2014-10-17 19:18:53

የአምልኮት ጸሎት ከባድ ነው ነገር ግን ደስታ ይሰጣል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትናው ዕለት እንደልማዳቸው በቅድስት ማርታ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ “የተለያዩ ጸጋዎች መለመን ቀላል ነው የምስጋና ጸሎት ማሳረግ ግን እጅግ ከባድ ነው ነገር ግን እውነተኛ ደስታን የምትሰጥ ይህች ጸሎት ናት” ሲሉ እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በማቅረብ ስታመልክ ብቻ መሆኑን ገልጠዋል፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ ከቀረቡት ንባባት የመጀመርያው የቅዱስ ጳውሎስ መል እክት ወደ ኤፈውሶን ሰዎች 1፤1-10 ሆኖ “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።” የሚል የምስጋና ጸሎት ይገኝበታል፣ ይህ ጸሎት ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በማቅረብ የአምልኮ ጸሎት ስለሆነ ደስታ የሚመራ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ተቸግረን አንዳንድ ነገሮችን ከእግዚአብሔር ለመጠየቅ ስንፈልግ መጸለይ እናውቃለን እንዲሁም የፈለግነውን ባገኘን ቍጥር ጌታን እናመሰግናለን፣ ነገር ግን የአምልኮ ጸሎት ለማሳረግ ይከብደናል፣ ጌታን ማክበርና ማምለክ እምብዛም የተለመደ አይደልምና፣ ይህንን ዓይነት ጸሎት ለመለማመድ ጌታ በሕይወታችን ስላከናወናቸው ነገሮች ስናስብና አምልኮና ስግደት ስናቀርብ ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን” የሚለውን በማሰብ ስለመረጥከኝ ቡሩክ አንተ እግዚአብሔር ጌታ ሆይ ቡሩክ ነህ ብለን አምልኮ ያቀረብን እንደሆነ የእግዚአብሔር አባታዊና ፍቅራዊ ቅርበት ደስታ ሊሰማን ይችላል፣
የአምልኮ ጸሎት ለማቅረብ መጀመርያ የሚያስፈልገው ታሪክህን ማስታወስ ነው፣ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ዓለም ሳይፈጠር መረጠን ይላል ነገር ግን ይህንን ልንረዳው አንችልም፣
“እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እኔን ማወቁና መምረጡ ስሜ በልቡ መኖሩ ልትረዳውስ ይቅር ልታስበውም የሚቻል አይደለም፣ ነገር ግን እውነቱ ይሄ ነው፣ ይህ በመንፈስ ቅዱስ አስተፍንሶ የተገለጠልን እውነት ነው፣ ይህንን የማናምን ከሆነ ከነአካቴው ክርስትያኖችም አይደለንም፣ ምናልባት ደረቅ በሆነ እምነት ክርስትያኖች ነን ለማለት እንችል ይሆናል ግን ክርስትያን አይደለንም፣ ክርስትያን ማለት የተመረጠ ማለትም በእግዚአብሔር ልብ ስሙ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተጻፈ ፍጥረት ነው፣ ይህንን የምናምን ከሆነ ይህንን ብቻ ማስተንተን ልባችንን በደስታ ይሞለዋል፣ የደህንነት እርግጠኝነትም ይሰጠናል፣ እሰቡት እስቲ ስማችን በእግዚአብሔር ልብ እንደ በእናቱ ማኅጸን ያለው ሕጻን ሲኖር ምንኛ ያህል ደስ ያሰኛል፣ የደስታችን ምንጭም የተመረጥን መሆናችን ማወቅና ማመን ነው፣ ይህንን ለመረዳት በኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢር መግባት አለብን እርሱ የተወዳጅ እግዚአብሔር አብ ምሥጢር ነው፣ ደሙን በማፍሰስ ደግሞ የእግዚአብሔር አብ ፍላጎት ፈቃድ ምሥጢር አሳወቀን፣ ስለዚህ በምሥጢሩ ጠለቅ ብሎ ለመግባት ይህ ሶስተኛ ዝንባሌ ማለት ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ በምድር ይሁን ብሎ ብቻ መለፍለፍ ሳይሆን ራሱ ጌታ በጌታ ሰማኒ ደም እስኪያልበው ድረስ ለምኖ በመጨረሻ ፈቃድህ እንጂ ፈቃዴ አይሁን ብሎ ሁሉን በእግዚአብሔር ፈቃድ በመተው አስተማረን፣
“መሥዋዕተ ቅዳሴ በምናሳርግበት ጊዜ በሶስተኛው ምሥጢር እንገባለን ይህንንም እንደገና በሙላት ልንረዳው አንችልም፣ ሕያው የሆነው የጌታ በክብሩ መካከላችን መኖሩንና ሕይወቱን እንደገና ለእኛ መሥዋዕት ማቅረቡ ነው፣ በዚህ አግባብ ወደ እግዚአብሔር ምሥጢር ጠለቅ ብለን ለመግባት ከፈለግን በየዕለቱ ቀስ በቀስ ልንማረው ያስፈልጋል፣ ክርስትያን የሆነ ሁሉ በዚህ ምሥጢር ለመግባት የሚታገል ነው፣ ምሥጢርን ልንቆጣጠረው አንችልም መሳተፍ ብቻ ነው ያለብን፣ ሲሉ ትልቁና ጥልቁ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሆነው ምሥጢረ ቍርባን የአምልኮ አችን ጠርዝ መሆኑን በመግለጥ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.