተ ክርስቲያን አንዲት ቅድስትና ካቶሊካዊት ሐዋርያዊት ነች፣ ሐዋርያት የእርሷ ምህረት የሚያፈልጋቸው ኃጢአተኞች እንጂ ፍጹማ አይደሉም፣ ቤተ ክርስቲያን ይህች ነች፣ እውነተኛይቱ የክርስቶስ ሙሽራ፣ ለሙሽራዋና ለዓንቀጸ እምነት ታማኝ ነች፣ ከቀራጮች ከአምንዝራዎች ጋር በአንድ ማዕድ መቀመጥ (ሊቃ.15 ተመልክት) አያስፈራትም፣ ቤተ ክርስቲያን ለድኾች በስቃይ ለሚገኙት የተበረገደ በር ያላት ለቅን ሰዎች ገዛ እራሳቸውን ፍጹማን አድገር ለሚገምቱት ብቻ ሳይሆን በኃጢአታቸው ለሚጸጸቱት ሁሉ በሮችዋ ክፍት ነው” ቤተ ክርስቲያን በሚወድቀው ወንድም የማታፍር ወይንም ሲወድቅ እያየቸው እንዳላየች ተኵኖ የሚኖርባት እንዳልሆነች ሲያመለከቱም፦ የወደቀው ከወደቀበት ተነስቶ እውነተኛውን ጉዞ እንዲከተል ከወደቀበት በማንሳት ወደ እውነተኛው መገናኘት ወደ ሆነው እርሱም ከሙሽራዋ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም የሚከወነው ግኑኝነት ከወዲሁ ይኸንን አልሞ እንዲጓዝ ትሸኘዋለች። ተቀዳሚው የእረኞች ኃላፊነት መንጋውን መመገብ ነው። ጌታ በእነርሱ ኃላፊነት ስር ለሰጣቸው በአባታዊና በምህረት መንፈስ በማስተናገድ ነገር ግን ከማስተናገድ በፊት መፈለግ ፈልጎ አግኞቶ ማስተናገድ ስለዚህ የጠፋቸው ለመፈለግ መውጣት እንዲኖር የሚል ነው ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጠቅሰው “በቤተ ክርስቲያን እረኞች አማካኝነት ክርስቶስ መንጋውን ይንከባከባል” ሉትን ሃሳብ ጠቅሰው ቤተ ክርስቲያን መንጋውን ታሰማራለች፣ ሲያጠፋም ታርመዋለች እጅግ እንደምታፈቅረውም በተጨባጭ ትገልጥለታለች፣ “ብፁዓን ጳጳሳት ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ውህደት ያላቸው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የማቀብ ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው፣ ይኽም በአገልጋይነት እንጂ በባላበትነት መንፈስ እይደለም” ብለው፦ “የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምንም’ኳ ሙሉ ቀጥተኛ የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መሪ ቢሆኑም የበላይ ጌታ ማለት ሳይሆን የበላይ አገልጋይ፣ የጌቶች ጌታ ሳይሆን የአገልጋዮች አገልጋይ ናቸው። ‘Servus servorum Dei-የእግዚአብሔር አገልጋዮች አገልጋይ’ የተአዝዞ ዋስ፣ ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ተመስላ በተግባር ይኽንን ለመኖርዋ ጥሪ ዋስ፣ ምንም’ኳ በክርስቶስ ፈቃድ የተመረጡ በመሆናቸውም በገዛ እራስ የሚሰጠው ግላዊ የእራስ ፍርድ ወደ ጎን የሚይደርጉ፣ በሕገ ቀኖና አንቀጽ 149 ‘የምእመናን መጋቤ (እረኛ) ና ተንከባካቢ (ሃኪም)’ ማለት ነው” ሱሉ ያሰመጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ መኒከቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.